Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽኑ የኳታሩን ብሔራዊ አትሌቲክስ ልዑክ ይፋ አደረገ

ፌዴሬሽኑ የኳታሩን ብሔራዊ አትሌቲክስ ልዑክ ይፋ አደረገ

ቀን:

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) ባለቤትነት፣ በተመረጡ ከተሞች ላለፉት ሦስት አሠርታት ሲያከናውነው የቆየው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመስከረም 16 እስከ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በኳታር ዶሃ ይደረጋል፡፡ ተሳታፊ አገሮች የልዑካናቸውን ዝርዝር ይፋ ማድረግ ጀምረዋል፡፡ በሩጫው ዘርፍ ከመካከለኛ ርቀት እስከ ማራቶን የምትሳተፈው ኢትዮጵያ ብሔራዊ አትሌቶቿን ይፋ አድርጋለች፡፡

ለወትሮ ኦሊምፒክን ጨምሮ የዓለም ሻምፒዮና ሲቃረብ በተለይ ከአትሌቶች ምርጫ ጋር ተያይዞ ሲደመጥ የነበረው ውዝግብና አለመግባባት እስካሁን ባለው ፌዴሬሽኑ አሠራር ቅሬታም ሆነ ተቃውሞ ያቀረበ አካል አልተደመጠም፡፡ ለዚህም ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከማራቶን እስከ 800 ሜትር በምርጫው የተካተቱ ሁሉም አትሌቶች በውድድር ዓመቱ ባስመዘገቡት ሰዓትና ወቅታዊ ብቃትን መሠረት ያደረገ መሆኑ፣ ከዚህ በፊት ይቀርብ የነበረው እሰጣ ገባ መቋጫ እንዲያገኝ ምክንያት ሆኗል የሚሉ አሉ፡፡

የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ፣ ከአትሌቶች ወቅታዊ ብቃትና ሰዓት ጋር በተገናኘ መምረጫ መስፈርቱ ከዚህ በፊት ከነበረው ዘንድሮ የተለየ እንዳልሆነ ሲገልፁ፣ ‹‹ከዚህ በፊት እንደነበረው ሁሉ ዘንድሮም ወቅታዊ ብቃትና ሰዓት ያላቸው አትሌቶች በሁለት የውድድር ዓይነት እንዲቀርቡ ተደርጓል፡፡ ይህ አሠራር እስካሁንም ነበር፣ ወደፊትም ይቀጥላል፤›› ብለው፣ ለዚህ አሁን ላይ ይፋ የሆነውን የብሔራዊ አትሌቶች ዝርዝር መመልከቱ በቂ ማሳያ ሊሆን እንደሚችል ያስረዳሉ፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በየውድድር ዓይነቱ ቁጥራቸው በርከት ያሉ አትሌቶችን በሆቴል በመያዝ ከሁለት ወር በላይ ዝግጅት ሲያደርግ መቆየቱን ያስረዱት የቴክኒክ ዳይሬክተሩ፣ በአሁኑ ወቅት ለሻምፒዮናው ብቁ ናቸው የተባሉት አትሌቶች፣ ከዚህ በፊት በዓለም አቀፍ ውድድሮች ላይ ያስመዘገቧቸው ሰዓቶችና ወቅታዊ ብቃታቸው ታይቶ የብሔራዊ አትሌቶች ምርጫና ዝርዝር እንዲገለፅ ተደርጓል፡፡

በምርጫው መሠረት ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረኮች ከፍተኛ ውጤት በማስመዝገብ በምትታወቅበት ረዥም ርቀት ማለትም 10,000 ሜትር ወንዶች ሐጎስ ገብረሕይወት፣ ዮሚፍ ቀጀልቻ (በአሜሪካ ናይኪ አካዴሚ ዝግጅት ሲያደርግ የቆየ)፣ አንዱአምላክ በልሁና ሰለሞን ባረጋ የሚወዳደሩ ሲሆኑ፣ በሴቶች አልማዝ አያና ቀጥታ ተጋባዥ (16ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና አሸናፊ)፣ ለተሰንበት ግደይ፣ ነጻነት ጉደታ፣ ሰንበሬ ተፈሪና ፀሐይ ገመቹ ተመራጭ ሆነዋል፡፡

የ5,000 ሜትር ወንዶች ተመራጮች ሙክታር እድሪስ ቀጥታ ተጋባዥ (16ኛው አትሌቲክስ ሻምፒዮና አሸናፊ)፣ ጥላሁን ኃይሌ፣ ሰለሞን ባረጋ (በወቅታዊ ብቃትና ሰዓት)፣ ሐጎስ ገብረሕይወት (በወቅታዊ ብቃትና ሰዓት)፣ አባዲ ሐዲስ ሲሆኑ፣ በሴቶች ለተሰንበት ግደይ (በወቅታዊ ብቃትና ሰዓት)፣ ሐዊ ፈይሳ፣ ፋንቱ ወርቁና ፀሐይ ገመቹ (በወቅታዊ ብቃትና ሰዓት) መሆናቸው ታውቋል፡፡

3000 ሜትር መሰናክል ሴቶች መቅደስ አበበ፣ ሎሚ ተፈራ፣ ዘርፌ ወንድማገኝ እና አገሬ በላቸው ሲሆኑ፣ በወንዶች ጌትነት ዋለ ቀጥታ ተጋባዥ (ዳይመንድ ሊግ አሸናፊ)፣ ጫላ ባዩ፣ ለሜሳ ግርማና ታከለ ንጋቱ ሆነዋል፡፡

1,500 ሜትር ወንዶች ለሻምፒዮናው ሰዓት (ሚኒማ) ያላቸው ሳሙኤል ተፈራ እና ታደሰ ለሚ ተመረጡ በሴቶች ገንዘቤ ዲባባ፣ ጉደፋይ ፀጋዬ፣ አክሱማዊት አምባዬ እና ለምለም ኃይሉ ተወዳዳሪ ናቸው፡፡ 800 ሜትር ሴቶች ጉደፋይ ፀጋዬ እና ድርቤ ወልተጂ ሲያዙ፣ በወንዶች ሚኒማ ያላቸው አትሌቶች ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት በምርጫው የተካተተ አትሌት አልተገለጸም፡፡

በማራቶን ወንዶች ሌሊሳ ፈይሳ 2፡ 07፣ 50 (ቦስተን ማራቶን)፣ ሙስነት ገረመው 2፡ 02፣ 55 (ዱባይ ማራቶን)፣ ሙሌ ዋሲሁን 2፡ 03፣ 16 (ለንደን ማራቶን)፣ ሹሬ ቂጣታ 2፡ 05፣ 01 (ለንደን ማራቶን) ባስመዘገቡት ውጤት መሠረት ሲመረጡ በሴቶች ሮዛ ደረጀ 2፡ 20፣ 51 ለንደን ማራቶን፣ ሩቲ አጋ 2፡ 20፣ 40 (ቶኪዮ ማራቶን)፣ ሹሬ ደምሴ 2፡ 20፣ 05 (ቶኪዮ ማራቶን) ተመርጠዋል፡፡ ምርጫውና ሰዓቱ አትሌቶቹ የተወዳደሩባቸው ከተሞች ዓይነትና ሁኔታን ግምት ውስጥ ያስገባ መሆኑም ተነግሯል፡፡ 20 ኪሎ ሜትር ዕርምጃ በሴቶች የኋልዬ በለጠው በብቸኝነት ስትሳተፍ፣ በወንዶች ግን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት አልተገለጸም፡፡ አሠልጣኞችና ሌሎች የልዑካን አባላትን በተመለከተ ሻምፒዮናው ሲቃረብ እንደሚገለጽ ነው አቶ ዱቤ ያብራሩት፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...