Wednesday, March 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የታሪክ ጓዳ

ትኩስ ፅሁፎች

በአዲስ አበባ ከተማ ከሚገኙት ታሪካዊ ሐውልቶች አንዱ አራዳ ጊዮርጊስ የሚገኘው የዳግማዊ ምኒልክ አባ ዳኘው ሐውልት ነው፡፡ ከ89 ዓመት (ዘጠና ፈሪ)  በፊት በወርኃ ጥቅምት የተመረቀውን የንጉሠ ነገሥቱን ኪነ ቅርፅ ያሠሩት ልጃቸው ንግሥተ ነገሥታት ዘውዲቱ ናቸው፡፡ የሐውልቱ ነዳፊ ጀርመናዊ አርክቴክት ሀርቴል ስፔንግለር ሲሆን በነሐስ የተቀረፀውምጀርመን ሀገር ነው፡፡  ንግሥቲቱ በማረፋቸው ምክንያት የሐውልቱን ፍጻሜ ባያዩም አልጋ ወራሻቸው ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ በዘውድ በዓላቸው ዋዜማ ሐውልቱን ገልጠው መርቀውታል፡፡ ፎቶው የምረቃውን ሥነ ሥርዓት ያሳያል፡፡ በሌላ በኩል የሚታየው የደብዳቤ ቅጂ ምስል ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሥርዓተ ንግሥናቸውን በመናገሻ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ፈጽመው እስከ ቤተ መንግሥታቸው የሚያደርጉትን ጉዞ ለመከታተል የሚፈልጉ ማድረግ ስለሚገባቸው ነገር የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ የጻፉትን የሚያሳይ ነው፡፡ ሌላኛው ፎቶ በዚያን ዘመን በአዲስ አበባ ከተማ መብራት የሚያፈልቀውን የኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ ላይ የተሰማራውን የኤሌክትሪክ ባለሙያ ያሳያል፡፡

የታሪክ ጓዳ

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች