በኤፍሬም አብርሃም (ኢንጂነር) የተጻፈው ‹‹ወንዝን ስንሻገር ራስን ፍለጋ›› ቅጽ 2 የግጥም መድበል መሰንበቻውን ገበያ ላይ ውሏል፡፡
ገጣሚው በመቅድሙ እንደገለጸው የሥነ ግጥም መጽሐፉ ፍሬ ነገር ‹‹ከፊታችን ያለውን ወንዙን ተሻግረን ለምና መልካም ሥነ ምድራዊ ገጽታና ይዞታ የሚገኝበት ቦታ ላይ ለመድረስ ይቻለናል የሚል ነው፡፡››
መድበሉ 54 የአማርኛና ሁለት የእንግሊዝኛ ግጥሞችን እንዲሁም በማሳረጊያ ውዳሴን ይዞ በብር 59.99 ለገበያ ቀርቧል፡