Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሚኒስቴሩ ወደ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ ሠራተኞችን ማስረጃ የሚያጣራ ተቆጣጣሪ በአየር መንገድ መደበ

ሚኒስቴሩ ወደ ዓረብ አገሮች የሚሄዱ ሠራተኞችን ማስረጃ የሚያጣራ ተቆጣጣሪ በአየር መንገድ መደበ

ቀን:

በሐዘንና በተለያዩ ምክንያቶች የመጡ ሠራተኞች በአንድ ዓመት ውስጥ መመለስ ይችላሉ

የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 ድንጋጌዎችን ለማስከበርና ሥልጠና በመስጠት የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ወስደው ያለፉ የቤት ሠራተኞች፣ ወደ ዓረብ አገሮች ሲሄዱ ያቀረቡት ማስረጃ ሕጉን ያከበረ መሆን አለመሆኑን የሚያረጋግጡ ተቆጣጣሪ ሠራተኞችን በኢትዮጵያ አየር መንገድ መመደቡ ታወቀ፡፡

በአየር መንገዱ የተመደበው ሠራተኛ ቀደም ብሎ በአየርና በየብስ ኬላ በተመደቡ ሠራተኞች እንዝህላልነትና በተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች በመያዝ፣ የተመደቡበትን የመቆጣጠር ኃላፊነት የዘነጉ ሠራተኞችን ኃላፊነት በመውሰድ፣ ጥብቅ ቁጥጥር በማድረግ ተጓዦች ያቀረቡትን ማስረጃ በተገቢው ሁኔታ ፈትሾ መፍቀድና መከልከል የሚያስችል ሥልጣን ያለው መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

ዜጎች ክብራቸውና ደኅንነታቸው ተጠብቆ ባላቸው ችሎታና አቅም ሠርተው ተጠቃሚ እንዲሆኑ፣ ተግባራዊ በተደረገው አዋጅ ቁጥር 923/2008 ድንጋጌ መሠረት መተግበር እንዳለበት፣ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትሯ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረጉት ውይይትና ድርድር፣ ከመስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ቀድሞ የነበረው አሠራር መቅረቱና በአዲስ አሠራር መተካቱም አስታውቀዋል፡፡

ሚኒስትሯ ከባለድርሻ አካላት ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ዜጎች ወደ ተፈቀደላቸው የዓረብ አገሮች የሚያደርጉት ጉዞ፣ ሕጉን የጠበቀ ብቻ መሆን እንዳለበትና ተጓዥ ሠራተኞችም በሕጉ በተቀመጠው ድንጋጌ መሠረት፣ ተገቢውን ሥልጠና መውሰድ እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ ሥልጠና ሳይወስዱ በሕገወጥ መንገድ ለመውጣት የሚሞክሩትና ሕገወጥ ደላሎች ላይ ከዚህ በኋላ ጥብቅ ዕርምጃ እንደሚወሰድ ገልጸዋል፡፡

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንነ ከዓመታት በፊት ስለውጭ አገሮች ሥራ ሥምሪት ሕጋዊነት ያስተላለፉትን መመርያና ሚኒስትሯ ኤርጎጌ (ዶ/ር) ሰሞኑን በወሰዱት ቁርጠኛ አቋም ምክንያት፣ የኤምግሬሽን፣ ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲም የአየር ኬላዎች ወደ ዓረብ አገሮች በሚሄዱ ተጓዦች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር እንዲያደርጉ ያስተላለፈውን ትዕዛዝ፣ ከመስከረም 30 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በመሆኑም ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ለሥራ ለሚሄዱ ኢትዮጵያውን ሥልጠና በመስጠት፣ የብቃት ማረጋገጫ ፈተና ሰጥቶ ላለፉት ሰርተፊኬት እንደሚሰጥም ታውቋል፡፡ እነዚህ ተጓዦችም ወደ ዓረብ አገሮች ለመሄድ ሁሉን ነገር ጨርሰው አየር መንገድ ሲደርሱ፣ ሚኒስቴሩ በመደባቸው ተቆጣጣሪ ሠራተኞች የያዙት ማስረጃ ተረጋግጦ እንደሚሄዱም ተገልጿል፡፡

ዓረብ አገሮች ውስጥ በሥራ ላይ እያሉ በአገር ቤት ባጋጠማቸው ሐዘንና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ኢትዮጵያ መጥተው አንድ ዓመት የቆዩ ብቻ መመለስ የሚችሉ መሆኑም ተገልጿል፡፡ ሁለት ዓመት የቆዩት ግን እንደ ሁኔታው ቃለ መጠይቅ ተደርጎላቸው፣ የሚወሰን መሆኑን ኤጀንሲው ለኬላዎች ማስተባበሪያ አሳውቋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም በተለይ ወደ ዱባይ የሚሄዱ ሠራተኞች፣ ሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በአየር መንገድ በወከላቸው ሠራተኞች ተለይተው ያለፉ ብቻ እንዲወጡ መወሰኑም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...