Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየየመን እስረኞችን መፍታት

የየመን እስረኞችን መፍታት

ቀን:

ከዓረብ አገሮች በድህነት ወለል ውስጥ ትገኛለች የምትባለው የመን፣ የእርስ በርስ ጦርነት ውስጥ ከተዘፈቀች ዘጠኝ ዓመታትን አስቆጥራለች፡፡ እነዚህ ዓመተት በሺዎች ለሚቆጠሩ ሞትን በሺዎች ለሚቆጠሩ ደግሞ ስደትን እንጂ ትሩፋት አልነበራቸውም፡፡

ከውስጥ የሃውቲ አማፅያን ከውጭ ሳዑዲ ዓረቢያ መራሹ ጦር ለየመን ምድር እሳትን ለሕዝቧ ሞትና ሰቆቃን እያወረዱ ነው፡፡

እ.ኤ.አ. በ2011 የቀድሞውን የየመን ፕሬዚዳንት ዓሊ አብደላህ ሳላህ ከሥልጣን ለማውረድ የተጀመረው አብዮት፣ እስካሁንም ባለመርገቡ የመን በጦርነትና በረሃብ እየታመሰች ትገኛለች፡፡

ዓሊ አብደላህ ሳላህ ከሥልጣን ከተነሱ በኋላ አገሪቷን የሚመሩት አብድራቡህ መንሱር ሃዲ፣ በአገሪቱ ያሉትን በርካታ ችግሮች ለመፍታት አልቻሉም፡፡ በየመን የጀሃዲስቶች ጥቃት፣ በደቡብ የሚገኙ ፅንፈኞች፣ ለቀድሞው ፕሬዚዳንት ሳላህ ታማኝ የነበሩ አገልጋዮች፣ ሙስናው፣ ሥራ አጥነቱና የምግብ ዋስትና መጥፋቱ ለሃዲ ከባድ ፈተና ሆኗል፡፡

የየመን እስረኞችን መፍታት

 

ይህ ለሃውቲ ንቅናቄ አባላት መልካም አጋጣሚን ፈጥሯል፡፡ የየመን ዛዲ ሺሃ ሙስሊም አባላት የቀድሞውን ፕሬዚዳንት ዓሊ አብደላ ሳላህ ለመጣል ሽምቅ ይዋጉ የነበረ ሲሆን፣ ከሳላህ በኋላ የመጡት ዋዲ ችግሮችን መፍታት አለመቻላቸውም ሃውቲዎች  በ2015 የየመንን መዲና ሰን እንዲቆጣጠሩ ምክንያት ሆኗል፡፡

ሃውቲዎች ሰንአን ብቻ ሳይሆን ከአገሪቱ በርካታ ከተሞችን የተቆጣጠሩ ሲሆን፣ የሃይዲን መንግሥት የምትደግፈው ሳዑዲ ዓረቢያ ደግሞ ሃውቲዎቹን ለማጥፋት የአውሮፕላን ድብደባ ትፈጽማለች፡፡

ይህ ያበቃ ዘንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰላም ጥሪ ካስተላለፈም ዓመታት ተቆጥረዋል፡፡ ሆኖም ስኬት አልተመዘገበም፡፡  በሳዑዲ መራሹ ጦር በአየር ሲደበደቡ የከረሙት የሃውቲ አማፅያን፣ ከሁለት ሳምንት በፊት በሳዑዲ ነዳጅ ኢንዱስትሪዎች  ላይ የአፀፋ ምላሻቸውን በሰው አልባ አውሮፕላን ሰጥተዋ፡፡

የዚህ ዜና ሳያበቃ ደግሞ ከወር በፊት 500 የሳዑዲ ዓረቢያ ወታደሮችን ገድለናል ወይም አቁስለናል ሲሉ ተንቀሳቃሽ ምስል ለቀዋል፡፡ ከዚህ ባለፈም 290 እስረኞችን ፈትተዋል፡፡

የእስረኞቹ ዜግነት ባይገለጽም፣ ይህ ወደ ሰላም ለመምጣት መልካም አጋጣሚ መሆኑን ዓለም አቀፉ የቀይ መስቀል ኮሚቴ አስታውቋል፡፡ ቢቢሲ እንደዘገበው፣ የየመን ሃውቲ  ንቅናቄ አባሎች እስረኞቹን የለቀቁት በተባበሩት መንግሥታት የሰላም ኢንሽየቲቭ አማካይነት ነው፡፡ ከተለቀቁት እስረኞች መካከልም 42 ያህሉ ሳዑዲ ዓረቢያ ባፈው ወር እስር ቤቶችን በአውሮፕላን ስትደበድብ ከሞት የተረፉ ናቸው፡፡ በወቅቱ ከ100 በላይ እስረኞች መገደላቸው ይታወሳል፡፡

በየመን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ፣ የሃውቲ  ዕርምጃ በሳዑዲም ሆነ በየመን በኩል ያሉ እስረኞችን ለመፍታትና ወደ ሰላም ለማምጣት በር ይከፍታል ብለዋል፡፡ እስረኞችን መፍታትም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በየመን የሚዋጉ አካላትን ወደ ሰላም ለማምጣት ከጀመረው እንቅስቃሴ አንዱ ነው፡፡

የሃውቲ  ኮሚቴ መሪ አብዱል ቃድር አል ሙርታዳ አሁን ከተለቀቁት 290 እስረኞች በተጨማሪ 350 እስረኞች ሊለቀቁ እንደሚችሉ ተናግረዋል፡፡ ከነዚህ ውስጥ ሦስቱ እስረኞች የሳዑዲ ዓረቢያ ዜግነት ያላቸው እንደሆኑም ጠቁመዋል፡፡

የየመን እስረኞችን መፍታት

 

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በየመን ያለውን ጦርነት ለማስቆም በስዊድን ስቶኮልም የጀመረው የሰላም ድርድር አካል የሆነው እስረኞችን የመልቀቅ አካሄድ ይቀጥላል ተብሎም ይታሰባል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ልዩ መልዕክተኛ ማርቲን ግሪፍትስ ሃውቲዎች እስረኞችን መፍታት መልካም ብለው፣ ሁሉም አካላት እስረኞችን መልካም በሆነ መልኩ እንዲለቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሃውቲ ንቅናቄ አባላት እስረኞቹን የለቀቁት በሳዑዲ ድንበር ከ200 በላይ የመንግሥት ደጋፊ ወታደሮችን መግደላቸውንና ከ2 ሺሕ በላይ መማረካቸውን ባስታወቁ ማግሥት ነበር፡፡

የሃውቲ  ንቅናቄ ቃል አቀባይ በመንግሥት ደጋፊዎች ላይ ንቅናቄው ዕርምጃ መውሰዱንና በዚህም በሺዎች የሚቆጠሩ መማረካቸውን፣ በመቶዎች የሚቆጠሩ ደግሞ መሞታቸውን ቢገልጹም፣ የሳዑዲ ዓረቢያ መራሹ ጦር ቃል አቀባይ የተማረከም ሆነ የተገደለ እንደሌለ፣ የየመን አማፂያን የተለመደ የማሳሳቻ ዜና መልቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

የሰብዓዊ ድጋፍ አድራጊዎች ግን የሃውቲ  ንቅናቄ አባላት የለቀቁት ተንቀሳቃሽ ምስል እውነት ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል፡፡

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን እውነተኛነቱን ማረጋገጥ ባይችሉም በሃውቲዎች የተለቀቀውንና የጦር መኪኖች ሲቃጠሉ የሚያሳየውን ተንቀሳቃሽ ምስል ይዘው ወጥተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...