Sunday, February 5, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትለብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ዙር ግንባታ ጨረታ ወጣ

ለብሔራዊ ስታዲየም ሁለተኛ ዙር ግንባታ ጨረታ ወጣ

ቀን:

ለጠቅላላ ግንባታው 2.5 ቢሊዮን ብር ተመድቧል

አደይ አበባ የሚል ስያሜን የያዘው አዲሱ ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታን ወደ ምዕራፍ ሁለት ለማሸጋገር የጨረታው ሒደት በመጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ፡፡ ስታዲየሙን ለመገንባት የተመደበው ጠቅላላ በጀት 2.5 ቢሊዮን ብር ሲሆን፣ ከዚህ ውስጥ ሁለት ቢሊዮን ብር ገደማ ለመጀመሪያው ዙር ግንባታ መውጣቱ ተነግሯል፡፡

በወንበር ከ60 ሺሕ በላይ ተመልካቾች የመያዝ አቅም ያለው ብሔራዊ ስታዲየም ግንባታው ከተጀመረ አራት ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ የስታዲየሙ የመጀመሪያ ዙር ግንባታ መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ በስድስት ወራት ለመዘግየቱ ምክንያት ተብሎ የተቀመጠው ደግሞ ከውጪ የሚገቡ ዕቃዎች መዘግየት፣ የብረት ዋጋ መናር፣ የውጭ ምንዛሪ ዕጥረት እንዲሁም ወቅታዊ የአገሪቱ ሁኔታ መሆኑ የስፖርት ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ናስር ለገሰ አስረድተዋል፡፡

በቻይና ስቴት ኮንስትራክሽን ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን አማካይነት በመገንባት ላይ የሚገኘው ብሔራዊ ስታዲየም፣ የሁለተኛውን ምዕራፍ ግንባታ ለመጀመር የሚያስችሉ ሁኔታዎች ማለትም ሁለት ጊዜ ጨረታ እንዲወጣ ከተደረገ በኋላ በአሁን ወቅት ከስምምነት ላይ መደረሱን አቶ ናስር ያስረዳሉ፡፡ የጨረታ ቡድኑና አማካሪ መሐንዲሱ ከተነጋገሩበት በኋላ ለከፍተኛ አመራሩ ቀርቦ ግንባታው በቅርቡ እንደሚጀመርም ተናግረዋል፡፡

የስታዲየሙ መጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ዘጠና ዘጠኝ በመቶ መጠናቀቁን ያስረዱት አቶ ናስር፣ በሁለተኛው ምዕራፍ ግንባታ የሚከናወኑት የጣሪያ ሥራ፣ የወንበር ገጠማ፣ የማጠቃለያ የሴኩሪቲና ሌሎችም መሠረተ ልማት የማሟያ ሥራዎች፣ ዋና ዋና መንገዶች፣ የመኪና ማቆሚያና የተለያየ ደረጃ ያላቸው የጂምናዚየም ሥራዎች ይሆናሉ፡፡

አደይ አበባ ስታዲየ በውስጡ ለከፍተኛ አመራሮች፣ ለሚዲያ ባለሙያዎች፣ ለስፖርተኞች፣ ለዳኞችና ለክብር እንግዶች ከሁለት ሺሕ በላይ መቀመጪያዎች ይኖሩታል፡፡

ከስታዲየሙ ውጪ ትናንሽ የእግር ኳስ ሜዳዎች፣ የመሮጭያ ትራክ (መም) እንዲሁም 3,500 መኪኖችን የሚያስተናገድ ፓርክ እንደሚኖረውም ተነግሯል፡፡ በአደጋ ጊዜ የሚያገለግል የሄሊኮፕተር ማረፊያን ጨምሮ የመረብ ኳስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የባድሜንተን፣ የሜዳ ቴኒስ፣ የቲያትር አዳራሾች፣ ሰው ሠራሽ ሐይቆችና ደረጃቸውን የጠበቁ መፀዳጃ ቤቶች ይኖሩታል ተብሏል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በጦርነቱ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ የመገንባቱ ውጥን

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል በሦስት ዙር ተካሄዶ በነበረው ጦርነት ምክንያት...

በርካታ ሰዎችን እያጠቁ የሚገኙት የሐሩራማ አካባቢ በሽታዎች

ትኩረት የሚሹ የትሮፒካል /ሐሩራማ በሽታዎች በአብዛኛው ተላላፊ ሲሆኑ፣ በዓይን...

ስለአገር ኢኮኖሚ ማሰብ የነበረባቸው ጭንቅላቶች በማያባሩ ግጭቶች ተነጥቀዋል!

አገራችን ኢትዮጵያ ውጪያዊና ውስጣዊ ፈተናዎቿ መብዛት ብዙ ዋጋ እያስከፈላት...