Tuesday, February 20, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልየባህል አልባሳትን የሚታደጋቸው ማን ነው?

የባህል አልባሳትን የሚታደጋቸው ማን ነው?

ቀን:

በተመስገን ተጋፋው

ኢትዮጵያ የተለያዩ ብሔረሰቦች መገኛና የብዙ ባህልና እሴት ባለቤት እንደመሆኗ ትውፊቶቿ ከሚገለጹባቸው መካከል አልባሳቷ የመጀመሪያውን ረድፍ ይይዛሉ፡፡ በዓለም መድረክ ኢትዮጵያውያን በተለይ አምረውና ደምቀው ብቅ የሚሉት የባህል ልብሶቻቸውን ለብሰው ሲታዩ እንደሆነ ይወሳል፡፡

የኢትዮጵያን የባህል አልባሳት ተወዳዳሪነት ለማሳደግ የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረትና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት ጋር በመተባበር ኅዳር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. በኔክሰስ ሆቴል የውይይት መድረክ አዘጋጅቶ ነበር፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በመድረኩ ላይ የተገኙት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ጽሕፈት ቤት ዳይሬክተር አቶ አህመድ መሐመድ፣ ቀደምትነቷን ከሚመሰክሩ ዕንቁ ሀብቶች መካከል የባህል አልባሳት እንደመገኘታቸው እነሱን በአግባቡ መጠቀም ከተቻለ አገሪቷ ያለችበትን የጎጆ ኢንዱስትሪ የሚያሳድግ የሀብት መሸጋገሪያ ድልድይ ለመሆን ዕድል እንደሚኖር ገልጸዋል፡፡

የሕዝቦች ማንነት መገለጫ የሆኑት የባህል አልባሳት ከኢኮኖሚ ዘርፍ አንፃር ጉልህ ሚና እንደሚጫወቱና ለሥራ ዕድል ፈጠራም ከከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚያበረክቱም ተናግረዋል፡፡

ለባህል አልባሳት ፈተና የሆነው በውጭ አገሮች በተለይ በቻይና የአገር ቤቱን አስመስለው በፋብሪካ የሚያመርቱት ጨርቅ ገበያውን መቆጣጠሩ ነው፡፡ ይህም በውጭ የተመረተው የባህል ልብስ ከዋጋ አንፃር አነስተኛ መሆኑ ነው ገበያውን ሊሸፍን የቻለው፡፡

የባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴርም እነዚህ ችግሮችን ለመፍታት በዕቅድ ከያዛቸው መካከል አንዱ የባህል አልባሳት ከገበያ ጀምሮ ያለባቸውን  ችግሮች ለመፍታት እንደሆነ አስረድተዋል፡፡ ለዚህም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንዲሠሩ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሚኒስቴሩ የዕደ ጥበባት ማበልፀጊያና የገበያ ልማት ተወካዩ አቶ ነጋሽ አሰፋ፣ በኢትዮጵያ በማንኛውም የከተማና የገጠር አካባቢ የሚመረቱ የየራሳቸውን አካባቢ ጥበብና ፈጠራ ነፀብራቅ መሆናቸውን አመልክተዋል፡፡ ከዚያ ባለፈ ማኅበረሰቡ በቀላሉ ወደ ሥራ የሚሰማራበት ዘርፍም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ 

የባህል አልባሳት ምርቶች በየጊዜው ዋጋቸው እየጨመረና እየናረ በመሄዱ አብዛኛው ተጠቃሚ የአገሩን ምርት በመተው መሰል ወደሆኑ የቻይና ምርቶች እየተሳበ መሆኑን አቶ ነጋሽ ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

በባህል አልባሳት ምርት ላይ በሚታዩ ችግሮችና ማነቆዎችም መካከል የተለያዩ ጥሬ ዕቃዎች ወይም የምርት ግብዓቶችን ማጣት፣ በጥሬ ዕቃዎች ላይ ዋጋ መጨመር፣ ይጠቀሳሉ፡፡ በአብዛኛው የባህል አልባሳት ለሽመና የሚውሉ ግብዓቶች ከጥጥ ውጪ ሌሎቹ ከውጭ መምጣታቸው ለኢንዱስትሪው ዕድገት መዋዥቅ ምክንያት ናቸው በማለት አቶ ነጋሽ ጠቁመዋል፡፡ ከዚህ ጋር ተያይዞም በዘርፉ የሚሠሩ መንግሥታዊም ሆኑ መንግሥታዊ ያልሆኑ አካላት የተናበበና የተቀናጀ ሥራ አለመሥራታቸው አንዱ ሳንካ መሆኑን አክለዋል፡፡

ለባህል አልባሳት የሚውሉ ጥጥ፣ ክር፣ ማግ እና ሌሎች የሽመና መሣሪያዎች፣ የመሳሰሉ ጥሬ ዕቃዎችን በአግባቡ አለማግኘት በዘርፉ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ እንደሚፈጥርም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያም ከሌሎች አገሮች ተወዳዳሪ እንድትሆን የባህል አልባሳት ግብዓቶችን ጥጥና የጥለት አቅርቦት የሚሻሻልበትን መንገድ መፍጠር፣ ለመቀቀያ፣ ለማጠንከሪያና ለማንጫ የሚያገለግሉ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ማስረፅ፣ የጥራት ቁጥጥር ሥርዓቱን በግብይትም ሆነ በምርት ክትትል ማድረግ መፍትሔ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡ የአገር ውስጥ የባህል አልባሳት ተጠቃሚነትን ማሳደግ፣ እንደሌሎች አገሮች ምርቶችን በብዛት ማምረት ከተቻለም ኢኮኖሚያዊ ሆነ ማኅበራዊ ዕድገትን ማሳካት ይቻላል ሲሉ አቶ ነጋሽ ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ አዕምሯዊ ንብረትና ጥበቃ ጽሕፈት ቤት የእሴት ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ወርቁ፣ አገር በቀል ልብሶችን በገበያ ላይ ተወዳዳሪ ለማድረግ የግል ዲዛይነሮች፣ ማኅበራት፣ እንዲሁም ሸማኔዎች የሚያመመርቷቸውን የባህል ልቦሶች እንደ አዕምሯዊ ንብረት ለማስጠበቅ ሥራዎች እየተሠሩ መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡ ይህንንም በዘላቂነት ለማስኬድ የአገሪቷን የባህል አልባሳት ለማስጠበቅ የሕግ ማዕቀፍ ለማውጣ መታቀዱንም ሳይናገሩ አላለፉም፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የካቲት አብዮት – ጥያቄዎችሽ ዛሬም እየወዘወዙን ነው!

በበቀለ ሹሜ አጭር መግቢያ የዚህ ጽሑፍ አቅራቢ ከ1960ዎች ወጣቶች ርዝራዦች አንዱ...

የሰሞኑ የ“መኖሪያ ቤቶች” የጨረታ ሽያጭ ምን ዓይነት ሕጋዊ መሠረት አለው?   

በዳዊት ዮሐንስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ከተማ አየር ላይ ከሚንሸረሸሩ ዜናዎች...

ሁለቱ ወጎች፡ ከሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! እስከ በዓሉ ቤርሙዳ

በተክለ ጻድቅ በላቸው ሰማየ ሰማያት አድርሶ መላሹ ቋንቋ! ከሁለት ሦስት ዓመት...

ለትግራይ ክልል ድርቅ ተፈናቃዮች አፋጣኝና ቀጣይነት ያለው ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና የሰላም ጉዳዩች ቋሚ...