Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበዋስትና የተለቀቁት የእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ጥያቄ አስነሳ

በዋስትና የተለቀቁት የእነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ ጉዳይ ጥያቄ አስነሳ

ቀን:

በባህር ዳርና አዲስ አበባ ከተሞች ውስጥ በተቀራራቢ ሰዓታት በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደሉት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ምክንያት ተጠርጥረው ለሦስት ወራት ያህል ታስረው የነበሩት ‹‹እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ እንዲለቀቁ የተደረጉበት ምክንያት የተጠረጠሩበት ጉዳይ ዋስትና ስለማያስከለክል ነውን?›› የሚል ጥያቄ እየተነሳ ነው፡፡

ተጠርጣሪዎቹ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ የነበሩት ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ፣ ኮሎኔል አለበል አማረና ኮሎኔል ባምላክ ዓባይ፣ ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. እያንዳንዳቸውን በ10,000 ብር ዋስትና መለቀቃቸውን አስመልክቶ፣ የሕግ ባለሙያዎችና የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች በሰጡት አስተያየት፣ የተጠረጠሩበት ወንጀል ዋስትና የማይከለክል ከሆነ፣ ‹‹ለምን ይህንን ያህል ጊዜ እንዲታሰሩ ተደረገ?›› በማለት ይጠይቃሉ፡፡

የሕግ ባለሙያው አቶ አብዱ መሐመድ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ተጠርጣሪዎቹ በእስር ያሳለፉት ጊዜ በጣም ብዙ ነው፡፡ መርማሪ ፖሊስና ዓቃቤ ሕግ ተጠርጠሪዎቹ የተጠረጠሩበት የወንጀል ድርጊት ውስጥ ታሳታፊ መሆናቸውን የሚያመላክት ተጨባጭ ማስረጃ ለመፈለግ፣ ቢበዛ ቢበዛ ከሁለት ቀጠሮ በላይ መሄድ አይገባቸውም ነበር፡፡ ማስረጃ ባይገኝ እንኳ፣ ‹‹አሁን እንዳደረጉት›› የተጠረጠሩበት ጉዳይ ዋስትና እንደማያስከለክል ከተረዱ፣ የዋስትና ሁኔታ ላይ በመከራከር በበቂ ዋስትና እንዲለቀቁ ማድረግ ይችሉ እንደነበር አስረድተዋል፡፡

ተጠርጣሪን ለሦስት ወራት አስሮ፣ ‹የተጠረጠሩበት ጉዳይ ዋስትና ስለማያስከለክል በዋስ ቢለቀቁ አልቃወምም፤›› ማለት ተገቢ አለመሆኑን አክለዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ አንድን ተጠርጣሪ አስሮና ወንጀል ፈልጎ ማስቀጣት ብቻ ሳይሆን፣ ተጠርጣሪው ነፃ መሆኑን የማጣራት ኃላፊነትም እንዳለበት የጠቆሙት የሕግ ባለሙያው፣ ያልተሠራ ወንጀል ወይም ማስረጃ ለመፈላለግ ሰዎችን በእስር ማቆየት፣ ሕገ መንግሥታዊና ተፈጥሯዊ የመዘዋወር መብትን ከማጣስ ባለፈ፣ በሕግ የሚያስጠይቅ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ደግሞ በሰጡት አስተያየት እንዳስረዱት፣ ማንንም ሰው በወንጀል መጠርጠር ይቻላል፡፡ ነገር ግን የተጠረጠሩበትን ወንጀል ሳያጣሩ ማሰር ግን አይቻልም፡፡ ይህንንም ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣን ላይ እንደወጡ፣ ‹‹ከዚህ በኋላ ሰዎች የተጠረጠሩበትን ወንጀል ሳናጣራ አናስርም፤›› በማለት ያረጋገጡት ቢሆንም፣ በተግባር ግን እየሆነ ያለው ሌላ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራም በወቅቱ ተጠርጥረው መታሰራቸው ያንን ያህል ‹‹ለምን?›› ባያስብልም፣ ከታሰሩ በኋላ ግን ይህንን ያህል ጊዜ መታሰር እንዳልነበረባቸውና ዓቃቤ ሕግ አሁን ላይ ያደረገውን፣ ቢያንስ ቢያንስ በሦስት ቀጠሮዎች ውስጥ ሊያደርገው ይችል እንደነበር ገልጸዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ አሁንም የተፈቱት የተጠረጠሩበት ጉዳይ ዋስትና ስለማያስከለክል ሳይሆን፣ የፈጸሙት ወይም ሊያስጠረጥራቸው የሚችል የምርመራ ውጤት በመጥፋቱ ነው ብለው እንደሚያምኑም ተናግረዋል፡፡

ጠበቆቻቸው በየቀጠሮው፣ ‹‹ዋስትና ሊያስከለክላቸው የሚችል ምንም ዓይነት ማስረጃ አልቀረበባቸውምና የዋስትና መብታቸው ይጠበቅልን፤›› እያሉ ሲከራከሩ፣ ፍርድ ቤቶቹም የቀረበውን ጥያቄ ውድቅ በማድረግ የተጠየቀውን የጊዜ ቀጠሮ በመፍቀድ ከሁለትና ሦስት ቀጠሮዎች በኋላ የቀረበውን የምርመራ መዝገብ ተመልክተውና መርምረው፣ ሕገ መንግሥታዊ የሆነውን የዋስና መብታቸውን ሊጠብቁላቸው ይገባ እንደነበርም አስተያየት ሰጥተዋል፡፡

የአማራ ክልል ዓቃቤ ሕግ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በባህር ዳር ከተማ በተገደሉት አምባቸው መኮንን (ዶ/ር)፣ አቶ እዘዝ ዋሴና አቶ ምግባሩ ከበደ፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ በተገደሉት ጄኔራል ሰዓረና ሜጀር ጄኔራል ገዛኢ አበራ ግድያ ጋር በተያያዘ ተጠርጥረዋል በሚል፣ አሁን በዋስ የተፈቱትን እነ ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞን ጨምሮ በርካታ ተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እያደረገ መሆኑን ስንዘግብ መቆየታችን ይታወሳል፡፡ ተጠርጣሪዎቹ የተወሰኑ ጊዜያት ቀጠሮ ከተፈቀደባቸው በኋላ፣ የወረዳው ፍርድ ቤት ተጨማሪ ጊዜ በመንፈጉ፣ በይግባኝ ባህር ዳር ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሄዶ ነበር፡፡

የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ይገባኙን ውድቅ በማድረጉ ለክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎትም አቤቱታ አቅርቦም ነበር፡፡ ሰበር ሰሚ ችሎቱም ጥያቄውን ውድቅ በማድረግ የክስ መመሥረቻ ጊዜ 15 ቀናት በመፍቀድ ለጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. ቀጠሮ ሰጥቶ ነበር፡፡ ተጠርጣሪዎቹም እስከዚያው ድረስ የዋስትና መብታቸው እንዲከበርላቸው ጠይቀው ነበር፡፡ በዚህ መሀል ዓቃቤ ሕግ የምርመራ መዝገቡን ሲመለከት፣ የተጠረጠሩት ‹‹ግድያው በተፈጸመበት ወቅት ተጠርጣሪዎቹ ኃላፊነታቸውን  ተወጥተዋል ወይስ አልተወጡም?›› በሚል ጭብጥ መሆኑን ጠቁሞ፣ ይኼ ደግሞ ዋስትና ስለማያስከለክል በዋስ ቢለቀቁ ተቃውሞ እንደሌለው አስተያየት በመስጠቱ፣ እያንዳንዳቸው በ10,000 ብር ዋስትና ከእስር ተፈትተዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...