Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ተቋም ለኢትዮጵያውያን ዕውቅና ሰጠ

የዓለም አቀፉ አትሌቲክስ ተቋም ለኢትዮጵያውያን ዕውቅና ሰጠ

ቀን:

/ ወልደመስቀል ኮስትሬ የምንጊዜም ምርጥ ተብለዋል

የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይ...ኤፍ) ለቀድሞ ጉምቱ የረዥምና መካከለኛ ርቀት አሠልጣኝ ወልደ መስቀል ኮስትሬ (/) እና ለኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ ዕውቅና ሰጠ፡፡ ተቋሙ ዕውቅና ከሰጣቸው ከዓለም ምርጥ ሰባት አሠልጣኞች የምንጊዜም ምርጥ / ወልደመስቀል ቀዳሚው ሆነዋል፡፡

የሻምበል አበበ ቢቂላ ፈለግ በመከተል በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬ ላይ ለደረሰው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ / ወልደመስቀል ኮስትሬ በኦሊምፒክና በዓለም ሻምፒዮና በተለይም በረዥም ርቀት መድረክ ስማቸው በወርቅ ቀለም ለተጻፈው ኃይሌ ገብረ ሥላሴ፣ ደራርቱ ቱሉ፣ ብርሃኔ አደሬ፣ ቀነኒሳ በቀለ፣ ጥሩነሽ ዲባባ፣ መሠረት ደፋር፣ ስለሽ ስህን፣ ገብረ እግዚአብር ገብረ ማርያምና ለሌሎችም ብርቅዬዎቹ አትሌቶች ለደረሱበት ውጤታማነትና ዕውቅና የአንበሳውን ድርሻ በመውሰድ ይጠቀሳሉ፡፡

በረዥምና መካከለኛ ርቀት በኦሊምፒክና በዓለም ሻምፒዮና ለዓመታት ከዕውቅና ማማ ሳይወርዱ፣ ታላላቅና አንፀባራቂ ድሎችን በማስመዝገብ የታወቁ አትሌቶችን በማፍራት የሚታወቁት / ወልደ መስቀል፣ በሕይወት በነበሩበት ወቅትም ይህንኑ ሽልማትና ዕውቅና በማግኘት ብቸኛው ኢትዮጵያዊ መሆናቸው ይታወቃል፡፡

የአሠልጣኝነት ሙያን የጀመሩት ... 1960ዎቹ በረዳትነት እንደሆነ የሚነገርላቸው / ወልደመስቀል፣ በዘርፉ የጥልቅ ዕውቀት ባለቤትም ናቸው፡፡ ዶክተሩ ካፈሯቸው አትሌቶች መካከል የወቅቱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚዳንት ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ ዕውቅናውን አስመልክቶ፣ ‹‹ታላቁ አሠልጣኝ ከዚህም በላይ ዕውቅናና ሽልማት ይገባቸዋል፤›› ብላ በእርሷ የአመራርነት ወቅት በዚህ ታላቅ የዓለም መድረክ በመሆኑ ደስተኛ እንደሚያደርጋት ለታላላቅ የዓለም መገናኛ ብዙኃን መናገሯ ተዘግቧል፡፡

የዓለም አቀፉ ማኅበር የኳታሩ የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ከመጀመሩ በፊት ባከናወነው ጉባዔው ጎን ለጎን አትሌቲክሱን ለማሳደግ በተለይም ከዓለም አቀፉ ተቋም ጋር ለሚኖረው የተቀላጠፈ አሠራርና ግንኙነት አስተዋጽዖ ላበረከቱ ሙያተኞች ዕውቅና ስጥቷል፡፡ ዕውቅና ከተሰጣቸው አንዱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የቴክኒክ ዳይሬክተር አቶ ዱቤ ጅሎ ናቸው። ዓርብ መስከረም 16 ቀን 2012 .. በዶሃ የተጀመረው 17ኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና 11 ቀናት ይካሄዳል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...