Friday, March 24, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር የሰባት ዓመታት ፅኑ እስራት ተፈረደበት

የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር የሰባት ዓመታት ፅኑ እስራት ተፈረደበት

ቀን:

በዕንቁ መጽሔት ምክንያት ከአምስት ዓመታት በፊት ከግብር ጋር በተያያዘ ክስ ተመሥርቶበት የነበረው የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር አቶ ፍቃዱ ማኅተመ ወርቅ፣ በሰባት ዓመታ ፅኑ እስራትና በ7,000 ብር እንዲቀጣ ውሳኔ ተሰጠ፡፡

የዕንቁ መጽሔት አሳታሚ ዓለማየሁ የኅትመት ማስታወቂያ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር፣ ‹‹ወንጀል እንዲፈጸም በመርዳትና በማበረታታት›› የሚል ክስ ተመሥርቶበት የነበረው አቶ ፍቃዱ፣ የቅጣት ውሳኔ የተላለፈበት በፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት ስምንተኛው ወንጀል ችሎት ነው፡፡

አቶ ፍቃዱ በተለይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣን ላይ ከወጡ በኋላ፣ እስከታሰረበት ዕለት ጥቅምት 11 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ የግዮን መጽሔት ማኔጂንግ ኤዲተር ሆኖ ይሠራ ነበር፡፡ አሁን ለቅጣት የዳረገውን ከገቢ ግብር ጋር የተያያዘው ክስ፣ እንደ ሌሎቹ በርካታ ተከሳሾች ክሱ የሚቋረጥለት መስሎት እንደነበረ ከመታሰሩ በፊት ለሪፖርተር ገልጿል፡፡ የግብር አዋጅ ቁጥር 268/94 አንቀጽ 101 ድንጋጌን መተላለፉን ጠቅሶ፣ በወቅቱ የኢትዮጵያ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለሥልጣን ዓቃቤ ሕግ የመሠረተበት ክስ፣ እንደ አዲስ አገርሽቶ ጥፋተኛ አስብሎታል፡፡

የዕንቁ መጽሔት አሳታሚ ከ2002 ዓ.ም. እስከ ከ2006 ዓ.ም. ድረስ ባለው የግብር ዘመን፣ ከሽያጭና ከማስታወቂያ ያገኝ ከነበረው የገቢ ትርፍ 629,140 ብር ለባለሥልጣኑ መክፈል ሲገባው ባለመክፈሉ፣ ክስ መመሥረቱም ታውቋል፡፡ በመሆኑም አቶ ፍቃዱ ጥፋተኛ በመባሉ የተጠቀሰውን የእስር ጊዜና የገንዘብ ቅጣት ተወስኖበት ወደ ማረሚያ ቤት ተልኳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላወራህ የፈለኩት ክቡር...

የትግራይ ክልል የሽግግር አስተዳደር ምሥረታና የሰላም ስምምነቱ ሒደት

በትግራይ ክልል ጊዜያዊ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት ደፋ ቀና እየተባለ...

ጥራዝ ነጠቅነት!

ከሜክሲኮ ወደ ጀሞ እየሄድን ነው፡፡ የተሳፈርንበት አሮጌ ሚኒባስ ታክሲ...