የሚያስፈልጉ ጥሬ ነገሮች
- 1 ዶሮ
- 1 ሎሚ
- የወይራ ዘይት (ሌላ የዘይት ዓይነት መጠቀም ይቻላል)
- ¾ ማንኪያ ጨው
- 1/8 የተፈጨ ቃሪያ
- ከ1 1/2 ማንኪያ ከሙን
- ½ ማንኪያ ቀረፋ
- ¼ ማንኪያ የተፈጨ ዝንጅብል
- ½ ኩባያ ውኃ
አዘገጃጀት
- የታረደውን ዶሮ ከሆዱ ውስጥ ያለውን ቆሻሻ እስኪጸዳ ሎሚ እየጨመሩ ማጠብ፤ ከላይ የተዘረዘሩትን ቅመሞች በዘይቱ አዋህዶ በዶሮዋ የውስጠኛ ክፍል መጨመርና የውጩንም ክፍል በደንብ መቀባት፣
- ለግማሽ ሰዓት ያህል ውስጥ ማስቀመጥ፤
- በመጨረሻም 180 ዲግሪ ሴንቲ ግሬድ በሆነ የኦቭን ሙቀት በቅመም የታሸችውን ዶሮ ለ2 ሰዓት ያህል ማብሰል፣
- የበሰለውን አሮስቶ እንደአስፈላጊነቱ ቆራርጦ ከማባያ አዋዜ ጋር ማቅረብ፡፡