Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናእነ አቶ በረከት ስምዖን የተመሠረተባቸውን ክስ ተከላከሉ ተባሉ

እነ አቶ በረከት ስምዖን የተመሠረተባቸውን ክስ ተከላከሉ ተባሉ

ቀን:

የሙስና ወንጀል ክስ ተመሥርቶባቸው ላለፉት ሰባት ወራት ሲከራከሩ የቆዩት እነ አቶ በረከት ስምዖን፣ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ምስክሮቹንና የሰነድ ማስረጃውን ማቅረቡ ተገልጾ እንዲከላከሉ ብይን ተሰጠ፡፡

በጥረት ኮርፖሬት ድርጅቶች ሥር ከሚገኙ ድርጅቶች በዳሽን ቢራና ዴቬንቱስ ቴክኖሎጂ ጋር በተያያዘ፣ ከፍተኛ የሆነ ሙስና ፈጽመዋል በማለት የአማራ ክልል ዓቃቤ ሕግ በአቶ በረከት ስምዖን፣ አቶ ታደሰ ካሳ (ጥንቅሹ) እና አቶ ዳንኤል ግዛው (የዴቬንቱስ ቴክኖሎጂ ባለድርሻ) ላይ ሚያዝያ 7 ቀን 2011 ዓ.ም. ክስ መመሥረቱ ይታወሳል፡፡

ክሱን ሲሰማና ሲመረምር የከረመው የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጥቅምት 21 ቀን 2012 ዓ.ም. በዋለው ችሎት፣ የቀረበባቸውን ክስ በመስቀለኛ ጥያቄ ማስተባበል አለመቻላቸውን በመግለጽ እንዲከላከሉ ብይን ሰጥቷል፡፡

በመሆኑም ተከሳሾቹ የመከላከያ ምስክሮቻቸውን ለኅዳር 24 ቀን 2012 ዓ.ም. እንዲያቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...

ግለሰብ ነጋዴዎችን በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ለማድረግ ያለመው ረቂቅ አዋጅ ተከለሰ

በምትኩ የንግድ ተቋማት በአስገዳጅነት የንግድ ምክር ቤት አባል ይሆናሉ...