ለሥነ ጽሑፍና ለሥነ ጽሕፈት አዝመራ ይበልታና ይሁንታን የሚያጎናፅፈው ሆሄ የሥነ ጽሑፍ ሽልማት ዓመታዊ መድረኩን ለሦስተኛ ጊዜ በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. አካሂዷል፡፡ የሽልማት ሥነ ሥርዓቱ የተከፈተው ታዋቂው ገጣሚና የሥነ ጽሑፍ መምህር የነበረው ደበበ ሰይፉ “የአክሱም ጫፍ አቁማዳ” ግጥምን በሙዚቃዊ ቴአትር በመዝሙር፣ ግጥም፣ ቀረርቶ፣ ፉከራ፣ ዳንስና ሰርከስ አቀናጅቶ በማቅረብ ነው፡፡ ፎቶዎቹ የመሰናዶውን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡