Wednesday, February 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትአትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአሜሪካዊ ማኔጀር ሁሴን ማኪን ውል አቋረጠ

አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአሜሪካዊ ማኔጀር ሁሴን ማኪን ውል አቋረጠ

ቀን:

ውሳኔው እንዲጸና ተጠይቋል

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን የአትሌቶችና የአሠልጣኞቻቸው ሥራ አስኪያጁን አሜሪካዊ ሚስተር ሁሴን ማኪ የተወካይነት ውል ማቋረጡን አስታወቀ፡፡ ፌዴሬሽኑ በውሳኔው የሚጸና ሆነ የአትሌት ተወካዮችን ጨምሮ በበርካቶች እግር ከወርች ለተተበተበው አትሌቲክሱ ትልቅ መፍትሔ እንደሚሆን ሙያተኞች ይናገራሉ፡፡

ታላላቅ ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን በማሠልጠን የሚታወቁትን የማናጀር ተወካዮች ጨምሮ ሥራ አስኪያጅ የሆኑት አሜሪካዊው የአትሌቶች ማናጀር ሁሴን ማኪ ከፌዴሬሽኑ ጋር የነበራቸው ውል እንዲቋረጥ ምክንያት የሆነው፣ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በአትሌቶች ላይ ያስተላለፈውን የዲሲፕሊን መመሪያ ተላልፈው በመገኘታቸው ነው፡፡ 

ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ከመስከረም 16 እስከ 25 ቀን 2012 ዓ.ም. በኳታር ዶሃ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ በማራቶን የተወዳደሩ አትሌቶች ለሦስት ወራት የማገገሚያ ጊዜ ቀድመው ምንም ዓይነት ውድድር እንዳያደርጉ በወቅቱ ሰርኩላር ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡ መመሪያውን በሚጥሱ የአትሌት ማኔጀሮችን ጨምሮ በሁሉም አካላት ላይ ፌዴሬሽኑ ዕርምጃ እወስዳለሁ ማለቱም ይታወሳል፡፡

ይሁንና የኤሊት ስፖርትሰ ማኔጅመንት ኢንተርናሽናል (Elite Sports Management INTL) ሥራ አስኪያጅና ከኢትዮጵያ አትሌት ተወካዮች አንዱ የሆኑት ስተ ሁሴን ማኪ፣ ሰርኩላሩን በመተላለፍ አትሌታቸውን ጥቅምት 23 ቀን 2012 ዓ.ም. በተካሄደው የኒውዮርክ ማራቶን አሳትፈው የአሠራር ጥሰት በመፈጸማቸው ፌዴሬሽኑ በተወካዩ ላይ የውል ማቋረጥ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አሜሪካዊ ማናጀር ሁሴን ማኪ ጨምሮ ለሌሎችም የውጭ አገር ዜጎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶችን በማናጀርነት እንዲያስተዳድሩ ውል እንደሚሰጥ፣ ይሁንና ማናጀር የሚያገኙ አትሌቶችም ሆነ ማናጀሮች የሚዋዋሉት ውል ሕጋዊነቱ የሚረጋገጠው ለፌዴሬሽኑ ደንብና መመሪያ ተገዥ እስከሆኑ ድረስ እንደሚሆን ጭምር ፌዴሬሽኑ ይገልጻል፡፡

የውሳኔውን ትክክለኛነት የሚያረጋግጡ የዘርፉ ሙያተኞች፣ ‹‹በማናጀር የሚተዳደሩ ብዙዎቹ አትሌቶች ከብሔራዊ ፌዴሬሽኑም ሆነ ለዕውቅና ካበቋቸው ክለቦች አቅም በላይ ከሆኑ ቆይተዋል፡፡ በዚህ ‹የተጠሪነት ወሰን› ክፍተት ቁጥራቸው በውል የማይታወቅ አትሌቶች ዕውቅና በሌላቸው ማናጀር ‹ተብዬዎች› ከጉልበታቸውም ሆነ ከገንዘባቸው ሳይሆኑ በአጭር የቀሩ አሉ፡፡ የፌደሬሽኑ ውሳኔ ቢዘገይ እንጂ ያልመሸበት በመሆኑ ውሳኔው በትክክል ተግባራዊ መሆን ይኖርበታል፤›› ይላሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በወቅታዊ ፀጥታና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የቀረበላቸውን ምክረ ሐሳብ እያደመጡ ነው]

ችግሩ ምን እንደሆነ በትክልል ለይተነዋል ግን ግን ምን? በይፋ መናገር አልነበረብንም። ለምን? ችግሩን...

የ12ኛ ክፍል የብሔራዊ ፈተና ውጤትና እንደምታው

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት (UNESCO) የትምህርትን...

ንግድ ባንክ ከቪዛና ማስተር ካርድ ጋር ተደራድሮ ያስጀመረው የገንዘብ ማስተላለፊያ ቴክኖሎጂና ፋይዳው

ከውጭ ወደ አገር በሕጋዊ መንገድ የሚላክ ገንዘብ (ሬሚታንስ) መጠን...

ይኼ አመላችን የት ያደርሰን ይሆን?

እነሆ ከፒያሳ ወደ ካዛንቺስ። ‹‹አዳም ሆይ በግንባር ወዝ ትበላለህ››...