ሰሞኑን አዲስ አበባ ጎራ ያሉት የዋሽንግተን ዲሲ ከንቲባ ሙሪየል ቦውሰር፣ በሁለቱ ከተሞች መካከል እህትማማዊነትን የሚያጠናክር ስምምነት ከምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ጋር አድርገዋል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በዘልማድ “ጋዜቦ” ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ማዞርያ “ዋሽንግተን ዲሲ” ተብሎ ተሰይሟል፡፡ ከማዞርያው ጀምሮ ወደ አፍሪካ ኅብረት የሚወስደው መንገድም የከንቲባ ሙሪየል ቦውዘርን ስም አግኝቷል፡፡ ከከንቲባዋ ጋር ከ50 በላይ በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ላይ የተሰማሩ ግለሰቦች አብረው አዲስ አበባ መግባታቸው ታውቋል፡፡ ፎቶዎቹ የኩነቱን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡