Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናኢትዮጵያ በአሥር ዓመታት የኑክሌር ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል ተዘጋጅታለች

ኢትዮጵያ በአሥር ዓመታት የኑክሌር ኃይል ጥቅም ላይ ለማዋል ተዘጋጅታለች

ቀን:

ባለፈው ሳምንት በሩሲያ ሶቺ ከተማ በተካሄደው የሩሲያ አፍሪካ የኢኮኖሚ ፎረም ወቅት፣ ኢትዮጵያ የኑክሌር ኃይልን ለሰላማዊ ዓላማ ማዋል የምትችልበትን መበደኛ ስምምነት ከሩሲያ ጋር ተፈራረመች፡፡ የስምምነቱ መፈረም በመጪዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ በኢትዮጵያ ኑክሌርን ጥቅም ላይ ለማዋል ያስችላል ተብሏል፡፡

የሁለቱ አገሮች የበይነ መንግሥታት ስምምነት በኢትዮጵያ የኑክሌር መሠረተ ልማትን ከመገንባት ባሻገር፣ የኑክሌር ማብላያ ማዕከልንና የኑክሌር ዝቃጮችን ክምችትና አወጋገድን የተመለከቱ ነጥቦችንም አካቷል፡፡

የኑክሌርና የጨረራ ደኅንነት መቆጣጠሪያ እንዲሁም የኑክሌር ቁስ አካላትን ደኅንነት የመጠበቅ ሥራዎች፣ የጨረራ ምንጮችን የኑክሌርና የራዲዮ አክቲቭ ቁሶችን የማከማቻ ፋሲሊቲዎችን የተመለከቱና ሌሎችም ጉዳዮች በስምምነቱ ተካተዋል፡፡ በመሆኑም በሁለቱ መንግሥታት መካከል የጋራ የትብብር ኮሚቴ እንዲቋቋም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የተመረጡ ፕሮጀክቶችንና ሳይንሳዊ ጥናቶችን ማካሄድ የሚያስችሉ ሥራዎች፣ የኑክሌር ቁሳቁስ፣ ማቴሪያል፣ እንዲሁም አካላትን ለማቅረብ የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎችን ጨምሮ በረጅም ጊዜ ሒደት ኢትዮጵያ የራሷን የኑክሌር ሳይንስና ቴክሎጂ ማዕከል መመሥረት የምትችልባቸውን ይዘቶች ስምምነቱ አካቷል፡፡

የኑክሌር ኃይል ስምምነቱ 3‚000 ሜጋ ዋት የኤሌክትሪክ ኃይል ከማመንጨት በተጨማሪ፣ ለሕክምናና ለግብርና ዘርፎችም ጥቅም እንደሚሰጥ ይጠበቃል፡፡ በኑክሌር የካንሰር ሕክምና አገልግሎት ከሚጠበቁት ውስጥ አንዱ ነው፡፡ ይህ ሁሉ በመጪዎቹ አሥር ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ እንደሚደረግ የኢትዮጵያ መንግሥት ይፋ ማድረጉ ይታወቃል፡፡

ከሁለት ዓመታት በፊት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ እንዲሁም በሩሲያ መንግሥት ሥር በሚተዳደረውና ሮሳቶም በተሰኘው የኑክሌር ኃይል ኮርፖሬሽን ኃላፊዎች መካከል ስምምነቱ በድጋሚ በሩሲያ ተፈርሟል፡፡ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ በኩል ስምምነቱን ሲፈርሙ፣ በሮሳቶም በኩል የኩባንያው ዳይሬክተር ጄኔራል አሌክሲይ ሊክሃቼቭ ፊርማቸውን አኑረዋል፡፡ እ.ኤ.አ. በ2017 የተካሄደውን የመግባቢያ ስምምነት ወደ ተግባር ለመቀየር የሚያስችል የትብብር ስምምነት እንደሆነ ተገልጿል፡፡  

የጨረራና የኑክሌር ቴክኖሎጂ ደኅንነት እንዲረጋገጥ፣ እንዲጠበቅና ለሰላማዊ አገልግሎት እንዲውል የማድረግ ኃላፊነትን ጨምሮ ሕዝብና አካባቢ ወደፊት ሊፈጠር ከሚችል የጨረራ ጠንቅ ለመከላከል የሚሠራ፣ የኢትዮጵያ የጨረራና ኑክሌር ቁጥጥር ባለሥልጣን የተሰኘው ተቋም እንደ ገና እንደ አዲስ እንዲደራጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ደንብ እየተዘጋጀለት ይገኛል፡፡ ይህ ተቋም የራዲዮ አክቲቭ ቁሶችና ተዛማጅ ተግባራት ላይ የሚያከናውናቸውን የቁጥጥር ሥራዎች የሚደግፉ፣ የምርምርና የልማት ሥራዎችንም የማካሄድ ኃላፊነት እንደሚኖረው ይጠበቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...