Wednesday, September 27, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ፍሬከናፍር‹‹ከእናንተና ከታላቋ አገራችሁ ፊት ያሉት ዕድሎች ወሰን አልባ ናቸው››

‹‹ከእናንተና ከታላቋ አገራችሁ ፊት ያሉት ዕድሎች ወሰን አልባ ናቸው››

ቀን:

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ሬይነር ለአዲሱ ዓመት መልካም ምኞታቸውን ለማስተላለፍ ካወጡት መግለጫ የተወሰደ፡፡ በመላው ዓለም አዲስ ዓመት ሲጀመር መልካም ምኞትን መግለጽ የተለመደ መሆኑን ገልጸው፣ ያለፈውን ዓመት በመገምገም አዲሱ ምን ይዞ ይመጣ ይሆን ይባላል ብለዋል፡፡ ኢትዮጵያዊያንም የአገራቸውን ጉዳይ በዚህ መንገድ እንደሚያዩ ጠቁመው፣ በጣም ብዙ ኢትዮጵያዊያን በአገራቸው እየተካሄደ ያለውን ለውጥ በመደገፍ መጪውን ጊዜ ብሩህ ለማድረግ ሲጥሩ ማየት ደስ የሚያሰኝ ነው ብለዋል፡፡ ለታሪካዊው ለውጥ ጥረት ዋናው ጉዳይ መሆኑንና ክልል፣ ብሔር ወይም እምነት ሳይገድባቸው መጪውን ጊዜ ብሩህ ማድረግ ለራስ፣ ለማኅበረሰብና ለአገር ኢኮኖሚ ዕድገት የፖለቲካ አካታችነትና መረጋጋት ቁልፍ መሆኑን ብዙዎች እንደሚነግሯቸው ገልጸዋል፡፡ ፈተናዎች ቢበዙምና የሚከናወኑ በርካታ ቀሪ ሥራዎች ቢኖሩም፣ ከኢትዮጵያና ከኢትዮጵያውያን ፊት ያሉ ዕድሎች ወሰን አልባ ናቸው ብለዋል፡፡ ዕድሎቹንም ለመጠቀም ኢትዮጵያዊያን ዝግጁ ለመሆናቸው ተስፋ አደርጋለሁ በማለት፣ የመልካም ምኞት መግለጫቸውን ‹‹መልካም አዲስ ዓመት›› ሲሉ አጠናቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአማራ ክልል ወቅታዊ ሁኔታ

እሑድ ጠዋት መስከረም 13 ቀን 2016 ዓ.ም. የፋኖ ታጣቂዎች...

ብሔራዊ ባንክ ለተመረጡ አልሚዎች የውጭ አካውንት እንዲከፍቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የፈቀደበት መመርያና ዝርዝሮቹ

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የውጭ ምንዛሪ አጠቃቀምንና ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮችን...

እነ ሰበብ ደርዳሪዎች!

ከሜክሲኮ ወደ ዓለም ባንክ ልንጓዝ ነው። ሾፌርና ወያላ ጎማ...