Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለቤትነት መብት ጥቅምና አስተዳደር የሚወስን ሕግ ሊወጣ ነው

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ባለቤትነት መብት ጥቅምና አስተዳደር የሚወስን ሕግ ሊወጣ ነው

ቀን:

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ኢንሹራንስ መግባት ይጠበቅባቸዋል

የጋራ መኖሪያ ይዞታ ለልማት ቢፈለግ ወይም ጉዳት ቢደርስበት የሀብት ክፍፍል እንዴት እንደሚፈጸም ይወስናል

የኮንዶሚኒየም ቤቶች ላይ የሚኖርን የጋራና የተናጥል ባለቤትነትና ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚነሳን የመብት፣ ጥቅምና አስተዳደራዊ ጉዳዮች የሚወስን የሕግ ማዕቀፍ ዝግጅት መጠናቀቁ ታወቀ፡፡ 

- Advertisement -

በ1952 ዓ.ም. የወጣው የፍትሐ ብሔር ሕግ የጋራ ሕንፃ አስተዳደርን አስመልክቶ ውስን ድንጋጌዎችን ቢይዝም፣ ጉድለቶቹን ለመሙላትና ወጥና ራሱን የቻለ እንዲሆን ለማድረግ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተጀመረውን የጋራ መኖሪያ ቤቶች ግንባታ ተከትሎ የጋራ ሕንፃዎች ባለቤትነት አዋጅ ቁጥር 370/1995 በ1995 ዓ.ም. ወጥቷል፡፡ ሆኖም በጊዜ ሒደት የመጡ ፍላጎቶችንና በወቅቱ ያልተስተዋሉ ክፍተቶች ጎልተው በመምጣታቸው፣ አዲስ ሕግ ማውጣት አስፈላጊ እንዳደረገው ሪፖርተር ያገኘው የሰነድ ማስረጃ ያመለክታል፡፡

የተረቀቀው የሕግ ማዕቀፍ የጋራ መኖሪያ ሕንፃ፣ ሕንፃው ያረፈበት ቦታ፣ የጋራ መጠቀሚያዎችና አጠቃላይ የጋራ መኖሪያ ግቢው ይዞታ ጋር የሚያያዙ መብት፣ ጥቅምና ግዴታዎችን እንደሚወስን የሰነዱ ሀተታ ያመለክታል፡፡ 

የጋራ መኖሪያ ሕንፃ በቤቶችና በጋራ መጠቀሚያዎች መሠረት ሊከፋፈል ይችላል ወይስ አይችልም የሚለውን ረቂቅ የሕግ ሰነዱ የሚመልስ ነው፡፡

በጋራ መጠቀሚያ ሕንፃና አጠቃላይ ይዞታ ላይ ባለቤቶች መብትና ጥቅም ቢኖራቸውም፣ የጋራ መኖሪያው በጉዳት ምክንያት አገልግሎት መስጠት እንደማይችል ከተረጋገጠ ወይም ይዞታው ለልማት ተፈልጎ እንዲፈርስ ካልተወሰነ በስተቀር ባለቤቶች በጋራ የመኖሪያ ሕንፃው ላይ ያላቸው መብት የማይከፋፈልና ከእያንዳንዱ ቤት የባለቤትነት መብት ጋር ሳይነጣጠል የሚቆይ መብት እንደሆነ ያመለክታል፡፡

ይህ ማለት ግን ከጋራ ባለቤትነት ውጭ ያለውን የተናጥል ባለቤትነት ማለትም በጋራ ሕንፃ ላይ የሚገኝን አንድን ቤት የመሸጥ የመለወጥ መብትን እንደማይገድብ ያስገነዝባል፡፡

የእያንዳንዱ ቤት የባለቤትነት መብት በጋራ ሕንፃ መጠቀሚያ ላይ የሚያስገኘው የማይከፋፈል መብት እንዴት እንደሚወሰንም ሰነዱ ያስረዳል፡፡ በዚህም መሠረት የተናጥል ቤት ባለቤትነት በጋራ ሕንፃ መጠቀሚያ ላይ የሚያስገኘው የማይከፋፈል መብት ድርሻ  በተናጥል ይዞታው የካሬ ልኬት መሠረት ከጋራ ሕንፃው በመቶኛ ስሌት ተሰልቶ የድርሻ መጠን እንደሚወሰን ያስረዳል፡፡ 

ለምሳሌ በ800 ሜትር ካሬ የወለል ስፋት ባለው አንድ የጋራ ሕንፃ ላይ 24 የግል ቤት ካላቸው የጋራ ባለቤቶች መካከል አንድ ባለ 30 ካሬ ይዞታ ያለው መኖሪያ ቤት ባለቤት በጋራ ሕንፃው ላይ የሚኖረው ድርሻ የግል ይዞታው የወለል ስፋት ሲካፈል ለጠቅላላ የጋራ ሕንፃ ይዞታው የወለል ስፋት እንደሚሆንና በዚህም ስሌት መሠረት ለአብነት የተጠቀሰው ባለ 30 ካሬ ይዞታ መኖሪያ ቤቱ ባለቤት በጋራ ሕንፃው ላይ የሚኖረው ድርሻ 3.75 በመቶ እንደሚሆን ያስረዳል፡፡

የጋራ ሕንፃ መጠቀሚ ማለት ምን እንደሚያካትትም ሰነዱ በዝርዝር ያስቀምጣል፡፡ በዚህ መሠረት የጋራ መጠቀሚያ ማለት በተናጠል ከተያዙት ቤቶች ውጭ ያለ ማናቸውም የሕንፃው አካል ማለትም የጋራ ግድግዳ፣ ደረጃ መወጣጫዎች፣ ኮሪደሮች፣ ሊፍት/አሳንሰር፣ ጣሪያ፣ የደረቅ ቆሻሻ ማስወገጃ ቴክኖሎጂዎች፣ የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች፣ ሴፕቲክ ታንክ፣ የውኃ ማጠራቀሚያ/ሪዘርቨየር/ እና ታንከሮች፣ የውኃ፣ የኤሌክትሪክና የቴሌ መስመሮች፣ የቴሌቪዥን፣ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ማስጠንቀቂያ መስመሮች፣ የአደጋ ጊዜ መወጣጫና ውጫዊ አካላት፣ የጋራ ሕንፃ መተላለፊያ፣ የመሠረተ ልማት መስመሮችና ተያያዥ ሲስተሞች፣ የጋራ መጸዳጃና መታጠቢያ ቤቶች፣ የመኪና ማቆሚያ ቦታዎች፣ የአረንጓዴ ቦታዎችና ሌሎች የሕንፃውንና የምድረ ግቢ አካላትን እንደሚያካትት ተመልክቷል፡፡

የጋራ ሕንፃው ከፍተኛ ውድመት ሲያጋጥመው ወይም ይዞታው ለሌላ ልማት በመንግሥት ተፈልጎ እንዲፈርስ ሲወሰን፣ የሀብት ክፍፍል ተደርጎ በዚህ የሕግ ማዕቀፍ መገዛቱ እንደሚያበቃም ሰነዱ ያመለክታል፡፡

ይህ ሁኔታ ሲያጋጥምም ከላይ በተገለጸው መንገድ የጋራ ድርሻ መጠን ተሰልቶ እንደሚከፋፈል ያመለክታል፣ ይህም በዚህ የሕግ ማዕቀፍ አማካይነት ሕጋዊ እውቅና በሚሰጣቸው የጋራ ሕንፃ የቤት ባለቤቶች ማኅበር አማካይነት ሕጉን መሠረት አድርጎ የሚፈጸም እንደሚሆን ያስረዳል፡፡

ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የጋራ ሕንፃዎች ይዞታ ለአንድ አካል ከተዛወረ፣ ከተወሰደ ወይም እንዲፈርሱ ከተደረገ ለሚደርሰው ጉዳት ወይም ካሳ መንግሥት ባወጣው አዋጅ (ለሕዝብ ጥቅም ሲባል በሚለቀቅ መሬት ላይ ለሠፈረ ንብረት ስለሚከፈል ካሳ) መሠረት የሚታይና የሚፈጸም መሆኑን ያመለክታል፡፡

የጋራ ሕንፃ ቤት ባለቤቶች ማኅበር የሕግ ሰውነት ያለው አካል ሆኖ በአስገዳጅት የሚቋቋም እንደሚሆንና የጋራ ባለቤቶችም የማኅበሩ አባል የመሆንና መዋጮዎችን የመክፈል ግዴታ እንደሚጣልባቸው ያስረዳል፡፡

የጋራ ሕንፃ ባለቤቶች ማኅበር ለጋራ መጠቀሚያዎች የመድን ዋስትና መግባት እንደሚኖርባቸው በአስገዳጅነት የተቀመጠ ሲሆን፣ ከጋራ መጠቀሚያዎች ውጪ ለሚገኙ ቤቶች የመድህን ዋስትና የመግባት ኃላፊነት የተናጥል ባለቤቶች እንደሚሆንና ይህም የሚበረታታ እንጂ አስገዳጅ እንደማይሆን በሰነዱ ተመልክቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...