Sunday, June 4, 2023
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢትዮጵያ በመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ውጤታማነት ከፍ ያለ ደረጃ ማግኘቷና የሥጋት ደረጃዋ ከፍ ማለቱ ተጠቆመ

- ማስታወቂያ -

ተዛማጅ ፅሁፎች

ተቀማጭነቱን በእንግሊዝ ያደረገው ኮንትሮል ሪስክ የተባለ አማካሪ ቡድን ኦክስፎርድ ኢኮኖሚክስ ጋር በተመባበር በቅርቡ ይፋ ባደረገው የአፍሪካ ሥጋትና ውጤታማነት መለኪያ ሪፖርት፣ ኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ከፍ ያለ ተጠቃሚነትን (ውጤታማነትን) የሚያገኙባት እንደሆነች በመግለጽ ከአሥር ነጥብ ስምንት ማግኘቷን ጠቅሶ ከፍ ያለ ደረጃ እንዳገኘች ይፋ አድርጓል፡፡ ሆኖም በሥጋት ረገድ ከፍ ያለ ደረጃ ላይ መቀመጧን አልሸሸገም፡፡

በርካታ የአፍሪካ አገሮችን የመዋዕለ ንዋይ ምቹነት ከተጠቃሚነትና ከሥጋት አንፃር ገምግሞ ደረጃ የሰጠው ይኼ ሪፖርት፣ ትንንሽ የሚባሉ አገሮች ከትልልቆቹ አንፃር ከፍተኛ ብልጫ ያሳዩበትና ቀድሞ ከፍተኛ ደረጃ ያገኙ የነበሩ እንደ ናሚቢያ ያሉ አገሮች ደግሞ ወደ ታች የተንሸራተቱበት ውጤት መታየቱን ሪፖርቱ አትቷል፡፡

ሪፖርቱ አገሮችን ከመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ተጠቃሚነትና ከሥጋት ልኬት በዘለለ፣ በየአገሮቹ ገንዘባቸውን የሚያፈሱ ባለሀብቶች ጥንቃቄ ቢያደርጉባቸው ያላቸውን ጉዳዮች በመለየት ምክር ለግሷል፡፡ የሪፖርቱ የመጀመርያ ምክር መዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች የመሪዎችን ስሜታዊ የለውጥ ሐሳብ ብቻ በመውሰድ፣ የለውጥ መሪዎቹ ያለ እንቅፋት የፈለጉትን የሚያደርጉ ይሆናሉ የሚል እሳቤ እንዳይዙ የሚል ነው፡፡

በመቀጠልም በአፍሪካ አገሮች መካከል እርስ በርስ የሚኖሩ ግንኙነቶችና ትብብሮች ሊያስገኙ የሚችሉትን አማራጮች ማጤን ይገባል በማለት የሚመክር ሲሆን፣ በሦስተኛ ምክሩ ባለ ብዙ ጽንፍ የሆነና እየሰፋ የመጣው የጂኦ ፖለቲካዊ ፉክክር በአገሮቹ ፖለቲካዊ ሒደትና የቢዝነስ ከባቢ ላይ ምን ያህል ተፅዕኖ እንደሚያሳድሩ ትኩረት አድርጉ ይላል፡፡

ሪፖርቱ በተጨማሪም ኢትዮጵያ በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) መሪነት የተለያዩ ዘርፎችን ለውድድር ክፍት እያደረገች እንዳለች በመጥቀስና በማድነቅ፣ የቴሌኮም ዘርፉን ለግል ባለሀብቶች ክፍት ለማድረግ መወሰኑን አመላክቷል፡፡

‹‹ከአንድ መቶ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ሊያስገኙ የሚችሉት ገበያ የፈጠረው ተስፋ፣ ኢትዮጵያ በመዋዕለ ንዋይ አፍሳሾች ተጠቃሚነት ረገድ ከፍ ያለን ውጤት እንድታስመዘግብ አድርጓል፡፡ ሆኖም ይኼ ደረጃ ካለፈው ወቅት እምብዛም ያልተለየ ሲሆን፣ የሥጋት ደረጃው ግን እጅግ ከፍተኛ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ለቴሌኮም ዘርፍ የተቀመጠው ለግል ባለሀብቶች ክፍት የማድረጊያ የጊዜ ገደብ አልፏል፡፡ የውጭ ምንዛሪ እጥረቱ አሁንም አለ፡፡ እንዲሁም የአካባቢ ምርጫዎች መራዘማቸው ደግሞ በፖለቲካ ማሻሻያው እንምብዛም ገፍቶ እንዳልሄደ ማሳያ ነው፤›› ሲል ሪፖርቱ ያትታል፡፡

ከኢትዮጵያ ጋር  ተመሳሳይ በሆነ ሒደት ውስጥ ያለችው አንጎላና በኢትዮጵያ እየታዩ ያሉት ሒደቶች የለውጥ አስተዳደሮች ውስንነቶች አሉባቸው ነው የሚለው ሪፖርቱ፣ ይኼም የሆነው መዋቅራዊ ችግሮችን ለመፍታት ጊዜ ስለሚጠይቅ ነው ይላል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ካሁን ቀደም በመንግሥት መር ኢኮኖሚ ውስጥ ሲሠሩ የቆዩ የመንግሥት ሠራተኞች አዲስ መዋቅርን ለማምጣት፣ እንዲሁም ወደ ግል ዘርፉ አሳታፊነት ለመሻገር ልምዱና ችሎታው ያንሳቸዋል ሲልም ሪፖርቱ ያስረዳል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች