Sunday, July 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ልናገርበአወዛጋቢ መረጃዎች የተሞላው የአንዳርጋቸው ጽጌ መጽሐፍ ያሳደረብኝ ቁጣ

በአወዛጋቢ መረጃዎች የተሞላው የአንዳርጋቸው ጽጌ መጽሐፍ ያሳደረብኝ ቁጣ

ቀን:

ዘሪሁን ተክሌ

የአንዳርጋቸው ጽጌን “ትውልድ አይደናገር፣ እኛም እንናገር” የተሰኘ መጽሐፍ ምርቃት አስመልክቶ ብዙ ስልኮች ከብዙ አቅጣጫዎች ሰሞኑን ተደወሉልኝ። ‹‹አነበብከው ወይ?››፣ ‹‹ቃለ መጠይቁን ሰማኸው ወይ?›› የሚሉ ጥያቄዎች ከወዳጅ ዘመዶቼ ተከታተሉ። መጽሐፉ በእጄ እስከሚገባ ድረስ አንዳርጋቸው ጽጌ ከአርትስ ቲቪ ጋር ያደረገውን ቃለ መጠይቅ በትዕግሥት አዳመጥኩ። መጽሐፉ እንደ ደረሰኝም ጊዜዬን ወስጄ በጥሞና አበብኩት። ‹‹ጉድ ሳይሰማ መስከረም አይጠባም›› እንደሚባለው ሆኖብኝ ተወጣሁት ብል ይሻላል።

 ከቃለ መጠይቁ ይዘት ጀምሮ የተማኝ ስሜት በጣም የተደበላለቀ ነው። የቁጣ፣ የንዴት፣ ከልብ የሚያሳዝንና የሚያስተዛዘብም ጽፍ ሆኖ ነው ያገኘሁት። አንድ ሰው ምን ሁኔታና ምን ዓይነት ልቦና ቢኖረው ነው እንደዚህ ያለን የውሸት ጥርቃሞ የሚደረድረው? ራሱንና የኔ የሚላችውን ሁሉ ከፍጥረቱ ጀምሮ እስከ ሽምግልና ድሜው የሌለ ታሪክ ጠፍጥፎ ያልሆኑትን ሆኑ ብሎ የሚተርከው? ሆን ብሎ የሌላውን ሰው ስም ለማጠልሸትስ ያን ያህል የሚጥረው? የእሳቤ መንገዱና የሚያገኘው ትርፍ ምን ቢሆን ነው?  የትስ ለመድረስ ነው? የተያያዘው የመመፃደቅ፣ የድፍረት፣ የንቀት፣ የውሸት፣ የውለታ ቢስነት፣ የእዘኑልኝ ተረት ተረት ማላዘን ምን ውጤት ለማግኘት ነው? ከሁሉም በላይ ደግሞ፣ መጽሐፉን ለሚያነበውና ቃለ መጠይቁን ለሚሰማው ኅብረተሰብስ ያለው ግምትስ ምን ያህል ዝቅተኛ ቢሆን ነው?

እስሁን ከሰማሁትና ካነበብኩት የምገነዘበው የትርክቶቹን ባዶነትና ጥራዝ ነጠቅነት ብቻ አይደለም፡፡ዕወቁኝአድንቁኝአሞግሱኝ አዙሪት ውስጥ ተነክሮ ድሜ ልኩን የሚዳክር ግለሰብ እንደሆነም ጭምር ነው። ከዚህ አዙሪት ውስጥ ለመውጣት በየጊዜው በሚያደርገው ትንቅንቅ ስንት የሰው ዳ (ቪክቲም) ያስፈልገው ይሆን? እንደገለው ከሆነ፣ የመጽሐፉ ላማ ለተከታዩ ትውልድ  የገሪቱ የታሪክ ጸሐፊ ምሁራን ያዛቡትን ለማቃናት፣ ታሪክን  በትክክል ለመተረክና እውነተኛውን የኢትዮጵያ ሕዝብ ታሪክ ለማሳወቅ ታስቦ ነው። አንዳርጋቸው ጽጌ  ለዚህ ላማው የገሪቱን የታሪክ ምሁራን በመኮነን ይጀምራል። ቀጥሎም፣ የታወቁና የተከበሩ አዛውንት ምሁራን የይወት ታሪካቸውን ከገሪቱ የታሪክ ደት ጋራ በማጣመር የጻፉትን ትረካ በመከለስና እንደፈለገው በመተርጎም በምንም መረጃ ላይ ያልተደገፈ አዲስ የኢትዮጵያ ታሪክ ያቀርባል።

መጽሐፉን ከዳር እስከ ዳር ለማንበብ የበረቱ የታሪክ ባለሙያዎች አስተያየታቸውንና ከዚህ መጽሐፍ የሚያገኙትን “ቁም ነገር” እንደሚያካፍሉን ኑ ተስፋ አለኝ። እስከ ዛሬ የወጡትን አንዳንድ ትችቶች/አስተያየቶች ሳነብ፣ ስለመጽሐፉ ያለኝን አሉታዊ አስተያየት የሚያጠነክሩ ሆነው አግኝቻቸዋለሁ።  የኔ ፈንታ፣ ስሜን እየጠራና እኔን በቀጥታ በተመለከተ በተረካቸው ዋና ዋና አንኳር አንኳር ውሸቶች/የተዛቡ ትረካዎች ላይ አተኩሮ ዕውነቱን ማሳወቅ ነው።

1. የአውሮፓ የኢትዮጵያ ተማሪዎች ማኅበርን ጽሑፎችና መጽሔቶች ከአውሮፓ በየጊዜው ለወንድሞቼና ለሱ በመላክ ንቃተ ሊናውን ከፍ በማድረግ አስተዋኦ እንዳደረግሁለት ይጽፋል (ገጽ 303)። ቢሆን ደስ ባለኝ ነበር። ነገር ግን ዓይን ያወጣ ውሸት ነው። በዚያን ጊዜ (እ.ኤ.አ. 1965/1966) እንኳን በፖስታ በሰውም በገሪቱ የተከለከለ ጽሑፍ መላክ አደገኛ መሆኑን በሚገባ ስለማውቅ ለወንድሞቼም ሆነ ለእርሱ መጽሐፍ ልኬ አላውቅም፣ የዚህ ዓይነቱ የጀብደኝነት ባህም የለኝም። እንኳን መጽሐፍ መላክ በደብዳቤ ከቤተሰብ ጋር ያለግንኙነት በጣም ውን ነበር።  በዚህ ብቻ አላበቃም ውሸቱ፣ የአንድ ወዳጄን ስም በመጥቀስ በእርሱ በኩል “ማርክሲስታዊ” መጽሐፎች እንደላኩለት ይናገራል።

ይህ ወዳጄ ከእኔ ሁለት ወይም ስት ዓመታት አስቀድሞ ወደ ገር ተመልሶ በትልቅ ላፊነት ቦታዎች ገሩን ያገለግል ነበር። አሁን በይወት የለም፣ ከኢአፓ  የመጀመርያ ሰለባዎች አንዱ ነበር። ስሙን ከእነ አያቱ ስምና ማረግ መጥቀስና የተገደለበትንም ሁኔታ መዘርዘር ያስፈለገው ለምንድነው? በገጽ 470ም ላይ እንደዚሁ ወደ ሌላው ወዳጄ ዘንድ ያውም “የፖለቲካ ትምህርት” እንዲሰጠው እንደላኩት ይጽፋል። ሁሉ ፈጽሞ ውሸት ነው። በኢሕአፓ አመራር ውስጥ የነበሩትን ሁሉንም በፌርነት በማገልገሌ ከ አስተሳባቸው አውቃቸው ነበር ብሎ እንደሚተርከው ሁሉ ሌሎቹንም ቢሆን በተለይ “አመራር” ቦታ ላይ የነበሩትን ሁሉ “አውቃለሁ” የሚል አባዜ ስለተጠናወተው ይሆን?   በመጽፉ ትረካ ላይ የሚንባረቀው ይ“ከኔ በላይ ማን አውቆ” የማለት ግብዝነት ይመስለኛል።

2. አንዳርጋቸው ጽጌ በኢሕአፓ ውስጥ በወቅቱ የተከሰተውን መከፋፈል (የክሊክና አንጃ) አቃቂ የመገዳደል ሁኔታ በመዘርዘር (እዚያን ቀን አሱ የሚያውቀውን መኪና በመጠቀም ጓደኛውን ፊቱ ላይ ገድለው መሄዳቸውንና የሚቀጥለው ተረኛ ግሞ እሱ እንደሆነ ነገረኝ)ይወቱ ከፍተኛ አደጋ ላይ እንደወደቀ፣ በድንጋጤና በፍርት ስሜት ሲገልጽልኝይወቱን ለማዳን ለአንዲት ሰኮንድ እንኳን አላመነታሁም ነበር። አብሮኝ የሚኖረውን ጓደኛዬን ወዲያውኑ አማክሬ፣ ለተወሰነ ጊዜ እቤታችን በመኖር ዘወር ማለት እንዲችል አደረግሁ። ወቅቱ ሁላችንም ከፍተኛ አደጋ ላይ የነበርንበትና ማን እንደገደለው እንኳን ሳይታወቅ ብዙ ሰው በየቀኑ፣ በየመንገዱ የሚገደልበት ጊዜ ነበር። እሱን በማስጠለል ሊደርስብን የሚችለውን አደጋ እኔና ጓደኛዬ በደንብ ብናውቅም ዋናው ላማችን “አለብኝ” ካለው የሞት አደጋ  የእሱን ይወት ማትረፍ  ብቻ ነበር። 

አንዳርጋቸው ጽጌ  ይህን ሰብዊ ድርጊት በመጽሐፉ ውስጥ (ገጽ 655/656) በሚያሳፍርና የብዕና ዝቅጠቱን በሚያመለክት ሁኔታ ገልታል። የተደረገለትን ሰብዓዊ ትብብር በሱ ብልጥነትና በእኛ የዋህነት የተፈመ አድርጎ ከመውዱም በላይ እኛ ሥራ በምንሄድበት ጊዜ በየክፍላችን እየዞረ መሳቢያችንን አንድ በአንድ እንደሚበረብር ያለ ፍረት ይተርካል። ወራዳ ድርጊቱን ለመደገፍ “ወቅቱ እንዲህ ነበር” ብሎ ያልፈዋል። እንደዚህ ዓይነቱን አሳፋሪና ወራዳ ተግባር በድል አድራጊነት  ሲተርክ  ደግሞ የመኢሶን ልሳን የነበረውን “የሰፊው ሕዝብ ድምፅ” ስቴንሲል እንዳገኘ ያትታል። ቀጥሎም እሱ ከስቴንስል ላይ አንብቦ የጨረሰውን ጽ እኔ ከሁለት ቀን በኋላ የወረቀት ላይ ትሙን ንዲያነበው እንደምሰጠው ይናገራል።

በስቴንሲልም በወረቀትም ስላነበበው ጽሑፍ ይዘት፣ ጥቅምና ጉዳት ግን ትንፍሽ አይልም። ሊያሳውቅ የሚፈልገው ሊደርስብን የሚችለውን አደጋ ተቀብለን ያስለልነውን ሰዎች ቤት በመበርበር በፈጸመው ጀብድ የቱን ያህል ምጡቅ የህቡዕ ታጋይ እንደሆነ ነው። ከዚህ “ከፍታ” ለመድረስ በመቸኮሉም ነው ቀደም ሲል ንቃተ ሊናው ዳበረው እኔ በምልክለት ጽሑፎችና መጽሐፍት ጭምር ነበር በማለት የዋሸውን የረሳውና አሁን ደግሞ የቤቴ በርባሪ ኖ ያረፈው። ራሱ እንደሚለው እኔው በወረቀት ለመስጠት ያልደበቅኩትን ጋዜጣ፣ “የሰፊው ሕዝብ ድምፅ” አስቀድሜ ቤቱን በርብሬ አንብቤው ነበር ብሎ በጀግንነት የሚተርከው። ያስጠጋን ሰው ቤት መበርብር የሚያኮራ ድርጊት መሆኑ ነው? ሞት አደጋ ላይ እንደወደቀ አስተዛዝኖ የነገረኝ፣ ከቤቴ ገብቶ ሊበረብረኝ ኑሯል? ለትውልድ አስተላልፋለሁ የሚለው ቁም ነገር ምኑ ላይ ይሆን?

ከሁሉም የደነቀኝ ደረቅ ውሸትእሱም ሆነ ሌላው ወንድሙ ከዓመታት በኋላ ፈረንይም ሆነ ኢትዮጵያ በተገናኘንባቸው ጊዜያአሁን በየዲያው እንደሚገልጸው ሁኔታዎችን አንስተን በቀጥታ የተነጋገርንበት ጊዜ የለም። ነገር  ግን ድርጅቱ “ባዘዘን መሠረት” በሚሉት “ተልዕኮዎቻቸው” ላይ የፈሙትን የወንጀል ርጊቶችና ጅብዱዎች “ቴአትራዊ” በሆነ መልክ ይተረኩና ይሳለቁ እንደነበር አስታውሳለሁ። ከጓደኞቻችንም ሰማን እያሉ እንደ “ጀብድ” የሚያወሩትንም የውንብድና ድርጊቶች ሳስታውስና አሁን ደግሞ በመጽሐፉ ላይ የሚያትታቸውን እውነትና ቅንነት የሚጎላቸው ኑዛዜዎች ሳነብ ታላቅ ሕመም ይማኛል። 

3. በመጽሐፉ ገጽ 568/569 ላይ፣ የኢሕአፓ ገዳይ ስኳድ እኔን ሊገድል ሲል፣ ከሱ ጋር በመታየቴ ይወቴ እንደተረፈ ያትትና ይህ በመሆኑ “ዛሬ ከፀፀት ድኛለሁ” ይላል።  በመቀጠልም በገ 656 ከኢሕአፓ ጋር የነበረውን ግንኙነት በመቋረጡ ነው እንጂ እኔንና ጓደኞቼን በሙሉ ላስጨርሳቸው እችል ነበር ይላል። አንድ ጊዜ የገዳይ ስኳድ፣ በሌላ ጊዜ አዛዥ፣ ቆየት ብሎ ደግሞ ከበላይ ትዛዝ ውሳኔ ተቀባይና አስፈጻሚ፣ በአብዛኛው ደግሞ ደጋግሞ ድርጅቱ የበላይ አካላት ሾፌር እንደነበር በመግለጽ ይዋትታል።  

አንዴ የቤታችን በርባሪ፣ በኔና በአጋጣሚ አብረውኝ ባያቸው ወይም በእሱ አስተሳሰብ ሊያውቃቸው ይችላል ብሎ የገመታቸውን ዎች ላይ ሁሉ የሞት ፍርድ ፈራጅ! ይህንን ሁሉ ወንጀልና ሪነት ከአርባ ዓመታት በላይ አምቆ ኖሮዛሬም እሱ ራሱ ከዚህ ይወትና ልምድ ትምህርት ያላገበት መሆኑን በግልጽ በሚታይበት ሁኔታ፣ “የትውልድ መምህር” ለመሆን የሚከጅልበት የእሳቤ መንገድ ምን ይሆን?

4. የከተማ ቀበሌና የገጠር ገበሬ ማበራት ለእኔ የመጀመያዎቹ ሕዝባዊ የዴሞክራሲ ተሳትፎ መድረኮች ናቸው ብዬ አምናለሁ። ማበራቱ በወቅቱ ሕዝባዊ ድል የምንላቸውን አዋጆች በሥራ ለማዋል ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል። በአዋጁ መሠረት እነዚህን መሠረታዊ ማበራት ማቋቋም፣ ማደራጀትና ማስተማር የማንም ዴሞክራትና ሕዝብ አፍቃሪ ዜጋ ሁሉ ኃላፊነት ነበር ብዬ እገምታለሁ። ለዚህም ነው በዚያን ጊዜ ሌላ ሥራ ቢኖርብኝም፣ ይ አጋጣሚ ለማንም ዴሞክራት ኢትዮጵያዊ ዝብ ጋር ለመራት ትልቅ ድል መሆኑም በማመን ባደኩበትና የቤተሰቦቼ መኖሪያ ቤት በሚገኘው ቀበሌ ለመሳተፍ የወሰንኩት። በወቅቱ በለውጡ ደት የማይስማሙትንም ጨምሮ መወያየት፣ መማር፣ ማስተማር ይቻላል የሚል ፅኑ እምነት ነበረኝ። ይህን የሚቃወሙ ድርጅቶች ነበሩ። ሁኔታው አልጋ ባልጋ አልነበረም። በተመራጮች ላይ ጦርነት ከፈቱ። ከእኔ በፊትም የቀበሌው የመጀመርያ ተመራጭና ሊቀመንበር የነበረችው የሁለት ልጆች እናት ከቀሌ ጽፈት ቤት ስትጣ ተገድላ ነበር። ከፍተኛ 3 ቀበሌ 53 ተመራጭ ሊቀመንበር ኜ ከተመረጥኩ አንድ ወር በማይሞላ ጊዜ ከምኖርበት ከናቴ መኖርያ ቤት ስወጣ እንደዚሁ ተተኩሶብኝ ነበር። በዚህም ምክንያት የቤተሰቤን መኖሪያ ቤትና ቀበሌውንም ለቅቄ ወጣሁ። ስለተሞከረብኝ ግድያ ዛሬ በመጽሐፉ የሚተርከውን ነበብኩ በኋላ በእጅጉ ጥርጣሬ ቢገባኝ ያስደንቃል? 

5. በዚህ ወቅት በከተማው ውስጥ በተለይ የቀበሌ ተመራጮች፣ በመኢሶን አባላትነትና  ደጋፊነት በ“ሰፊው ዝብ ድምፅ” አንባቢነት ጭምር በሚጠረጠሩት የሠራተኛ ማበራት መሪዎች፣ አንዳንድ የመንግት ሠራተኞች ላይ ያነጣጠረ ግድያ  በሰፊው ይፈጸም የነበረበት አሳዛኝ ጊዜ ነበር። ይህን ተከትሎ በቀበሌዎች የተደረጉት ሁለት የመሣሪያ የማሰባሰብ ዘመቻዎች በየቀኑ፣ በየመንገዱ የሚደረገውን ግድያ መግታት አልቻሉም ነበር። ስተኛ ዘመቻ በተለየ መልኩ ለማካሄድ በመንግታቅዶ ለየቀበሌው የተደራጀና ሙሉ ትጥቅ የያዙ ወታደራዊ ቡድኖች የአሰሳው መሪዎች ሆነው ተመደቡ። ለቀበሌው ተመራጮችና ጥበቃ አባላት፣ ሠፈሩንና ነዋሪውን በቅርብ ስለሚያውቁና ወደፊትም አብረው አንደሚኖሩ በመገንዘብ፣ ቃድ ከሌለው መሣሪያ በስተቀር ሌላ እንዳይወረስ ፍተሻው ሰን በማክብርና በ ሥርዓት እንዲካሄድ ወደ ዝርፊያ የሚያመለክት ድርጊት እንዳይፈጸም ማብራያና ትምህርት ቀደም ብሎ ተሰጣቸው። በመንግሥት የሚፈለጉም ሰዎች ስምና ፎቶግራፎች በብዙን መገናኛዎች በሰፊው ተበተኑ። ኮፒ ለእያንዳንዱ ፈታሽ መሪዎች ታደለ። በዚህ መልክ የተቀናጀው አሳሽ፣ በቡድን ተከፋፍሎ አሰሳውን ሲያካሄድ ዋለ።

እኔ የነበርኩበት ቡድን የንግድ ባንክንና የመከላከያ ሚኒስቴርን አልፎ  ቢሮዎችን ለመፈተሽ ወደ ኪዳኔ በየነ አመራ። ከው ፊት ለፊት ንደርስና መንገዱን ገና ሁላችንም አቋርጠን ሳንጨርስ ከቀደሙት ከቡድኑ ወታደራዊ አባላት አንዱ የአውቶማቲክ መሣርያውን እሩምታ ለቀቀው። ወደ ተተኮሰበት አቅጣጫ ስመለከት ተመቶ የወደቀ ሰው አየሁ። በዚህ ጊዜ ሌላ የተኩስ መልስም ሊኖር እንደሚችል በመገንዘብ ዝቅ ብ ጥግ ያዝኩኝ። ከጥቂት ሰኮንዶች በኋላ የመጀመርያ ድርጊቴ የተኮሰውን ወታደር ለምን? ንዴት? ማን ላይ? ንደተኮሰ ስጠይቀው የሚፈለግ ሰው እንዳየ ነገረኝ። በኔ ግምት “በመሰለኝ”፣ ሰላማዊ ሰው ላይ ተኩሶ ይሆናል ብዬ ተበሰጫጨሁ። እነርሱ ግን በርግጠኛነት መሯሯጣቸውን ቀጠሉ። የተመታው ሁለተኛው ሰው ወደ ፎቁ ወጥቶ ራሱን ወረወረ። ይህ ሰው በኋላ እንደተረጋገጠው ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይ ነበር። የሆነው ይብቻ ነው። አንዳርጋቸው ጽጌና ወንድሙ በገጽ 566 ላይ የሚተርኩት የፈጠራ ወሬ ነው። የማንንም መኪና ሆነ የማውቀው ወይም የሚፈለግ ሰው አላየሁም።

7. ዶ/ር ተስፋዬ ደበሳይን አውቀዋለሁ ወይ? በ1965/66 በፈረንይ የኢትዮጵያ ተማሪዎች መታዊ ጉባ በሞንትፐሊዬ ከተማ በተሳተፈበት ጊዜ ከሌሎች ተሳታፊዎች ጋር አግኝቼው ነበር። ከዚያ በፊትም ሆነ በኋላም በምንም አጋጣሚ አልተገናኘንም። ትውውቃችን አንርጋችው ጽጌ  እንደሚተርከው ፈጽሞ አይደለም።  በዚያን ዘመን እርሱ ከሚለው ጓደኛ ጋርም ፓሪስ አልኖርኩም። ይህንን ሁሉ ፈጠራ መተረክ ምን ገፋፋው? ዓላማው ምንድነው? ጥያቄዎቹን ሊመልስ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው። 

አንዳርጋቸው ጽጌ  የትረካውን እውነትት ለማረጋገጥ፣ ወንድሙ እኔ እናት ቤት ምሳውን በልቶ አሰሳውን ይከታተል እንደነበርና የሆነውን ሁሉ እሱው እንደነገረው ያለ ማንገራገር፣ ያለ መጠራጠር፣ በእርግጠኝነት ይጽፋል/ይናገራል። ወንድሙ ለምን እኔንና አሰሳውን ተከትሎ እንደሚድ ሲያስረዳ፣ በገጽ 566 የገጽ ግርጌ ማስታወሻ “ከምሳ በኋላ ዘሪሁን ወደ ነበረበት አካባቢ ለምን እንደሄደ አልነገረኝም። እዚን ጊዜ የትንሾች ነገር አይታወቅም ብሎ እንደ ዋዛ ያልፈዋል። ይህ ነው የአንዳርጋቸውና የወንድሙ “የይን ማኝነት”። በሌላ ገጽ ይንኑ ወንድሙን፣ “በትልቅ ላፊነት”፣ በስፖርት ሜዳ ላይ የሰበሰባቸውን የጉለሌ ታዳጊ ወጣቶች የኢሕአፓን ማያ በማስለበስ ለሜይ አንድ ቀን ሲቀረው.ኤ.. 1976  ልፍ ያዘጋጀና ያለፈ “ጀግና” በማለት በኩራት ያወድሰዋል። በዚያ ቀውጢ ቀን ስንት ፃናት ቤታቸው እንደተመለሱ ቤት ይቁጠረው! በዚህ ይነቱ ምስክር ላይ በመመረት ነው አንዳርጋቸው ጽጌ የውሸት መርዙን የሚረጨው። በእንደዚህ ይነት ማስረጃ ነው ታሪክ እየጻፍኩ፣ ትውልዱንም እያስተማርኩ ነው የሚለው። በዚህ አላለቀም። በአንዳርጋቸው ጽጌ ወሬ ላይ በመንተራስ አቶ ክፍሉ ታደሰም ይህንኑ ልብ ወለድ ትርክት አንዳርጋችው ጽጌ (የአክስቱ ልጅ) ስለነገረኝ ትክክል መሆን አለበት በሚል ግምት በመጸሐፉ ዘግቧል። 

8. በመጨረሻ ገጾቹ ላይ ጸፊው (ገጽ 662) እኔ ከገር የወጣሁት በእናቱ መላና የሱ ቤተብ ባለው ግንኙነት እንደሆነ ጽፏል። ይህም ሌላው ልብ ወለድ ነው።  ለትረካው እሱ እንደሚለው ይበልጥ ሼክስፒሪያን ፍሜ ይሰጠዋል ብሎ ገምቶ ይሆን? ሁኔታውን የሚያውቁ ሰዎች በይወት አሉ። ይታዘቡኛል ብሎ እንኳን አለማሰቡ የሚያስደንቅ ነው። በታሪክም፣ በሁኔታዎችም፣ በገጠመኞችም፣ በዘመድም፣ በጓደኛም መዋሸቱን ሙያ አድርጎ ይዞታል? ሌላም፣ ሌላም አለ። ስለእኔ በዚሁ ላብቃ።

በዚህ አጋጣሚ ሳልገልጽው የማላልፈው ሌላ አጠቃላይ እውነት አለ። “የልሳዎቹ ትውልድ” ከሚባለው ውስጥ  ለገሪቱ ጭቁን ዝቦች በእውነት የወገኑ ወጣትና ምሁራን ነበሩ። ይህንን ልማቸውን ውን ለማድረግ በየአቅጣጫውና በየጎራው እየተደራጁ ብዙ ባትተዋል፣ ብዙ መስዋትነት ከፍለዋል። ስለዚህም ሊከበሩ ይገባል። ስለዚህ ትውልድ ድርሻ በአዎንታና በአሉታ መልኩ ገና ብዙ የሚጻፍና እስሁንም ከተጻፉት የምንማረው ይኖራል። ገራችን ታሪክ በተደጋጋሚ እንደታየውና ዛሬም በተመሳሳይ የገሪቱን የፖለቲካ መድረክ ያጠለሸ ያለው ሳብንና ግለሰብን ያለ መለየትና የሳብ ልዩነትን ያለ መቀበል አባዜ በሰፊው እያጠላለፈን ይታያል። ከዚህ አዙሪት ለመወጣት ከሁሉም አቅጣጫ ጥረትና የፖለቲካ ብስለት ያስፈልጋል። ካለፉት የፖለቲካ ታሪካችን የምንወስደው ትምህርት ስለአሁኑ የገራችን ሁኔታ ግንዛቤ ብርሃን ሰጪና አስተማሪ መሆን አለበት እላለሁ።

በዚህ አቅጣጫ አንዳንድ ጸሐፊዎች በጽፍ፣ በዲዮና ቴሌቪዥ እንዲሁም በማበራዊ ዲያዎች የሌላውን ሰው ስም በማንሳት የፈለገውን ትርክት ያለ ምንም ልጓምና ያለቅንጣት ላፊነት፣ ትርክቱ በብዙ አቅጣጫ ሊያመጣ የሚችለውን ችግርና ቀውስ ከሳቤ ባለማስገባት ሲባትቱ ይታያል። ይህ ብዙ ጊዜ የሚደረገው በጥራዝ ነጠቅነት፣ ያለ ምንም ጥናት፣ ያለ ምንም ማስረጃ፣ ከሚመለከተው ግለሰብ ጋር እውነቱን ለማግኘት ምንም ይነት ጥረት ሳይደረግ ነው። ይህ ነ ምግባር የጎደለው አራር እንደ አንድ ፖለቲካ ትግል ዘዴ ሆኖ በሰፊው አየተራጨ ነው። እያንዳንዱ ጸሐፊ፣ ጦማረኛ፣ የማበራዊ ዲያ አክቲቪስት ንዲሁም ዲያዎች ለሚያሳልፉት መልዕክት ይዘት ተጠያቂነትና ላፊነት መውሰድ ይገባዋል። የነ ምግባር የሚባልም የግል ልጓምም አለ። የግና የሰብዊ መብት ተሟጋቾች፣ ይህን በተለይ ከማበራዊ ዲያዎች ማደግና በሰፊው መራጨት ጋር ተያይዞ የመጣ ስድ “ባህል”ከልማቱ ጥፋቱ እንዳይበዛ ከወዲሁ መስተማር ይገባቸዋል።

ከአዘጋጁ፡- ፊው ከፈረንይ ሞንትፐሊዬ ዩኒርሲቲ በልማት ፕላንና በኪኖሚክ ትንተና በሰኔ 1966 (ጁን 1974) የማስተርስ ዲግሪ ካገኙ በኋላ በትምህርት ሚኒስቴር በትምህርት ፋይናን ኢኮኖሚስትነት፣ ፕላን ቡድን መሪነት፣ የትምህርት አቅጣጫ ለውጥ ጥናት አራት ት አገልግለዋል። በተባበሩት መንግታት ድርጅት የትምህርት፣ የባህልና የሳይንስ ድርጅት (ዩኔስኮ) በልዩ ልዩ የላፊነት ቦታዎች በፓሪስና በጄኔቫ ከ27 ት በላይ ተዋል። ለሰብዓዊ መብቶች መከበርና ለሕግ የበላይነት በማለት በጄነቫ የኢሰመጉ (የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባዔ) በኋላም ሰመጉ ድጋፍ ኮሚቴ ከሌሎች ጋር በማቋቋም ገዛ አድርጓል። አህሬ (AHRE- association for human rights in ethiopia) የሚባል የሰመጉ የድጋፍ ማበር ከሌሎች ጋር መተው በቦርድ አባልነት  እያገለገ ነው። በአሁኑ ጊዜም የሚኖሩት ፈረንሣይ ውስጥ ነው፡፡ ጽሑፉ የእሳቸውን አመለካከት ብቻ የሚያንፀባርቅ ሲሆን፣ በኢሜይል አድራሻው [email protected] ማግኘት ይቻላል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...