በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ ሁሉም የመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የትምህርት ቤት ምገባ ተጀምሯል፡፡ ከቅደመ መደበኛ እስከ ስምንተኛ ክፍል የሚገኙ ሁሉንም ተማሪዎች ባቀፈው የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራም፣ 300 ሺሕ ተማሪዎች ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራሙን፣ በብሔራዊ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጥቅምት 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በመገኘት በይፋ ያስጀመሩት የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እንደተናገሩት፣ የተማሪዎች ምገባ ፕሮግራምም ሆነ የዩኒፎርምና የትምህርት መርጃ ቁሳቁስ ከዚህ በኋላም ቢሆን ተጠናክሮ ይቀጥላል፡፡
300 ሺሕ ተማሪዎችን ለመመገብ ከአሥር ሺሕ በላይ እናቶች በማኅበር ተደራጅተው መሰማራታቸው ይታወቃል፡፡