ከሰባት አሠርታት በላይ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ ሼባ ማይልስን የጀመረበት 20ኛ ዓመትና የደንበኞችን ቀን ኅዳር 2 ቀን 2012 ዓ.ም. አክብሯል፡፡ በስካይ ላይት ሆቴል በነበረው ሥነ በዓል ታማኝ ደንበኞች ያላቸውን በተለያዩ የሙያ ዘርፎች የተሰማሩ ግለሰቦችን ሸልሟል፡፡ ሽልማቱን ያበረከቱት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ናቸው፡፡ ፎቶዎቹ የመሰናዶውን ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡