Monday, April 15, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

በማኑፋክቸሪንግ በቴክኖሎጂ ንግድ ትርዒት ከ50 በላይ የውጭ አምራቾች ታድመዋል

ተዛማጅ ፅሁፎች

የኢዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የሚያዘጋጀው ዓለም አቀፉ የማኑፋክቸሪንግና የቴክኖሎጂ ንግድ ትርዒት ከ120 በላይ አምራቾችን በማሳተፍ ለሦስተኛ ጊዜ በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል እየተካሄደ ነው፡፡

በርካታ የአፍሪካ ነጋዴዎች በተሳተፉበት ዓውደ ርዕይ፣ ከ50 በላይ የሚሆኑት ከውጭ የመጡ አምራቾች እንደሆኑ የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ወ/ሮ መሰንበት ሸንቁጥ ገልጸዋል፡፡ ዓውድ ርዕዩ ከጥቅምት 20 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ጥቅምት 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ድረስ ክፍት ሆኖ እንደሚቆይ ተገልጿል፡፡

‹‹ዓለም የደረሰበት ደረጃ ለመድረስ አገራችን በቴክኖሎጂ የተደገፈ አሠራርና አስተሳሰብ ያስፈልጋታል፤›› በማለት ዓውደ ርዕዩም አገር ውስጥ ያሉ አምራቾች ራሳቸውን ከውጭ አምራቾች ጋር በማነጻጸር የሚገኙበትን ደረጃ የሚለኩበት መድረክ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የዓውድ ርዕዩ ዋና ዓላማ ማሻሻጥ ብቻ እንዳልሆነ የገለጹት ፕሬዚዳንቷ፣ የቴክኖሎጂና የልምድ ልውውጥ ከመፍጠር ባሻገር የቢዝነስ ግንኙነትን ለማጠናከር እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

በቅርቡ ኢትዮጵያን ጨምሮ በአብዛኞቹ የአፍሪካ ኅብረት አባል አገሮች የተፈረመውን ነፃ የንግድ ቀጣና ስምምነት ያወሱት ወ/ሮ መሰንበት፣ ‹‹የትኛውም የአፍሪካ አገር የሚኖረውን የንግድ ልውውጥ ከታክስ ነፃ ማስገባት በመቻሉ ምክንያት የእኛ አገር አምራቾች ከሌሎች ጋር መወዳደር የሚችሉበትን አጋጣሚ ይፈጥራል፡፡ በተጨማሪም የአገር ውስጥ አምራቾች ጥራቱን የጠበቀና ፍላጎትን የሚያሟላ ዕቃ ለማቅረብ ዝግጁነታቸውን የሚያዩበት ነው፤›› በማለት ገልጸዋል፡፡

በዓውደ ርዕዩ ላይ ከተገኙ የውጭ አገር አምራቾች መካከል የጋና አምራቾች በስፋት ምርቶቻቸውን ይዘው የቀረቡ ሲሆን፣ ባህላዊ አልባሳቶችና የውበት መጠበቂያዎች ካቀረቧቸው መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ ከአገር ውስጥ አቅራቢዎች መካከል ደግሞ የንፅህና መጠበቂያ አምራቾች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃ አምራቾች፣ በቆዳ ምርቶች ላይ የሚሳተፉ አካላት፣ ኢንዱስትሪ ዘርፉ ላይ የተሰማሩ ኩባንያዎች እንዲሁም በቡና ዘርፉ ላይ ያሉ ነጋዴዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች