Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለኬንያ ብስራት ለኢትዮጵያ ሥጋት የሆነው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ድል

ለኬንያ ብስራት ለኢትዮጵያ ሥጋት የሆነው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ድል

ቀን:

ኬንያውያን አትሌቶች ባለፈው ሳምንት መገባደጃ በድርብ ድል ተንበሽብሸዋል፡፡ ታዋቂው የማራቶን አውራ ኢልዩድ ኪፕቾጌ ታሪካዊ የተሰኘውን ውጤት በማስመዝገብ ዓለምን አስደምሟል፡፡ በሴቶችም ለ16 ዓመታት በእንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ ተይዞ የቆየው የርቀቱ ክብረወሰን በብሪጂድ ኮስጄይ አማካይነት መሰበሩ ለኬንያውያን ብስራት ሲሆን ለኢትዮጵያውያን ደግሞ ሥጋት ሆኗል፡፡

በርካታ በሳይንስ የተደገፉ ሙከራዎች ሲካሄዱበት የከረመውን ማራቶን ከሁለት ሰዓት በታች የመግባት ዕቅድ አሳክቷል፡፡ በሰው ልጅ ብቃት ከሁለት ሰዓት በታች ማራቶንን ማሸነፍ ከባድ እንደሆነ ሲነገር ቢቆይም፣ ኬንያዊ ኪፕቾጌ ግን 1፡ 59:40 በማስመዝገብ የታሪክ ባለቤት ለመሆን በቅቷል፡፡

የማይቻለውን በመቻሉ ዓለም ያወደሰው ኪፕቾጌ፣ ‹‹እንኳን ደስ ያለህ፣ አኮራኸን፣›› የሚል ሙገሳን የአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ኡሁሩ ኬንያታን ጨምሮ ከኬንያውያንና ከሌሎችም ዓለማት ተላልፎለታል፡፡

ለኬንያ ብስራት ለኢትዮጵያ ሥጋት የሆነው የሰሞኑ የአትሌቲክስ ድል

 

ይህ የኪፕቾጌ ድል ከጥቂት ሳምንታት በፊት በኢትዮጵያዊው ቀነኒሳ በቀለ የተሞከረውና ከዚህ ቀደም በክብረ ወሰንነት በዚሁ በኬንያው አትሌት ተይዞ የሚገኘውን ሰዓት ተገዳድሮት የነበረ መሆኑ፣ ምናልባትም ከሰሞኑ ኪፕቾጌ ያስመዘገበው አዲስ ክብረወሰን በቀነኒሳ ሲጠበቅ የነበረ በመሆኑ ሲነገር መቆየቱ የሚዘነጋ አይደለም፡፡

ቀነኒሳም ለኢትዮጵያም የወደፊት ተስፋ የሰነቀ አበረታች ውጤት በመሆኑ በዓለም መገናኛ ብዙኃን ዕውቅናም ተችሮት ነበር፡፡ ይሁንና የሰሞኑ የኪፕቾጌ ድል ግን ቀነኒሳን ጨምሮ ለሌሎችም አትዮጵያውያን አትሌቶች ሌላ ከባድ ፈተናም ሥጋትም የደቀነ፣ አቀበት ያህል ከባድ ሥራ ከፊት ለፊታቸው ጥሎባቸዋል፡፡

ምንም እንኳን የኪፕቾጌ አዲሱ ክብረ ወሰን በመደበኛው የዓለም አቀፍ አትሌቲክ ፌደሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) የውድድር መስክ ባይመዘገብም፣ ለኢትዮጵያውያን አትሌቶችና ለዘርፉ ሙያተኞች ፈተና መሆኑ ግን የማይካድ እውነታ ሆኗል፡፡

በተያያዘ ዜና በአሜሪካ ቺካጎ በተደረገው የሴቶች ማራቶን በኬንያዊቷ እንስት የተመዘገበው አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን በተመሳሳይ የሳምንቱ የዓለም ትልቅ መነጋገሪያ ሆኖ ተመዝግቧል፡፡

በብሪጂድ ኮስጄይ የተመዘገበው አዲስ የዓለም ክብረ ወሰን ከ16 ዓመት በፊት በእንግሊዛዊቷ ፓውላ ራድክሊፍ 2፡15:25 ሰዓትን በአንድ ደቂቃ ሃያ አንድ ሰከንድ ተሻሽሎ 2፡14:04 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ ኢትዮጵያውያኑ በሁለቱም ጾታ ኬንያውያኑን ተከትለው በመግባት የሁለተኛና የሦስተኛ ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁ መሆኑ ታውቋል፡፡

በኦስትሪያ ቪየና በተደረገውና ኪፕቾጌ ታሪክ በሠራበት ማራቶን ደጀን ደበላና አሰፋ መንግሥቱ ርቀቱን 2፡05. 46 እና 2፡05:48 ሲያጠናቅቁ፣ በችካጎው የሴቶች ማራቶን ደግሞ አባብል የሻነውና ገለቴ ቡርቃ 2፡20:51 እና 2፡20:55 በማጠናቀቅ የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ባለቤት መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኩባንያ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ባንኮች ውጤታማነት

የጠቅላላ ጉባኤ፣ የጥቆማና ምርጫ ኮሚቴ፣ የተቆጣጣሪ ቦርድ፣ የዳይሬክተሮች ቦርድና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...