Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበአፍሪካ ሕፃናት አሳታፊ ጦርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

በአፍሪካ ሕፃናት አሳታፊ ጦርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ

ቀን:

በሔለን ተስፋዬ

በአፍሪካ ሕፃናት አሳታፊ ጦርነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መምጣቱን የአፍሪካን ቻይልድ ፖሊሲ ፎረምና ሴቭ ዘ ችልድረን ሕፃናትና ግጭትን አስመልክተው ባዘጋጁት መድረክ ተገለጸ፡፡

ጥቅምት 4 ቀን 2012 ዓ.ም. በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የስብሰባ ማዕከል በተደረገው ኮንፍረንስ የተገኙት የአፍሪካን ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም ዳይሬክተር አሰፋ በቀለ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ በአፍሪካ የሚታየው ሕፃናት አሳታፊ ጦርነትም አኅጉሪቷ ለሕፃናት አደገኛ ከሆኑ ሥፍራዎች ውስጥ እንድትመደብ አድርጓታል፡፡

- Advertisement -

ዳይሬክተሩ እንደሚሉት፣ በጦርነት ምክንያት በአፍሪካ ሕፃናት ላይ የሚደርሰው ጉዳት የቀጠለ ሲሆን፣ ከጊዜ ወደ ጊዜም እየተባባሰ መጥቷል፡፡ ሆኖም የአፍሪካ መሪዎች የሕፃናትን ከአስከፊ ችግርና ሰቆቃ መታደግ ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

በአፍሪካ ለሕፃናት ጥበቃ ቢኖርም፣ የሚሰጠው ጥበቃ እጅግ አናሳና አዝጋሚ ነው፡፡ ችግሩን የሚፈጥሩ የጦር ወንጀለኞችና ዘግናኝ የመብት ጥሰቶች የሚያደርሱ አካላት ሕግ ፊት አለመቅረባቸው ችግሩን እንዳባባሰው አክለዋል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2018 ባወጣው ሪፖርት፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ፣ ሊቢያ መብት ጥሰት ከሚፈጸምባቸው አገሮች መካከል ከቀዳሚዎቹ እንደሚገኙ አስፍሯል፡፡ 152 ሚሊዮን የአፍሪካ ሕፃናት ወይም ከአራት የአፍሪካ ሕፃናት ውስጥ አንዱ በጦርነት ቀጣና ውስጥ እንደሚኖርም መረጃዎች ያሳያሉ፡፡

ከዓለም በግጭት ቀጣና ውስጥ ከሚኖሩት ሕፃናት አንድ አምስተኛው በአፍሪካ ውስጥ እንደሚገኙና ከእነዚህ ሕፃናት ውስጥ ከአንድ ሦስተኛው በላይ ወሲባዊ ጥቃቶችን እንደሚፈጽሙ በአፍሪካን ቻይልድ ፖሊሲ ፎረም የታተመው ዘ ዋር ኦን አፍሪካንስ ችልድረን ያሳያል፡፡

 እ.ኤ.አ. በታኅሣሥ 2013 ላይ 19 ሺሕ የሚሆኙ ሕፃናት በደቡብ ሱዳን ውስጥ በሚገኙ ታጣቂ ኃይሎች መመልመላቸውንም በሪፖርቱ ሰፍሯል፡፡

ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ ለአፍሪከ ኅብረትና ለአባል አገሮች በአኅጉሪቱ አንዳንድ አገሮች የተከፈቱ በርካታ ጦርነቶችን እንዲያስቆሙና በግጭት ቀጣናዎች ውስጥ የሚኖሩ ሕፃናትን ደኅንነት እንዲያስጠብቁ ያሳሰቡት የሴቭ ዘ ችልድረን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሄሌና ታይቤል ናቸው፡፡

ግጭት በሚበዛባቸው አካባቢዎች አጣብቂኝ ውስጥ የገቡ ሕፃናት ፍትሕ፣ የደኅንነት ዋስትናና ተጨባጭ የሆነ የመልሶ ማገገሚያ ዕገዛ እንዲደረግላቸው እንፈልጋለን ሲሉም ሥራ አስፈጻሚዋ ገልጸዋል፡፡

የአፍሪካ መንግሥታት ሕፃናትና ታዳጊዎች በአስገዳጅ የትጥቅ ትግል ምልመላ፣ በአፈና፣ በአስገድዶ መድፈርና በወሲባዊ ጥቃቶች ተጠቂ እንዳይሆኑ ለማድረግና በትምህርት ቤቶች፣ በሆስፒታሎችና በሰብዓዊ ዕርዳታ መስጫ ተቋማት ላይ የሚደርሱ ጥቃቶችን ማስቆም ይጠበቅባቸዋል ሲሉም ሄሌና ተናግረዋል፡፡

ሴቭ  ዘ ችልድረን ‹‹Stop the War on Children›› በሚል ርዕሰ በ2010 ባወጣው ሪፖርት፣ ከአራት አፍሪካውያን ሕፃናት አንዱ በግጭት ቀጣና ውስጥ ይኖራል፣ በሕፃናት ላይ የሚደርሱት ከባድ አካላዊ፣ ሥነ ልቦናዊ ጥሰቶች ደግሞ በሦስት እጥፍ መጨመራቸውን አሳይቷል፡፡

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ኅብረትና አባል አገሮች በአፍሪካ ያሉ በርካታ ጦርነቶችን እንዲያስቆሙና በግጭት ውስጥ የሚኖሩ ሕፃናትን ደኅንነት ለማስጠበቅ ኃላፊነታቸውን እንዲወጡም ዶ/ር አሰፋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በአፍሪካ የምግብ ዋስትና ማጣት፣ የአየር ንብረት ለውጥ የመልካም አስተዳዳር ችግር፣ የሕግ የበላይነት አለመከበር፣ ሙስና፣ የጎሳና የብሔር ግጭት የመሳሰሉት ሕፃናት ላይ የሕግ ጥሰት እንዲፈጸም አስተዋጽኦ ማድረጉን አስረድተዋል፡፡

የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ ሽብርተኝነት የእርስ በርስ ጦርነት፣ የሕፃናት አፈና፣ ግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ፣ ለአስገድዶ መድፈርና ለሕፃናት ሕገወጥ ዝውውር የተመቻቸ ሁኔታ መፍጠሩን ገልጸው፣ በኢትዮጵያ አሁን እየተካሄደ ያለው የዘርና የጎሳ ግጭት በዚሁ ከቀጠለ፣ እንደ ሌሎች የአፍሪካ አገሮች ቀውስ ውስጥ መግባት አይቀሬ ነው ብለዋል፡፡

በአፍሪካ አሁን እየተከሰተ ያለውን የእርስ በእርስ ጦርነትና ሌሎች ችግሮችን መፍታት መንግሥታት ላይ የሚጣል ብቻ ባለመሆኑ፣ ሁሉም ማኅበረሰብ ችግሩን ለመፍታት መጣር አለበት ሲሉ አሳስበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...