Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየዓለም ሚቲዎሮሎጂ የአፍሪካ ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ተከፈተ

የዓለም ሚቲዎሮሎጂ የአፍሪካ ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ተከፈተ

ቀን:

ስምንት አገሮች ታጭተው ነበር

በሔለን ተስፋዬ

የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት (ዓሚድ) የአፍሪካ ቅርንጫፍ በአዲስ አበባ ተከፈተ፡፡ የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት በኢትዮጵያ እንዲከፈት የተወሰነው አዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት መቀመጫና የዲፕሎማት መኖሪያ በመሆኗ በርካታ ሥራዎችን ለማከናወን ስለምትመች ነው ያሉት የብሔራዊ ሜትሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ፈጠነ ተሾመ ናቸው፡፡

- Advertisement -

የዓሚድ የአፍሪካ ጽሕፈት ቤት በአዲስ አበባ መከፈቱ ለኢትዮጵያ የሜትሮሎጂ ኤጀንሲ የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር ለማድረግ ከፍተኛ ጠቀሜታ ይኖረዋል ተብሏል፡፡ ኢትዮጵያ የተመረጠችው ለዕጩነት ከቀረቡ ከስምንት የአፍሪካ አገሮች መካከል እንደሆነም አቶ ፈጠነ ገልጸዋል፡፡

አኅጉራዊው ሚቲዎሮሎጂካል ጽሕፈት ቤት መቀመጫ አገርና የዓለም የሚቲዎሮሎጂ ድርጅት ቀደም ሲል ከነበረው ከጄኔቫ ስዊዘርላንድ አዲስ አበባ እንዲሆን መወሰኑ ይታወቃል፡፡

ይህም የዓሚድ አባል አገሮች አኅጉራዊ ግንባታ ሥራዎች ላይ ድጋፍ ለማድረግ፣ በአየር ሁኔታና ፀባይ ትንበያ አገልግሎት ዙሪያ ተገቢውን ድጋፍ ለማድረግ፣ በአየር ንብረት ዙሪያ ትኩረት አድርገው ለሚሠሩ ተቋማት አስፈላጊውን ድጋፍ ለመስጠት እንደሚያስችል የዓሚድ ዋና ጸሐፊ ፒተር ታላስ ተናግረዋል፡፡

ዓሚድ፣ የአፍሪካ አኅጉር ጽሕፈት ቤት መቀመጫ አዲስ አበባ እንዲሆን ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር በሐምሌ ወር 2011 ዓ.ም. ነበር የተፈራረመው፡፡ በዚህም እንደ አፍሪካ ኅብረት ከመሳሰሉ ድርጅቶች ጋር ግንኙነቱን በማጠናከርና በቅርበት በመሥራት አባል አገሮችን ለመደገፍ እንደሚያስችል አቶ ፈጠነ አስረድተዋል፡፡

አቶ ፈጠነ፣ በአፍሪካ አኅጉር የሚቲዎሮሎጂ ጽሕፈት ቤቱ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ይሆናል ብለዋል፡፡

እያደገ የመጣውን የአየር ሁኔታና ጠባይ ትንተና ለፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት የጎላ ሚና እንደሚኖረው ይታመናል ያሉት አቶ ፈጠነ፣ እየዘመነ ከመጣው የትራንስፖርትና የግንባታ ዘርፍ አኳያ፣ የግብርና ምርትና የታዳሽ ኃይል አቅርቦትን ለመጨመር ያለው መነሳሳት፣ በአየር ሁኔታና ፀባይ መረጃ ላይ ይበልጥ መተማመን እንዲኖር ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

የአፍሪካ አኅጉር የሚቲዎሮሎጂ ጽሕፈት ቤት ወደ ኢትዮጵያ መዛወሩ ከዓሚድ ከሚገኘው ድጋፍ በቅርበት ተጠቃሚ ለመሆንም የጎላ ፋይዳ ይኖረዋል፡፡ ይህም የቅድመ ማስጠንቀቂያ ሥርዓቶችን ለማጠናከርና ለማሻሻል፣ የአየር ሁኔታና ጠባይ አስተዳደርን የተቀናጀ ለማድረግ፣ የፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎች ስምረት እንዲሁም ለማኅበራዊ ኢኮኖሚ ዕድገት የሚኖረውን አስተዋጽኦ ለማሳደግ ለአኅጉሪቱ እንደሚበጅ ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...