Monday, March 4, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለጂቡቲ ውኃ ለማቅረብ በ340 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው ፕሮጀክት የአቅሙን ያህል ማቅረብ አልቻለም

ለጂቡቲ ውኃ ለማቅረብ በ340 ሚሊዮን ዶላር የተገነባው ፕሮጀክት የአቅሙን ያህል ማቅረብ አልቻለም

ቀን:

ከሶማሌ ክልል ለጂቡቲ ንፁህ የመጠጥ ውኃ እንዲያቀርብ በ340 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባው ፕሮጀክት የአቅሙን ያህል ማቅረብ አልቻለም፡፡ ግዙፍ የውኃ ማምረቻና የማስተላለፊያ መስመር ጨምሮ ዋናው የመሠረተ ልማቱ አካል ከአንድ ዓመት በፊት ግንባታው ቢጠናቀቅም፣ በኤሌክትሪክ ኃይል እጥረት ምክንያት የሚፈለገውን ያህል ምርት መላክ አለመቻሉ ታውቋል፡፡

ግንባታውን ሲያከናውን የቆየው ሲሲጂ ኦቨርሲስ የተባለው የቻይናው ግዙፍ የግንባታ ተቋም ከድሬዳዋ ከተማ 35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው የሽኒሌ ወረዳ አቅራቢያ በሚገኝ ሥፍራ፣ የውኃ ማምረቻ ፕሮጀክትና ከ200 ኪሎ ሜትር በላይ እንደሚረዝም የተነገረለትን የውኃ መስመር ሥራ በ2009 ዓ.ም. ጀምሮ በ2011 ዓ.ም. ቢያጠናቅቅም፣ ባለፈው አንድ ዓመት ወስጥ ለጂቡቲ ዋና ከተማ የሚጠበቀውን ያህል ውኃ ማድረስ አለመቻሉ ታውቋል፡፡

ለዚህም እንቅፋት የሆነበት ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚጠብቀውን ኃይል፣ በሚፈለገው መጠንና ጊዜ ሊያገኝ አለመቻሉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ለበረሃማዋ ጂቡቲ በቀን እስከ 100 ሺሕ ኪዩቢክ ሜትር ወይም በዓመት እስከ 36 ሚሊዮን ኪዩቢክ ሜትር ውኃ ያቀርባል ተብሎ የተጀመረው ፕሮጀክት ከቻይና ኤግዚም ባንክ በተገኘ ብድር መገንባቱን፣ ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ፕሮጀክቱ በሁለቱ አገሮች ስምምነት መሠረት ለጂቡቲ ለ30 ዓመታት የመጠጥ ውኃ በነፃ እንዲያቀርብ ተደርጎ የተቀረፀ ነው፡፡

የፕሮጀክቱ ዋና አካል በሆነው ማምረቻ ግዙፍ ታንከር ያለው ሲሆን፣ በአቅራቢያው ከተቆፈሩ 28 የውኃ ጉድጓዶች የተሰበሰበ ውኃ በማጣሪያ ለመጠጥ ተስማሚ አድርጎ ይመረታል፡፡

በተዘረጋው ድንበር ተሻጋሪ የማስተላለፊያ መስመር አማካይነት ውኃው ለጂቡቲ እንደሚያቀርብ፣ ባለፈው አንድ ዓመት ኩባንያው ዲዚል ጄኔሬተሮችን በመጠቀም ከአቅሙ በታች በጣም ያነሰ ውኃ ወደ ጂቡቲ ለመላክ ሙከራ ሲያደርግ ነበር ተብሏል፡፡

ይሁን እንጂ ከጄኔሬተሩ የፈረስ ጉልበትና ከሚጠቀምበት የነዳጅ ወጪ አንፃር ውኃን ለማቅረብ አዋጭ አለመሆኑን፣ አንድ የኩባንያው መሐንዲስ ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ አሁን ባለው ሁኔታም በጄኔሬተሩ አማካይነት ውኃ ለማስተላለፍ የነዳጅ ፍጆታው በሰዓት አንድ ሺሕ ሊትር እንደሆነና መወደዱን ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ሪፖርተር ያናገራቸው እኚህ መሐንዲስ ዝርዝር ጉዳዮችን ለመግለጽ ኃላፊነት እንደሌላቸው ቢገልጹም፣ ኩባንያው ከመንግሥት ጋር ስለመነጋገሩና ስለተሰጠው ምላሽ ተጠይቀው፣ ችግሩ በአገሪቱ ውስጥ ካለው የኃይል እጥረት ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል፡፡ኩባንያቸው የገጠመው ችግር በኢትዮጵያ ከሚገኙት ሌሎች ሜጋ ፕሮጀክቶች የተለየ ነው ብለው እንደማያስቡም ጠቁመዋል፡፡

በዕቅዱ መሠረት ቢኬድ ኖሮ ፕሮጀክቱ ካለፈው አንድ ዓመት ጀምሮ በጅቡቲ ዲክሂል፣ አሊሳቢሀ፣ አርታና ዊአህ በተባሉ ሥፍራዎች ንፁህ የመጠጥ ውኃ ማቅረብ ይጠበቅበት እንደነበር ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ቁጥር ሲጨምር የሚኒባስ ታክሲዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱ ሊታሰብበት ይገባል

በአዲስ አበባ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ከፍተኛ የሚባለውን ድርሻ...

ሃምሳ ዓመታት ያስቆጠረው አብዮትና የኢትዮጵያ ፖለቲካ ውጣ ውረድ

የኢትዮጵያ ሕዝቦች የዴሞክራሲ ለውጥ ጥያቄ የሚነሳው ከፋሺስት ኢጣሊያ ወረራ...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የተፈጸመው ሕገወጥ ተግባር ምንድነው?

የአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት የዳይሬክተሮች ቦርድ፣...

በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት ላይ ምርመራ እንዲደረግ ውሳኔ ተላለፈ

ፕሬዚዳንቷና ዋና ጸሐፊው ተጠያቂ ሊሆኑ ይችላሉ ተብሏል ከአዲስ አበባ ንግድና...