Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ በፊት ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ እንዲፈጠር...

የሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ከሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ በፊት ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ እንዲፈጠር አሳሰበ

ቀን:

በኅዳር ወር 2012 ዓ.ም. ይካሄዳል ተብሎ ከታቀደው የደቡብ ክልል የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ አስቀድሞ አስተዳደራዊና ሕጋዊ ማዕቀፎች በማዘጋጀት፣ እንዲሁም ተዓማኒ በሆነ የጊዜ ሰሌዳ ላይ አስቀድሞ መግባባት ላይ በመድረስ ሕዝበ ውሳኔውን ለማካሄድ የሚያስችል ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ ለመፍጠር አፋጣኝ ዕርምጃ መውሰድ እንደሚያስፈልግ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ዳንኤል በቀለ (ዶ/ር) አሳሰቡ፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ ይህን ማሳሰቢያ የሰጡት ከመስከረም 7 እስከ 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ ያደረጉትን የሥራ ጉብኝት አስመልክቶ በሰጡት ማብራሪያ ወቅት ነው፡፡

በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም. ከሲዳማ ዞን የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በተነሳው ግጭት ምክንያት በፖሊስ ቁጥጥር ሥር የሚገኙ ዜጎችን የጎበኙት ዋና ኮሚሽነሩ ከጉብኝቱ በኋላ፣ ‹‹ለችግሩ መነሻ የሆነው ዋነኛ ምክንያት በሲዳማ ዞን ምክር ቤት ለቀረበው የክልልነት ጥያቄ በሚመለከታቸው አካላት ሲሰጥ የነበረው ምላሽ ወቅታዊና ሥልታዊ አለመሆን፣ በሌላ በኩል ጥያቄውን በተናጠል ውሳኔና በኃይል ጭምር ለማስፈጸም የፈለጉ ቡድኖች ባራመዱት አስተሳሰብ የተነሳ የተፈጠረ የፖለቲካ ውጥረትና ቀውስ በመሆኑ ነው፤›› በማለት፣ አሁንም ከመጪው ኅዳር ሕዝበ ውሳኔ አስቀድሞ ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ መፍጠሩ አስፈላጊ መሆኑን አበክረው አሳስበዋል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ በሐዋሳ ከተማ የተገኙት በአገሪቱ ውስጥ እየተካሄደ የሚገኘውን አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍና ራዕይ ምክንያት፣ በኮሚሽኑ ውስጥም ስለሚደረገው የለውጥ መርሐ ግብር ከባለድርሻ አካላት ጋር ምክክር ለማድረግ መሆኑን ኮሚሽኑ ለሪፖርተር በላከው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በቆይታቸውም በሐዋሳ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ድንገተኛ ጉብኝት ማድረጋቸው የተገለጸ ሲሆን፣ በዚሁ ጉብኝታቸው ወቅትም በሐምሌ ወር ተከስቶ በነበረው ግጭት ምክንያት በቁጥጥር ሥር የሚገኙ እስረኞችንና የአያያዛቸውን ሁኔታ ከመጎብኘታቸው ባለፈ ከክልሉ ርዕሰ መስተዳደር፣ ከክልሉ ምክር ቤቶች አፈ ጉባዔዎች፣ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ከመገናኛ ብዙኃንም ጋር ተገናኝተው በሰብዓዊ መብቶች ላይ ውይይት ማድረጋቸው ተገልጿል፡፡

በሐምሌው ግጭት ተጎጂ ከነበሩ ቤተሰቦች ጋርም ውይይት ያደረጉት ዋና ኮሚሽነሩ፣ ‹‹በግጭቱ የተጎዱ ሰዎችንና ቤተሰቦችን በተገቢ መጠን ከመርዳትና መልሶ ከማቋቋም በተጨማሪ፣ የምርመራው በፍጥነት መጠናቀቅ አፋጣኝ ትኩረት ይሻል፤›› በማለት፣ ምርመራው በፍጥነት መጠናቀቅ እንደሚኖርበት አሳስበዋል፡፡

‹‹ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽንና ከሌሎች ምንጮች በተገኘው መረጃ መሠረት እስካሁን በተደረገው የፖሊስ ምርመራ በሦስት ማዕከላት በእስር ይገኙ ከነበሩ ወደ 1,500 ገደማ እስረኞች ውስጥ ከግማሽ በላይ መለቀቃቸውን ተረድተናል፤›› በማለት ኮሚሽኑ በመግለጫው አስታውቋል፡፡

‹‹ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ በጋራ እያካሄዱ ባሉት የምርመራ ሥራ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከእስር እንዲለቀቁ ማስቻሉ ጥሩ ዕርምጃ ነው፤›› በማለት ኮሚሽኑ አስታውቆ፣ ነገር ግን ለችግሩ መነሻ ለሆኑ ጉዳዮች በቅጡ መፍትሔ መስጠት አስፈላጊ መሆኑንም ጠቁሟል፡፡

ዋና ኮሚሽነሩ ኮሚሽኑን በአዲስ መልክ በማደራጀትና በማጠናከር ነፃ የሰብዓዊ መብት ተቋም አድርጎ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት፣ ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በየደረጃውና በየክልሉ የሚደረገው ምክክር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አስታውቀዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...