Friday, July 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበኢትዮጵያ ስፖርት ያልጠራው ‹‹የተጠሪነት ወሰን››

በኢትዮጵያ ስፖርት ያልጠራው ‹‹የተጠሪነት ወሰን››

ቀን:

በኢትዮጵያ ሕጋዊ ሰውነት አግኝተው በመንቀሳቀስ ላይ የሚገኙ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ጨምሮ ከ27 በላይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች እንዳሉ ይታመናል፡፡ ይሁንና መንግሥት ለእነዚህ ተቋማት በአስፈጻሚነት ለሚያዋቅራቸው አመራሮች ግልፅነትና ተጠያቂነት ያለበት የጠራ ‹‹የተጠሪነት ወሰን›› ማስቀመጥ ባለመቻሉ የስፖርቱ ዘርፍ ውጤታማ ከመሆን ይልቅ የውዝግብ አውድማ ከሆነ ውሎ አድሯል፣ እንደቀጠለም ነው፡፡

የኢትዮጵያ ስፖርት የመንግሥት ካቢኔ በተቀያየረ ቁጥር ግልፅ ባልሆነ የተጠሪነት ወሰን በተለያዩ ተቋማት ስር እንዲተዳደር መደረጉ፣ ይህም ለአገሪቱ ስፖርት ውድቀት ዓይነተኛ ሚና ሲጫወት መቆየቱ የሚያምኑ የዘርፉ ሙያተኞች አሉ፡፡ እያንዳንዱ ስፖርት ከምሥረታው አሁን እስከሚገኝበት ባለው ሒደት ውስጥ በተለይም መንግሥት በአስፈጻሚነት የሚያስቀምጣቸው ተቋማት ‹‹ከበላይ የመጣ ትዕዛዝ ነው›› በሚል ብሔራዊ ተቋማት በፖሊሲና በሕግ የተሰጣቸውን ኃላፊነት እንዳያከናውኑ ትልቅ ተግዳሮት በመሆኑ መንግሥት በሚኒስቴር፣ በስፖርት ኮሚሽን እንዲሁም በብሔራዊ ኦሊምፒክና በብሔራዊ ፌዴሬሽን ደረጃ የሚያዋቅራቸው ተቋማት የኃላፊነት ድርሻ ምን መምሰልና የት ድረስ ሊሆን እንደሚችል ትክክለኛ የሕግ ማዕቀፍና የተጠሪነት ወሰን ሊያስቀምጥ እንደሚገባ ሙያተኞቹ ያስረዳሉ፡፡

በቅርቡ በሞሮኮ ራባት ፍጻሜውን ባገኘው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች የተሳተፈው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ልዑክ በ6 የወርቅ፣ በ5 የብርና 12 የነሐስ በድምሩ 23 ሜዳሊያዎችን አስመዝግቦ መመለሱ ይታወሳል፡፡ ይሁንና መንግሥት ለልዑካን ቡድኑ ዕውቅና ይሰጥ ዘንድ እየተከናወነ ባለው ሒደት፣ ኮሚሽኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ ጋር ተነጋግሮና መክሮ ፕሮግራሙን ከማከናወን ይልቅ ሌሎችን ያገለለበት ሁኔታ  መኖሩ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የብሔራዊ ፌዴሬሽን ኃላፊዎች ቅሬታቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ መዋቅራዊ አደረጃጀቱን በተመለከተም የሌሎች አገሮችን ማለትም የደቡብ አፍሪካን፣ የናይጄሪያን፣ የኬንያን፣ የአሜሪካን፣ የጀርመንና የቻይናን እንዲሁም ሌሎችም አገሮች ተሞክሮ በመመልከት ማስተካከል እንደሚያስፈልግ ጭምር ይመክራሉ፡፡

እንደ ኃላፊዎቹ ከሆነ፣ ኮሚሽኑ እየሄደበት ያለው አካሄድ ለዘርፉ ሰላማዊ እንቅስቃሴም ሆነ ለስፖርቱ ዕድገት እንደማይበጅ፣ ከስፖርት ኮሚሽኑ ጀምሮ ስፖርቱን ለመምራት በተዋረድ የተዋቀሩ ሁሉም ተቋማት ያመኑበት፣ ሁሉም በተሰጠው ኃላፊነትና የተጠሪነት ወሰን ልክ ለዕውቅናው የድርሻውን እንዲወጣ ማድረግ ሲገባ አለመደረጉ ያሳዘናቸው ስለመሆኑ ጭምር ይናገራሉ፡፡

የኢትዮጵያ ስፖርት ከላይ ከመንግሥት ጀምሮ በተዋረድ እስከ ታችኛው  የማኅበረሰብ ክፍል ድረስ የጋራ ጥረትና ርብርብ እንደሚጠይቅ የሚናገሩት እነዚሁ ኃላፊዎች፣ ወቅቱ በመስከረም ወር በኳታር ዶሃ የሚከናወነውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮኛ ጨምሮ የ2020 ቶኪዮ ኦሊምፒክ ዝግጅት ከወዲሁ የሚጀመርበት እንደመሆኑ፣ ለስፖርቱ ዕድገትም ሆነ ለተቋማቱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ እንቅፋት መሆኑ የሚነገርለት ‹‹የተጠሪነት ወሰን›› መንግሥት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ሊያስቀምጥለት እንደሚገባ ደጋግመው ያሳስባሉ፡፡ ስፖርት ኮሚሽን ስለጉዳዩ የሚለውን ለማወቅ ያደረግነው ጥረት አልተሳካም፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...