Saturday, June 10, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትመፍትሔ የሚሻው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጎል ድርቅ

መፍትሔ የሚሻው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የጎል ድርቅ

ቀን:

በኢንስትራክተር አብርሃም መብርሃቱ የሚሠለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን (ዋልያዎቹ) ስብስብ እስካሁን በምሥራቅ አፍሪካ በደካማነቷ ከምትጠቀሰው ጅቡቲ በስተቀር በሌሎች አገሮች ላይ የሚስተዋልበት ጎል የማስቆጠር ክፍተት፤ ባለፈው ረቡዕ ነሐሴ 29 ቀን 2011 .. 2022 ኳታር የዓለም ዋንጫ የመጀመርያ ቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የሌሶቶ አቻውን በባህር ዳር ስታዲየም አስተናግዶ ጨዋታውን ያለ ጎል በአቻ ውጤት ማጠናቀቁ ማረጋገጫ ሆኗል፡፡

በባህር ዳር በነበረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የኢትዮጵያ ቡድን ጨዋታውን በሜዳውና በደጋፊው ፊት እንደማድረጉ አልፎ አልፎ ኳስ ተቆጣጥሮ ለመጫወትና ወደ ተጋጣሚ የግብ ክልል ለመግባት የሚያደርጋቸው ሙከራዎች ከጥንካሬዎቹ ተጠቃሽ ነበሩ፡፡ ይሁንና ይህ ጠንካራ ጎኑ በጎል የታጀበ አለመሆኑ እምነት እንዳይጣልበት ምክንያት ሆኗል፡፡

ቡድኑ በዚያኑ ዕለት ተጉዞ ሌሶቶ የገባ ሲሆን፣ እሑድ ጳጉሜን 3 ቀን የመልሱን ጨዋታ አድርጓል፡፡ የቡድኑ ዋና አሠልጣኝ አብርሃም ስብስባቸው ኳስ ጋር በተገናኘ ከቀን ወደ ቀን ያሻሻላቸው ነገሮች ቢኖሩም አሁንም ግን ጎል ማስቆጠር አለመቻሉ በቀጣይ ሊሠሩበት የሚገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ አሠልጣኙ ከሆነ፣ ቡድኑ ከሌሶቶ ጋር ያደረገው እንቅስቃሴ ከሙሉ የጨዋታ ብልጫ ጋር ነበር፡፡ ይህንኑ ብልጫ በመልሱ ጨዋታ በመድገም ለማሸነፍ ጥረት እንደሚያደርጉ ከጨዋታው በኋላ በነበረው መግለጫ አስረግጠው የተናገሩበት አጋጣሚ ነበር፡፡ ይሁንና በዕለቱ የተደረገውን የጨዋታውን እንቅስቃሴ አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሚሰጡ ሙያተኞች፣ የኢትዮጵያ ቡድን በአጠቃላይ ይህ ነው የሚባል ጠንካራ ጎን እንዳልነበረው፣ ተጨዋቾቹ በአንድ ሁለት ቅብብል ብልጫ እንዲወስዱ ያደረጋቸው የተጋጣሚ ቡድን ተጨዋቾች ጨዋታውን ከሜዳቸው ውጪ የሚያከናውኑ እንደመሆኑ፣ ውጤት አስጠብቆ ለመውጣትና ትንፋሽ እየሰበሰቡ ባገኙት አጋጣሚ ለመጠቀም ከነበራቸው ፍላጎት እንደሆነና በዚህም ጎል የማስቆጠር አጋጣሚዎችን አግኝተው ሳይጠቀሙባቸው የቀሩት ዕድሎች በማሳያነት ይጠቅሳሉ፡፡

ኢንስትራክተር አብርሃም በመግለጫቸው ከተናገሯቸው መካከል፣ ተጨዋቾቻቸው ያገኟቸው የጎል አጋጣሚዎች አለመጠቀም እንደተጠበቀ፣ ሜዳ ላይ በነበራቸው እንቅስቃሴ ግን ደስተኛ ስለመሆናቸውና ስብስባቸው በተለይም በአጥቂዎቻቸው ላይ በሒደት ተከታታይነት ያለው ሥራ መሥራት እንዳለባቸው የተናገሩት ይጠቀሳል፡፡

ቡድኑ ለመልሱ ጨዋታ ወደ ሥፍራው ያመራው በዚያኑ ቀን መሆኑ እየታወቀ አሠልጣኙ በቀጣዩ ጨዋታ ክፍተቶቻቸው ላይ እንደሚሠሩ መናገራቸውን ተከትሎ አስተያየት ሰጪዎቹ፣ ‹‹ዋና አሠልጣኙ ዕርምት ለማድረግ ያቀዱት 2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ውጪ ለሚጠብቃቸው አኅጉራዊ ጨዋታዎች ከሆነ ትክክል ናቸው፤›› በማለት የአሠልጣኙን አስተያየት አይቀበሉትም፡፡

በዕለቱ ከሁለቱ ቡድኖች የሜዳ ላይ ቴክኒካዊና ታክቲካዊ ብቃት ይልቅ፣ ዋሊያዎቹን ለማበረታት ወደ ሜዳ የገባው የባህር ዳር ተመልካች፣ ኢትዮጵያውያንን ብቻ ሳይሆን የእንግዳውን ቡድን ትኩረት የሳበ እንደነበር ታይቷል፡፡ የሌሶቶ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ታቦ ሲኖንግ ከጨዋታው በኋላ በነበራቸው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ ‹‹ኢትዮጵያውያን ጥሩ ኳስ የሚጫወት ቡድን ይወዳሉ፡፡ ምናልባትም እናንተ (ተጨዋቾቻቸውን) ከኢትዮጵያውያኑ ተጨዋቾች የተሻለ እንቅስቃሴ የምታሳዩ ከሆናችሁ ድጋፋቸውን የሚሰጡት በእርግጠኝነት ለእናንተ ይሆናል፤›› በማለት ከጨዋታው በፊት ተመልካቹን በመመልከት ሥጋት ገብቷቸው ለነበሩት ተጨዋቾቻቸው እንደነገሯቸው ማስረዳታቸው ታውቋል፡፡

ለአኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች ተመሳሳይ መድረኮችን ያስተናገደው የባህር ዳር ስታዲየም አሁንም ሽንፈት አላስተናገደም፡፡ በአረንጓዴ፣ በቢጫና ቀዩ ሰንደቅ ያሸበረቀው የባህር ዳር ስታዲየም ከዋሊያዎቹ የጎል ድርቅ በስተቀር ስፖርታዊ ጨዋነት የተስተዋለበት እንደነበር የሌሶቶም ሆነ የኢትዮጵያ ቡድን አሠልጣኞች ተናግረዋል፡፡

ዋሊያዎቹ ከዓለም ዋንጫው ቅድመ ማጣሪያ በኋላ አፍሪካውያን በውስጥ ሊጎቻቸው የሚጫወቱ ተጨዋቾች ብቻ በሚሳተፉበት የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) የሩዋንዳ አቻው በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም እንደሚያስተናግድ ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አያሌ የውኃ “ጠርሙሶች”ን በጫንቃ

መሰንበቻውን በአይቮሪ ኮስት መዲና አቢጃን የምትኖር አንዲት ሴት፣ በሚደንቅ...

ወልቃይትን ማዕከል ያደረገው የምዕራባዊያን ጫና

በትግራይ ክልል የተከሰተው የዕርዳታ እህል ዘረፋ የዓለም አቀፍ ተቋማት...

ከቀጣዩ ዓመት በጀት ውስጥ 281 ቢሊዮን ብሩ የበጀት ጉደለት ነው ተባለ

ለቀጣዩ በጀት ዓመት ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር አጠቃላይ በጀት...