Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትዓመታዊ የኮካ ኮላ እግር ኳስ ዋንጫ ማጠናቀቂያውን በባቱ አደረገ

ዓመታዊ የኮካ ኮላ እግር ኳስ ዋንጫ ማጠናቀቂያውን በባቱ አደረገ

ቀን:

አምስተኛው ዓመቱን የያዘው የኮካ ኮላ እግር ኳስ ጨዋታ የዘንድሮውን ማጠናቀቂያ ባቱ ከተማ ላይ አድርጓል፡፡ ሁሉንም ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በማሳተፍ ከ15 ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችን ሲያወዳድር ሰንብቷል፡፡

ኮካ ኮላ ድርጅት ከኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽንና ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የታዳጊ ውድድሩን ከግንቦት ወር ጀምሮ በሁለቱም ጾታ ሲያከናውን ቆይቷል፡፡

ለአራት ወራት በዘለቀው ውድድር ከ45,000 በላይ በወንድም በሴትም ዕድሜያቸው ከ15 ዓመት በታች ወጣቶችን ማሳተፉ ተገልጿል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ኮካ ኮላ ዓመታዊ ውድድር የታዳጊ ወጣቶችን በማሳተፍ፣ አቅማቸውን ለማጎልበትና መሠረታዊ የሆኑ የእግር ኳስ ክህሎትን እንዲያዳብሩ በር ከፋች ሻምፒዮና እንደሆነ ይነገርለታል፡፡

ውድድሩ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በሁለቱም ጾታ አቅማቸውን ማሳየት የቻሉ ወጣቶች ከስፖርት አካዴሚዎች እስከ ፕሪሚየር ሊግ ክለቦች በመዘዋወር ተተኪዎችን መሆን ችለዋል፡፡

የብሔራዊ ቡድን ውጤት ማጣት ተከትሎ አስተያየታቸውን የሚሰነዝሩት ባለሙያዎች ቀዳሚው ሙግታቸው የወጣቶች እግር ኳስ ውድድርን ማብዛት ላይ ነው፡፡

በአንፃሩ ክለቦችም ሆኑ የእግር ኳሱ የበላይ አስተዳዳሪ ለክፍተቶቹ መላ ሲያበጁ አይስተዋልም፡፡ የትምህርት ቤት ውድድሮች እየጠፉ በመጡበት በዚህ ወቅት  የሚከናወነውን የኮካ ኮላ ውድድር ማበረታታትና ተመሳሳይ ውድድሮችን ቁጥር መጨመር እንደሚያስፈልግ በየመድረኩ ተጠቁሟል፡፡

እሑድ ጳጉሜን 3 ቀን 2011 ዓ.ም. የተጠናቀቀው የኮካ ኮላ ውድድር ላይ ከወንዶች ምድብ አማራና ኦሮሚያ ለፍጻሜ የደረሱ ሲሆን በሴቶቹም ሁለቱ ክልሎች ለፍጻሜ ደርሰዋል፡፡

በወንዶች ኦሮሚያ አማራን 3ለ1 በመረታት እንዲሁም በሴቶች አማራ ኦሮሚያን 3ለ1 በመረታት የዋንጫና የገንዘብ ተሸላሚ ሆነዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...