Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽኑና ክለቦች በ“ክለብ ተገቢነት መሥፈርት” ላይ እንዲሠሩ ተጠየቀ

ፌዴሬሽኑና ክለቦች በ“ክለብ ተገቢነት መሥፈርት” ላይ እንዲሠሩ ተጠየቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እግር ኳሱን በሁሉም ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ተደራሽ ለማድረግ ከሚያደርገው ጥረት ጎን ለጎን ክለቦች በተለይም የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የሚፈለግባቸውን “የክለብ ተገቢነት መሥፈርት” (ላይሰንሲንግ) እንዲያሟሉ ማድረግ እንደሚጠበቅበት ተጠየቀ፡፡ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) በዚህ ጉዳይ ለብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያ መስጠት መጀመሩ ታውቋል፡፡

ካፍ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ክለቦች ሊያሟሉ የሚገባው የክለብ ተገቢነት መሥፈርት በተጨማሪ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በ2011 ዓ.ም. እና 2012 ዓ.ም. የውድድር ዓመት በአኅጉራዊ መድረክ የሚሳተፉ ክለቦችን ዝርዝር እንዲያሳውቅ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ማሳወቅ ባለመቻሉ የተነሳ በኢትዮጵያ ላይ 5,000 የአሜሪካ ዶላር የገንዘብ ቅጣት ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ቅጣቱን አስመልክቶ በላከው መግለጫ ካፍ ያስተላለፈው የገንዘብ ቅጣት፣ የፕሪሚየር ሊጉ የ2011 ዓ.ም. ውድድር ዓመት አሸናፊ መቐለ 70 እንደርታና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው የፋሲል ከተማ ክለቦች በአኅጉራዊ ተሳትፏቸው ከክለብ የተገቢነት መሥፈርት ጋር ተያይዞ ማሟላት የነበረባቸውን ባለማሟላታቸው እንደሆነ ማሳወቁ ይታወቃል፡፡ ፌዴሬሽኑ ቅጣቱን ለማስነሳት ተደጋጋሚ ጥረት እንዳደረገ፣ ሆኖም ካፍ በውሳኔው መፅናቱን ጭምር በመግለጫው አካቷል፡፡

ካፍ ከክለብ የተገቢነት መሥፈርት ጋር ተያይዞ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ላይ ተጨማሪ ቅጣት የሚጥልበት ዕድል እንዳለው የሚናገሩ ሙያተኞች አሉ፡፡ ሙያተኞቹ ምክንያቱን አስመልክቶ፣ ‹‹ክለቦች አሁንም በትኩረት የሚወዛገቡት ውድድር ተኮር ላይ ነው፡፡ ከውድድር ጎን ለጎን በካፍ መሥፈርት መሠረት ክለቦች ሊያሟሉ ከሚገባቸው መካከል ፋይናንስ፣ መሠረተ ልማትና የሰው ኃይል መሠረታዊ ናቸው፡፡ በዚህ እሳቤ ከኢትዮጵያ ፕሪሚየር ክለቦች ውስጥ ታላላቆቹን ጨምሮ ብዙዎቹ ሙሉ በሙሉ ማለት በሚያስችል መልኩ መሥፈርቱን የሚያሟሉ አይደሉም፤›› ብለው ያምናሉ፡፡

ይህን በሕግ የመከታተልና የማስፈጸም ኃላፊነት የተሰጠው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቢሆንም አሁን ባለው ሁኔታ የተቋሙ አቅም ጥያቄ ውስጥ መግባቱን የሚናገሩት ሙያተኞቹ፣ በቅርቡ ከተጨዋቾች የደመወዝ ጣሪያ ጋር ተያይዞ የተላለፈው ውሳኔ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ እየተደረገ አለመሆኑ ምሳሌ አድርገው ይጠቅሳሉ፡፡

ክለቦች ዛሬም ቀደም ሲል በነበረው ዓይነት አሠራር ለአንድ ተጨዋች የፊርማና መሰል ወጪዎች እየከፈሉ መሆኑ የአደባባይ ምስጢር ሆኖ የሚወሰድ ዕርምጃ እንደ ሌለ የሚናገሩት እነዚሁ ሙያተኞች፣ በሌላ በኩል ክለቦች እንዲያሟሉ ከሚጠበቅባቸው መካከል በዋናነት የፋይናንስ ሥርዓት፣ የሰው ኃይል፣ የሜዳ ዓይነትና መሰል መሠረተ ልማት ላይ በጣም ብዙ እንደሚቀራቸው ይናገራሉ፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የካፍ ክለብ ተገቢነት መሥፈርት (ላይሰንሲንግ) ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ ተድላ ዳኛቸው በበኩላቸው፣ ፌዴሬሽኑም ሆነ ክለቦች በዚህ ጉዳይ ላይ የተጠናከረ ሥራ መሥራት ካልቻሉ ነገሮችን አስቸጋሪ እንደሚያደርጋቸው ያምናሉ፡፡

እንደ ኃላፊው የአገሪቱ ክለቦች በአብዛኛው በካፍ የክለብ ተገቢነት መሥፈርት መሠረት ይገምገሙ ቢባል አንድም ክለብ እንደማይኖር፣ አሁንም ክለቦች ከውድድር ጋርና መሰል ጉዳዮች ላይ እያጠፉት ያለውን ጊዜ በመቀነስ መሠረታዊ ለሚባሉ በተለይም በክለብ ተገቢነት መሥፈርት ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥተው ሊሠሩ እንደሚገባ ያሳስባሉ፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...