Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ መጻሕፍት ታወቁ

የሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት የመጨረሻ ዕጩ መጻሕፍት ታወቁ

ቀን:

በመጪው ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚካሄደው የሦስተኛው ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት በረዥም ልቦለድና በግጥም፣ በልጆች እና በጥናትና ምርምር መጻሕፍት ዘርፍ የመጨረሻዎቹ ዕጩዎች መለየታቸው ታወቀ፡፡

ሆሄ ሽልማት ለሪፖርተር በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በዘንድሮው ሽልማት ከአማርኛ በተጨማሪ በትግርኛና በአፋን ኦሮሞ የተጻፉ የልጆች መጻሕፍትም ተካተዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍት ኤጀንሲ ጋር በመተባበርም ዘንድሮ የጥናትና ምርምር መጽሐፍ መርጦ ለመሸለም ተዘጋጅቷል፡፡

በ2010 ዓ.ም. ከታተሙና በመስፈርቱ መሠረት ለውድድር የተመረጡት 13 ልቦለዶች መካከል አምስት ዕጩዎች መልህቅ (ዘነበ ወላ)፣ መርበብት (ዓለማየሁ ዋሴ)፣ አፍ (አዳም ረታ)፣ ኤቶዮጵ ዶ/ር (ኤልያስ ገብሩ)፣ ጃን ተከል (ፍሬ ዘር) ናቸው፡፡

በግጥም ዘርፍ የዓመቱ ምርጥ አምስት ዕጩ መጻሕፍት፣ ክብ ልፋት (መስፍን ወልደትንሳኤ)፣ የልብ ማህተም (ሰሎሞን ሳህለ)፣ የወይራ ሥር ጸሎት (በድሉ ዋቅጅራ)፣ ወደ መንገድ ሰዎች (መዘክር ግርማ)፣ የማያልቅ አዲስ ልብስ (በቃሉ ሙሉ) ሲሆኑ፤ በልጆች መጻሕፍት ዘርፍ ዕጩዎቹ ተረቶች በግጥም (በኃይሉ ገብረእግዚአብሔር)፣ ውሸታሙ ቢሊጮ (ታለጌታ ይመር)፣ ጦጢት ጉድ ሆነች (ትክክል ገና) መሆናቸው ታውቋል፡፡

በጥናትና ምርምር ዘርፍ ሦስቱ ዕጩ መጻሕፍት የጎጃም ትውልድ በሙሉ ከዓባይ እስከ ዓባይ (አለቃ ተክለየሱስ ዋቅጅራ እንደጻፉት/ ግርማ ጌታሁን እንዳዘጋጀው)፣ የብራና መጻሕፍት አዘገጃጀት (ሊቀ ጉባኤ ፈቃደሥላሴ ተፈራ)፣ የግእዝ ቅኔያት (አዘጋጅ ሥርግው ገላው (ዶ/ር)/ አለቃ አፈወርቅ እንደጻፉት) ናቸው፡፡

 በየዘርፉ አንደኛ የሚወጡትን የመጨረሻዎቹን አሸናፊዎች ለመለየት በዳኞች ከሚደረገው ዳግም ግምገማ በተጨማሪ ከአንባቢያን የሚሰበሰበው ድምፅ ከአጠቃላይ ውጤቱ 20 በመቶ የሚይዝ መሆኑን ያስታወቀው ተቋሙ፣ አንባቢያን አንደኛ መውጣት ይገባዋል የሚሉትን መጽሐፍ ርዕስ እስከ ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ በሽልማቱ የፌስቡክ ገጽ www.facebbo.com Hohe-Awards እንዲሁም በሽልማቱ የትዊተር አድራሻ @HoheAwards የመጽሐፉን ርዕስ ማሳወቅ የሚችሉበት ዕድል ተመቻችቷል ብሏል፡፡

በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ከምሽቱ 12፡00 እስከ 2፡00 ሰዓት በሚካሄደው የሽልማት ፕሮግራም፣ ለሥነ ጽሑፍ ዕድገትና ለንባብ ባህል መዳበር የላቀ አስተዋጽኦ ያበረከቱ ግለሰቦችና ተቋማት በዝግጅቱ ላይ ዕውቅና ይሰጣቸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...

አሳርና ተስፋ!

ከቱሉ ዲምቱ ወደ ቦሌ ጉዞ ልንጀምር ነው፡፡ ገና ከመንጋቱ...