Monday, July 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናባለፈው ዓመት በክልሎች በተፈጠሩ ግጭቶች 1,200 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

ባለፈው ዓመት በክልሎች በተፈጠሩ ግጭቶች 1,200 በላይ ሰዎች መሞታቸው ተገለጸ

ቀን:

በ2011 ዓ.ም. በሁሉም ክልሎች በተፈጠሩ ሁከቶች ሳቢያ በደረሱ ግጭቶች የ1,229 ሰዎች ሕይወት ማለፉንና ከ2.2 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን፣ የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ አስታወቀ፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የተደራጁ ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎች ዳይሬክተር አቶ ፍቃዱ ፀጋ እንደገለጹት፣ ሕይወታቸው ካለፈ 1,229 ሰዎች በተጨማሪ 1,393 ሰዎች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡ በ19 ሰዎች ላይ ደግሞ የግድያ ሙከራ ተደርጎባቸዋል፡፡ ከንብረት ጋር በተያያዘ ግምቱ 2.29 ቢሊዮን ብር የሆነ ንብረት ለውድመት መዳረጉን፣ 1,200,437 ዜጎች ከመኖሪያ ቀዬአቸውና አካባቢያቸው መፈናቀላቸውን ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

በወንጀል ድርጊቱ ተሳትፈዋል በተባሉ 1,323 ተጠርጣሪዎች ላይ ክስ የተመሠረተ ቢሆንም፣ በቁጥጥር ሥር ውለው ጉዳያቸውን በፍርድ ቤት እየተከታተሉ የሚገኙ 645 ብቻ መሆናቸውንም አቶ ፍቃዱ ጠቁመዋል፡፡ ከተያዙት ውስጥ አሥር ተጠርጣሪዎች በምሕረት መፈታታቸውንም አክለዋል፡፡

በአማራ ክልል መከተል ዞን ጃዊ ወረዳ፣ በጎንደር አካባቢ፣ በሰሜን ሸዋ አስተዳደር፣ በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በካማሺ ዞን የተለያዩ ወረዳዎችና ቀበሌዎች፣ እንዲሁም በኦሮሚያ ክልል በምሥራቅና በምዕራብ ወለጋ ዞኖች፣ በተለያዩ ቀበሌዎችና በበርታ ብሔረሰብ መካከል በተፈጠረ ሁከትና ግጭት በአጠቃላይ 1,647 መጠርጠራቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከተጠርጣሪዎቹ ውስጥ 185 ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውንም አቶ ፍቃዱ ገልጸዋል፡፡ ተጨማሪ 1,462 ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑን ጠቁመው፣ ኅብረተሰቡ አሳልፎ በመስጠት ትብብር እንዲያደርግ ጥሪ ቀርቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...