Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልበላሊበላ የሥነ ዕደ ጥበብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

በላሊበላ የሥነ ዕደ ጥበብ ፌስቲቫል ሊካሄድ ነው

ቀን:

ከ20 በላይ ኢንተርፕራይዞች ይሳተፋሉ

በቱሪስት መስህብነቷ፣ በዕደ ጥበብ ሥራዎቿና በውቅር አብያተ ክርስቲያናት በምትታወቀው ላሊበላ ከተማ፣ የዕደ ጥበብና የእጅ ሥራ ፌስቲቫል ሊካሄድ መሆኑን በግሪኒንግ ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክት አማካሪ አቶ ሮምሃ አልአዛር ገለጹ፡፡

አቶ ሮምሃ ለሪፖርተር እንደለጹት፣ ጥቅምት 15 እና 16 ቀን 2012 ዓ.ም. በሚካሄደው ፌስቲቫል፣ የቆዳ ምርቶች፣ የሸክላ ሥራዎች፣ ጌጣጌጦችና የተለያዩ የእጅ ሥራዎች ይቀርባሉ፡፡

ከ20 በላይ በኪነ ጥበብና በዕደ ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ፌስቲቫል፣ በላሊበላ በገጠርጌ ጐዳና የሚካሄድ ይሆናል፡፡ ፌስቲቫሉ በአካባቢው የዕደ ጥበብ ባለሙያዎች የተሠሩ የዕደ ጥበብ ሥራዎችን ለማስተዋወቅ ከማስቻሉም በተጨማሪ፣ የባለሙያዎችን ዕምቅ ችሎታ ለማውጣት ብሎም የገበያ ትስስር ለመፍጠር ዕድል እንደሚከፍት አቶ ሮምሃ ተናግረዋል፡፡

በላሊበላ ቱሪዝም ቢሮ የሚደገፈው የዕደ ጥበብ ፌስቲቫል የዕደ ጥበብ ሥራዎችን ለአገር ውስጥና ለውጭ ቱሪስቶች ለማስተዋወቅ እንደሚረዳም አክለዋል፡፡

በአውሮፓ ኅብረት ድጋፍ በኢትዮጵያ የንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ በፕሪሳይስ ኮንሰልት ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበርና በስሎቫኒያ አይኤንኦኤ ትብብር የሚከናወነው ‹‹ግሪኒንግ ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ›› ፕሮጀክት አካል የሆነው ፌስቲቫል፣ በዘርፉ ዕድገት ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ችግሮችን ለመፍታት ያስችላል፡፡

የግሪኒንግ ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክት በቆዳ፣ በጨርቃ ጨርቅና በዕደ ጥበብ ዘርፍ እገዛ እያደረገ ሲሆን፣ በዕደ ጥበብ ዘርፍ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በላሊበላ ይሠራል፡፡

ፕሮጀክቱ በላሊበላ በዕደ ጥበብ ዘርፍ ለተሰማሩ ባለሙያዎች የሙያ ማሻሻያ ሥልጠና መስጠቱን፣ ከበግ ፀጉርና ከተለያዩ ግብዓቶች የሚሠሩ የዕደ ጥበብ ውጤቶችን ማስተዋወቁን እንዲሁም ንድፍና የገበያ ትስስር ላይ እየሠራ መሆኑን አቶ ሮምሃ ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከዕደ ጥበብ ዘርፍ ገቢ ለማግኘት የሚያስችል አቅም ቢኖራትም፣ ከዘርፉ ይህንንም ያህል ተጠቃሚ አልሆነችም፡፡ የፕሮጀክቱ አካል የሆነው ፌስቲቫልም በዕደ ጥበብ ዘርፍ የተሰማሩ ግለሰቦችና ኢንተርፕራይዞችን አቅም በማሳየት የገበያ ትስስርን ይፈጥራል ተብሎ ተስፋ ተጥሎበታል፡፡

በኢትዮጵያ የዕደ ጥበብ ዘርፍ ከጐጆ ኢንዱስትሪ የዘለለ አይደለም፡፡ በመሆኑም ትክክለኛ መረጃ፣ ምን ያህል ግለሰቦችም ሆኑ ኢንተርፕራይዞች በዘርፉ እንደተሰማሩ፣ የምርቶቹ ብዛትና ዓይነት እንዲሁም ለሥራ ፈጠራ ያላቸው አስተዋጽኦ ተደራጅቶ አይገኝም፡፡

የፌዴራል ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ኤጀንሲ መረጃ እንደሚያሳየው፣ ዘርፉ ከ1.5 ሚሊዮን እስከ ሁለት ሚሊዮን ያህል የሥራ ዕድል እንደሚፈጥር ይገምታል፡፡

በኢትዮጵያ የዕደ ጥበብ ሥራ ከተጀመረ ከሺሕ ዓመት በላይ የተቆጠረ ቢሆንም፣ የዕደ ጥበብ ውጤቶችን ለውጭ ገበያ ማቅረቡ ግን ብዙም አልተሠራበትም፡፡ አንዳንድ ነጋዴዎች ከጀርመን፣ ከጣልያን፣ ከእንግሊዝና ፈረንሳይ ጋር ትስስር ቢፈጥሩም፣ የንግድ ልውውጡ አነስተኛ ነው፡፡

በዘርፉ ንግድ የተሰማሩትም በወር የሚያስገቡት ውጭ ምንዛሪ ከሌላው ዘርፍ ሲነጻጸር አነስተኛ ነው፡፡ ለዚህ አንዱ ምክንያት ደግሞ ኢትዮጵያ በርካታ የዕደ ጥበብ ዓይነቶች ቢኖርዋትም በደንብ አለመተዋወቃቸውና የገበያ ትስስር አለመፈጠሩ ነው፡፡

ዕደ ጥበብና እጅ ሥራ ከፍተኛ የውጭ ምንዛሪ የሚያስገኙ ቢሆንም፣ በኢትዮጵያ አላደገም፡፡ የግሪኒንግ ኢትዮጵያ ማኑፋክቸሪንግ ፕሮጀክትም በዕደ ጥበብና እጅ ሥራ የካበቱ ልምዶች ባሉበት ላሊበላ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ አንዱ የገበያ ትስስር መፍጠር ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...