Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትመቐለ የመጀመርያዋን አኅጉራዊ ውድድር ታስተናግዳለች

መቐለ የመጀመርያዋን አኅጉራዊ ውድድር ታስተናግዳለች

ቀን:

በኢትዮጵያ ክልል ከተሞች ከተገነቡና ከፍተኛ የተመልካች ቁጥር ማስተናገድ ከሚችሉ እንዲሁም ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ስታድየሞች ተብለው ከሚጠቀሱት አንዱ የመቐለው ስታድየም ነው፡፡ ይህ ስታዲየም እሑድ፣ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ኢትዮጵያና ሩዋንዳ ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የሚያደርጉትን የመጀመርያውን አኅጉራዊ ውድድር ያስተናግዳል፡፡

አፍሪካውያን በውስጥ ሊጎቻቸው የሚጫወቱ ተጨዋቾች ብቻ በሚያሳትፉበት የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) በመጪው ዓመት በካሜሩን አስተናጋጅነት ይካሄዳል፡፡ በቅድመ ማጣሪያው ጂቡቲን በጠባብ ውጤት አሸንፋ በሁለተኛው ዙር ማጣሪያ ሩዋንዳን የምትገጥመው ኢትዮጵያ፣ ለመቐለ ከተማና ነዋሪዎቿ የመጀመርያ በሆነው ዓለም አቀፍ ውድድር ጨዋታው እንደሚስተናገድ መታወቁ፣ ፉክክሩን ከወዲሁ ልዩ እንደሚያደርገው ይጠበቃል፡፡

በኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የሚሠለጥነው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለውድድሩ 24 ተጨዋቾችን በመምረት መቐለ ከተማ የገባው መስከረም 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ሲሆን፣ ተጋጣሚው የሩዋንዳ ቡድንም መስከረም 8 ቀን 2012 ዓ.ም. አዲስ አበባ ገብቶ እሑድ መስከረም 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ጨዋታውን በመቐለ ስታድየም እንደሚያካሂድ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

አሠልጣኙ ለሩዋንዳው ጨዋታ በስዊድን ሁለተኛ ሊግ የሚጫወተውን ቢኒያም በላይና በግብፅ ሊግ የሚጫወቱትን ሽመልስ በቀለ፣ ጋቶች ፓኖምና ኡመድ ኡኩሪን በማስቀረት ለሩዋንዳው ግጥሚያ ያካተቷቸው ተጨዋቾች በአብዛኛው ለኳታሩ የዓለም ዋንጫ ከሌሶቶ ጋር በነበራቸው የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ የተመረጡት ሲሆኑ፣ ለቡድኑ ቅንጅትም ጠቃሚ እንደሆነ እየተገለጸ ነው፡፡

የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ የሚደረግበት የመቐለ ስታድየም፣አኅጉራዊ ውድድሮቸችን ሲያስተናግድ የሩዋንዳው ቡድን የመጀመርያው ቢሆንም፣ የመቐለና አካባቢዋ ነዋሪዎች ለስታድየሙ ድምቀት ከመሆንም ባሻገር፣ ለኢትዮጵያ ቡድን ሥነ ልቦና የሚሰጡት ድጋፍ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል፡፡ ጨዋታውን ሱዳን በኮሚሽነርነት፣ ኬንያ በዋና ዳኝነት ይመሩታል፡፡

የአዲስ አበባ ስታድየምን ጨምሮ በመቐለና በሌሎችም ክልሎች የተገነቡትና በመገንባት ላይ የሚገኙት ስታድየሞች፣ የዓለም አቀፉ እግር ኳስ ማኅበር (ፊፋ) ያወጣውን ዝቅተኛ መሥፈርት አያሟሉም ተብለው አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች እንዳያስተናግዱ ዕግድ ወጥቶባቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ሆኖም የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌደሬሽን (ካፍ) እና ፊፋ የመቐለና የባሕር ዳር ስታድየሞች ከሌሎቹ አንፃር የተሻለ ይዘት ስላላቸው፣ የተጓደሉ ግንባታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ እንዲሟሉ ቀነ ገደብ በማስቀመጥ ባሕር ዳር ስታዲየም የሌሶቶን፣ መቐለ ደግሞ የሩዋንዳን ጨዋታ እንዲያስተናግዱ ፈቃድ መስጠቱ ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...