Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናኢሕአዴግን ለማዋሀድ የሚደረገው የችኮላ እንቅስቃሴ አገር የመበተን አደጋ መጋረጡን ሕወሓት አስታወቀ

ኢሕአዴግን ለማዋሀድ የሚደረገው የችኮላ እንቅስቃሴ አገር የመበተን አደጋ መጋረጡን ሕወሓት አስታወቀ

ቀን:

የሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 26 እስከ ጥቅምት 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ፣ ኢሕአዴግን ለማወሀድ የሚደረገው የችኮላ እንቅስቃሴ አገርን የመተበን አደጋ መጋረጡን አስታወቀ፡፡

በአገሪቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግሮች እየተበራከቱ፣ ጥፋት በጥፋት ላይ እየተደራረበና የጥፋቱ ከፍተኛ መጠን በየቀኑ እየጨመረ ወደ ከፋ አገር የመበተን ደረጃ ደርሷል የሚለው የኮሚቴው መግለጫ፣ አደጋው ወደከፋ ደረጀ እንዲሄድ እያደረገ ካለው አንዱ ምክንያት የፓርቲ ውህደት ለመፈጸም እየተደረገ ያለው የችኮላ እንቅስቃሴ መሆን ገልጿል፡፡ ‹‹የፓርቲው ውህደት ጥያቄ በኢሕአዴግ ውስጥ በተለያየ ጊዜያት እየተነሳ የቆየና ይህንን ለማድረግ ሊሟሉ የሚገባቸው መሠረታዊ ጉዳዮችን እንዲታዩና በጥናት ላይ በመመሥረት እንዲመለሱ መግባባት ላይ የተደረሰበት ጉዳይ ነው፤›› የሚለው የማዕከላዊ ኮሚቴ መግላጫ፣ ሕወሓትም በመሠረተ ሐሳብ ደረጃ የተለየ እምነት እንዳልነበረው ጠቁሟል፡፡

ሆኖም ውህደቱን ለማድረግ በሁሉም መሠረታዊ የመስመር ጥያቄዎች፣ ፕሮግራሞች፣ ስትራቴጂ ወደ አንድ የሚያስተሳስር አመለካከትና እምነት በሁሉም እህት ድርጅቶች ሲፈጠር ብቻ መተግበር እንደሚችል የጠቆመው የኮሚቴው መግለጫ፣ አንድ ሊያደርግ የሚችል የጋራ አመለካከትና የተግባር አንድነት ሳይኖር አንድ ድርጅት እንደ ድርጅት ህልውና ሊኖረው እንደማይቻል ገልጿል፡፡

- Advertisement -

‹‹ከውህደት በፊት የሚዋሃድ አመለካከትንና እምነትን መለየት አለብን፤›› የሚለው መግለጫ፣ ‹‹ኢሕአዴግንና አገርን እየበተኑ ካሉት የተገዙ ደባል አመለካከቶች የሚለይ መስመር በጠራ መልኩ ሳይለይና ሳይቀመጥ ውህደትን ማሰብ አይቻልም፤›› ብሏል፡፡

በደፈረሰ አመለካከትና በአንድነት ሊሰምሩ በማይችሉ እሳትና ጅጭ አስተሳሰቦችን በተሸከመ ኢሕአዴግ ውህደት ቀርቶ በግንባርነት መቀጠል የማይችል የተበተነ ድርጅት መሆኑን የገለጸው የማዕከላዊ ኮሚቴ መግለጫ፣ ‹‹እንደዚህ ያለ የተበተነ ድርጅትን ወደ አንድ ፓርቲ ውህደት ይመጣል ብሎ ማሰብ በራሱ ድርጅቱን ከመበተን አልፎ አገርን የሚበትን ተግባር ነው፤›› ብሏል፡፡

በቅርቡ ከግንባሩ እምነትና መተዳደሪያ ደንብ ውጪ የፓርቲ ውህደት ለመፈጸም እየተደረገ ያለው ሩጫ ችግሩ እንዲባባስ የሚያደርግ ፀረ ዴሞክራሲያዊ አካሄድ እየሰፋ መምጣቱን ያሳያል ያለው ማዕከላዊ ኮሚቴው፣ የቅርፅ ውህደት ብቻ ሳይሆን በይዘትና በያዘው ፕሮግራሙ በመሠረቱ የተለወጠ አዲስ ፓርቲ ለመመሥረት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ በዚህም የኢትዮጵያ ሕዝቦች ኢሕአዴግ የያዘውን ፕሮግራም መሠረት አድርገው የሰጡት አገርን የመምራት ሥልጣን እንደሚያከትም ገልጿል፡፡ ‹‹አገርን ለመምራት ኃላፊነት ያልተሰጠው አዲስ ፓርቲ እንዲመሠረት ጥረት እየተደረገ ነው፤›› ያለው ኮሚቴው፣ እንዲህ ያለ አዲስ ፓርቲ በአገሪቱ ፖለቲካ ድርጅቶች የምዝገባ ሕግ ያላለፈ፣ በሕዝቦች ፈቃደኝነት በሥልጣን ላይ የመቆየትም ሆነ ሥልጣንን ለመያዝና ለመወዳደር የማይችል ሕገወጥ ድርጅት ነው ብሏል፡፡

‹‹በመሆኑም በውህደት ስም በፍፁም ፀረ ዴሞክራሲያዊ መንገድ አዲስ አሃዳዊ ድርጅት ሊመሠረት አይገባም፡፡ በሁሉም መለኪያዎች አንድ ፓርቲ ለመሆን የሚያስችል መነሻና ምክንያት በሌለበት ኢሕአዴግን አፍርሶ ሌላ ፓርቲ ለማቋቋም ማሰብ አገር የሚበትን ተግባር ነው፤›› ያለው የኮሚቴው መግለጫ፣ ኢሕአዴግ እንደ ግንባር ተደራጅቶ ችግሮችን በትግል እየፈታ አገር ሊመራ ይገባል ብሏል፡፡

አጋር ፓርቲዎችም በውህደት ስም እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ህልውናቸውን እንደሚያጠፋ ተገንዝበው፣ ወደ ኢሕአደግ ሙሉ አባልነት ገብተው በጋራ ትግልና ጥረት አገርን የሚያድን ተግባር እንዲፈጽሙ ማዕከላዊ ኮሚቴው ጥሪውን አቅርቧል፡፡ ሕወሓት እንዲህ ያለ አገርን የሚበትን ተግባር ውስጥ ገብቶ መንቦራጨቅ እንደማይፈልግም ገልጾ፣ መላው የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በውህደት ስም ኢሕአዴግን ለማፍረስ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ኃላፊነት በተሞላበት ተገቢውን ትግል እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው በመግለጫው የትግራይና የኤርትራ ሕዝቦች ለጋራ መብትና ጥቅም በጋራ የታገሉ ወንድማማች ሕዝቦች መሆናቸውን ገልጾ፣ የነበረውና አሁንም ያለው ዝምድናና መደጋገፍ ወደ ዘላቂ አስተማማኝ ደረጃ ለማድረስ ባለፈው ዓመት የተጀመረው የሰላም ጭላንጭል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...