Tuesday, July 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየጤና አደጋዎችን ለመታደግ ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዙ 300 ሞተር ሳይክሎች ርክክብ...

የጤና አደጋዎችን ለመታደግ ከ43 ሚሊዮን ብር በላይ የተገዙ 300 ሞተር ሳይክሎች ርክክብ ተከናወነ

ቀን:

የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ድንገተኛ የማኅበረሰብ ጤና አደጋዎችን የመከላከልና ምላሽ ለመስጠት፣ ተደራሽ ያልሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ ለማድረግና መኪና በማይገባባቸውና የትራንስፖርት ችግር ባሉባቸው ወረዳዎች ለተመደቡት ድንገተኛ የኅብረተሰብ ጤና አደጋ ባለሙያዎች ከ43 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የገዛቸውን 300 ሞተር ሳይክሎች አስረከበ፡፡

በኢንስቲትዩቱ ቅጥር ግቢ ጥቅምት 12 ቀን 2012 ዓ.ም. በተከናወነው ሥነ ሥርዓት ላይ ሞተር ሳይክሎቹን ያስረከቡት፣ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ኤባ አባተ (ዶ/ር) ሲሆኑ፣ የተረከቡት ደግሞ የየክልሉ ጤና ቢሮዎች ኃላፊዎች ናቸው፡፡

ዋና ዳይሬክተሩ፣ ሞተሮቹ ድንገተኛ የማኅበረሰብ አደጋዎችን አስመልክቶ የሚከናወነውን የቅኝት ሥራ በተጠናከረ ለማከናወንና ተደራሽ ያልሆኑ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ተደራሽ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ባለሙያዎቹ የተሰጣቸውን ሞተር ሳይክሎች ለተጠቀሱት ተግባራት ብቻ በማዋል በእንክብካቤ እንዲይዟቸው፣ ይህ ዓይነቱ እገዛና ድጋፍ ቀጣይነት እንዳለውም ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

ዶ/ር በየነ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ከ1000 በላይ ወረዳዎች ያሉ ቢሆንም፣ ለመጀመርያ ጊዜ በእነዚህ ሞተር ሳይክሎች አማካይነት ቢያንስ 300 ወረዳዎችን ለመድረስ ታስኗል፡፡

ወረርሽኝ መከሰቱን አስመልክቶ ከኅብረተሰቡ ጭምጭምታ ሲሰማ ቦታው ድረስ ሄዶ ለማረጋገጥና በዚህም ተገቢውን ምላሽ ለመስጠት በትራንስፖርት እጦት ሳቢያ ብዙ ጊዜ ችግር እንደሚፈጠር፣ በዚህም አጋጣሚ ወረርሽኙ እንደሚስፋፋና ማኅበረሰቡም ለወረርሽኙና ከዛም አልፎ ለህልፈተ ሕይወት እንደሚጋለጥ ገልጸዋል፡፡

ይህን ችግር በዘላቂነት ለመፍታት የትራንስፖርት ሥርዓቱ እንደ አገር መስተካከል እንደሚኖርበት ጠቁመው፣ በሞተር ሳይክሎች መጠቀምን እንደ አማራጭ መፍትሔ ማየታቸውን አመልክተዋል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት በቀጣዩ አምስት ዓመታት ውስጥ ከሦስት ቢሊዮን በላይ ሆነውን የዓለም ሕዝብ ተጠቃሚ የሚያደርግ ‹‹ዘ ትራፕልስ ታርጌትስ›› የሚባል ዕቅድ አውጥቶ ወደ ሥራ ገብቷል፡፡ በዕቅዱ መሠረት የመጀመርያው ግብ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሆነውን የዓለም ሕዝብ አጠቃላይ የጤና ሽፋን እንዲያገኝ ማድረግ ነው፡፡ ሁለተኛው ግብ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሚሆነውን የዓለም ማኅበረሰብ ከኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከል ሲሆን፣ ሦስተኛው ግብ ደግሞ ከአንድ ቢሊዮን በላይ የሚሆነውን የዓለም ማኅበረሰብ ጤና ማሻሻል መሆኑን መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...