Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ የብድር ስምምነቶችን ለማፅደቅ ፓርላማው መመርመር ጀመረ

ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ የብድር ስምምነቶችን ለማፅደቅ ፓርላማው መመርመር ጀመረ

ቀን:

በኢትዮጵያ መንግሥትና በተለያዩ አገሮች መንግሥታትና የፋይናንስ ተቋማት መካከል የተፈረሙና ድምራቸው ከአንድ ቢሊዮን ዶላር በላይ የሆኑ ረቂቅ የብድር ስምምነቶችን ለማፅደቅ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ውይይት አደረገባቸው፡፡

ሐሙስ መስከረም 29 ቀን 212 ዓ.ም. አምስተኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አምስተ ዓመት የሥራ ዘመን አንደ መደበኛ ጉባዔውን ሲያካሄድ ምክር ቤቱ 14 አጀንዳዎች ላይ ተወያይቷል፡፡ በዕለቱ ምክር ቤቱ ከቀረቡለት አጀንዳዎች ስድስቱ የብድር ስምምነትን የሚመለከቱ ነበሩ፡፡ምምነቶቹ በዋነኝነት የመጠጥ ውኃ አቅርቦትን ተደራሽ በማድረግ፣ የአርሶና አርብቶ አደሩን ኑሮ በማሻሻል ተጠቃሚነቱን ሊያሳድግ የሚችሉና ለመሠረተ ልማት ዝርጋታ የሚውሉ የብድር ስምምነቶች ናቸው፡፡

ከቀረቡትም የማፅደቂያ ረቂቅ አዋጆች ውስጥ በቅድሚያ በአባላቱ ውይይት የተደረገበት ከዓረብ ባንክ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ልማትና ከነዳጅ አምራችና ላኪ አገሮች ለዲላ ቡሌ ሆራ ዋጮ የመንገድ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ የሚሆን 42 ሚሊዮን ዶላር ብድር ሲሆን፣ ከኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ 22 ሚሊዮን ዶላር በአጠቃላይ የ64 ሚሊዮን ዶላር በጀት የተያዘ መሆኑን ረዳት የመንግሥት ተጠሪ አምባሳደር መስፍን ቸርነት ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት ገልጸዋል፡፡

የጌዴኦና ጉጂ ማኅበረሰብን ተጠቃሚ የሚያደርገው የዲላ ቡሌ ሆራ ዋጮ የመንገድ ፕሮጀክት የንግድ ሥርዓትን ለማሳደግ እንዲሁም አካባቢው የሚታወቅባቸውን የግብርና ምርቶች በቀላሉ ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ረዳት ተጠሪው አክለዋል፡፡

ስምምነቱ 27 ዓመታት ተከፍሎ የሚጠናቀቅና ጥቅም ላይ ባልዋለው ብድር በዓመት አንድ ከመቶ ወለድ እንዲከፈል የሚያስገድድም እንደሆነ ተመልክቷል፡፡ በብድር ስምነቱና በማፅደቂያ ረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት ከተደረገ በኋላ ለዝርዝር ዕይታ በሙሉ ድምፅ ለገቢ፣ በጀትና ፋይናንስ ቋሚ ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

በተጨማሪም ለቆላማ አካባቢዎች የኑሮ ማሻሻያ ፕሮጀክት 350 ሚሊዮን  ዶላር ማስፈጸሚያ ከዓለም አቀፍ ልማት ማኅበረሰብ የተገኘ ሲሆን፣ ስድስት ክልሎች ማለትም በሶማሌ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያ፣ በደቡብ፣ በጋምቤላናቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ባሉ አርብቶ አደሮችና ከፊል አርብቶ አደሮች በአጠቃላይ 100 ወረዳዎችን ያቀፈ ፕሮጀክት እንደሆነ በሪፖርቱ ላይ ተብራቷል፡፡

ብድሩ 32 ዓመታት የጊዜ ገደብ ያለውና ከወለድ ነፃ ሲሆን፣ ስድስት ዓመታት የችሮታ ጊዜ ያለው ሆኖ በሚሰጠው አገልግሎት ጥቅም ላይ ባልዋለው ብቻ በየዓመቱ 0.75 የወለድ ክፍያ እንዲከፈል የሚደነግግ መሆኑንና ተጠቃሚነቱን ከፍ እንደሚያደርግ ተነስቷል፡፡

ክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ በስፋት ለሚታየው የንፁህ የመጠጥ ውኃ ተደራሽነት ችግርን ለመፍታትና ማኅበረሰቡን በልማት ተጠቃሚነቱን ለማረጋገጥ የሚያስችል ከዓለም አቀፍ የልማት ማኅበር 300 ሚሊዮን ዶላር፣ ከኮሪያ ኤክስፖርት ኢምፖርት ባንክ ደግሞ 110 ሚሊዮን ዶላር ብድር የተገኘ መሆኑን ረዳት የመንግሥት ተጠሪው ገልጸዋል፡፡

ብድሩ ለከርሰ ምድር ውኃ፣ ለመስኖ ልማት፣ ለመጠጥ ውኃ አቅርቦት፣ ለአካባቢ ጽዳት እንዲሁም ለገጠር ግብርና ልማት ሥራና ለውኃ ሀብት አስተዳደር አቅም ማሳደጊያ እንደሆነ ነው የተብራራው፡፡

በምክር ቤቱም የተመራለት ቋሚ ኮሚቴም በጥልቀት ሊያየው እንደሚገባው አስተያየት የተሰጠ ሲሆን፣ በተለይ የተመሩ የብድር ስምምነቶች ከፍትሐዊነት ጋር ተያይዞና ፕሮጀክቶቹ የሚሠሩባቸው ወረዳዎችም ሆኑ ቀበሌዎች በግልጽ አለመቀመጣቸው ችግር እንዳይፈጥር ቋሚ ኮሚቴው በትኩረት ማየት እንዳለበት  በምክር ቤቱ አባላት አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

አገሪቱ ከዚህ ቀደም የተወሰዱ ብድሮችን የመመለስ አቅሟ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየመነመነ የመጣ መሆኑ እንደሚታወስ ምክር ቤቱ ገልጾ፣ አሁን ላይ የተደረጉ የብድር ስምምነቶች አዋጪነታቸው መታየት ስላለበት የገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ፕሮጀክቶች የደረሱበትን ደረጃ ለምክር ቤቱ በዝርዝር ማቅረብ እንዳለበት አፈባዔው ታገሰ ጫፎም አጽንዖት ሰጥተዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...