Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጤናን አዋኪው ክስተት

ጤናን አዋኪው ክስተት

ቀን:

በተመስገን ተጋፋው

በኢትዮጵያ አንዳንድ ሥፍራዎች የነበሩ ግጭቶች ቢረግቡም፣ ሰላም ሰፍኗል ለማለት ግን አያስደፍርም፡፡ የግለሰቦች ፖለቲካ ፍላጎት በማኅበረሰቡ ላይ አሉታዊ ጫናን አሳድሯል፡፡ ልጆቻቸውን ዩኒቨርሲቲም ሆነ ትምህርት ቤት የላኩ ወላጆች፣ ከራሳቸው አልፈው የልጆቻቸው ደኅንነት ጉዳይ እያሳሰባቸው መሆኑን ያነጋገርናቸው ወላጆች ነግረውናል፡፡ የኑሮ ውድነት ጣራ በነካበት ላይ የሰላም መደፍረሱ ለጭንቀትና ለሐሳብ እንደዳረጋቸውም ገልጸውልናል፡፡ ጭንቀቱም እንዲህ በቃል እንደሚነገረው አይደለም፡፡ በተለይ ልጁን ከሥሩ ለይቶ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርት ወደ ክልል የላከ ቤተሰብ ውጥረት ውስጥ ይገኛል፡፡

የሰላም ዕጦቱ ፖለቲካውን ተመርኩዞ መምጣቱ፣ በቡድን በመከፋፈል የጎሳ፣ የሃይማኖትና የብሔር ልዩነት በመፍጠር የአገሪቱን ሰላም ለማደፍረስ የሚሯሯጡ መኖራቸው፣ ልዩነትን በጉልበት ለመጫን የሚደረግ ሩጫ ኢትዮጵያ ያለችበትን ኢኮኖሚያዊም ሆነ ማኅበራዊ ችግር ለመቅረፍ አዳጋች አድርጎታል፡፡

በቅርቡ በኦሮሚያ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች ላይ በነበረ ግጭት በሺዎች የሚቆጠሩ ተፈናቅለዋል፣ ጉዞ በማድረግ ላይ የነበሩ ተስተጓጉለዋል፡፡ በሰዎች ላይ ሞትና ጉዳት፣ በንብረት ላይ ውድመት ተከስቷል፡፡ ይህ ችግር የእምነት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ድርጅቶችና የተለያዩ ሥፍራዎች ላይ ሥጋት ፈጥሯል፡፡ ሰሞኑን ዩኒቨርሲቲዎች ላይ የነገሠው ሥጋት ደግሞ ሌላ ውጥረትን ጨምሯል፡፡ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ለመሥራት ሥጋትም አለ፡፡ በማኅበረሰቡ ላይ የሚፈጠረው ውዥንብር ከሥጋት ባለፈ የጤና መዛባትን ያስከትላል፡፡

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ልቦና ትምህርት ክፍል ዋና ኃላፊ አበባው ምናየ (ዶ/ር) እንደሚሉት፣ በሰላም ዕጦት ምክንያት በሰዎች አዕምሮ ላይ የሰቀቀን ስሜት፣ አለመተማመን፣ ጭንቀት፣ አለመረጋጋት ይፈጥራል፡፡

በሃይማኖት ቦታዎችና በብሔር ብሔረሰቦች ላይ አለመተማመን እንዲፈጠር፣ በሥራ አካባቢዎች ላይ ሰዎች ተረጋግተው እንዳይሠሩና ቤተሰብም ልጆቻቸውን ለማስተማር ሥጋት ውስጥ ይጥላቸዋል፡፡  

በዚህ ችግር ሕፃናት የበለጠ ተጎጂ ናቸው፡፡ በአዕምሮአቸውም የሚቀረጸው ሃይማኖትን፣ ብሔርን፣ ባህልን ጭምር እንዲጠሉ ነው፡፡ ዶ/ር አበባው እንደሚሉትም ከዚሁ ጎን ለጎን በትምህርታቸው ላይ ጉዳት ያስከትላል፡፡ በሰው ልጅ ጤና ላይም የአዕምሮ መዛባትንና ጥላቻንም ይፈጥራል፡፡

ከአራት እስከ አሥራ አምስት ዓመት ክልል ላይ የሚገኙ ሕፃናት አዕምሯቸው ሁሉ ነገር የሚያምን ስለሆነ በአካባቢያቸው ላይ የሚፈጠር ግድያና ግጭትን በሚያዩበት ጊዜ በጤናቸው ላይ ቀውስ ሊፈጥር ይችላል፡፡

በአፍሪካ ሰላምን በማደፍረስና በማወክ የሰው ልጅ ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ግለሰቦች እንደሚገኙ፣ ችግሩም በአብዛኞቹ አገሮች ላይ ዕልባት አለማግኘቱንና መባባሱን የሚገልጹት የሥነ ልቦና ባለሙያው፣ የኢትዮጵያው ክስተት ካሁኑ ዕልባት ማግኘት እንዳለበት ለዚህም የሃይማኖት ተቋማት፣ ትምህርት ቤቶች፣ ጤና ጣቢያዎች ከመንግሥት ጋር እጅና ጓንት በመሆን ሰላም የማስፈን ሥራን መሥራት እንደሚገባቸው አሳስበዋል፡፡

የሕዝቡን ሰላም የሚያደፈርሱ ሰዎች ላይ መንግሥት ትኩረት በመስጠት ዕርምጃ መውሰድ እንዳለበት፣ ዕርምጃ መውሰድ እንዳለበት፣ ይህ ካልሆነ ግን አገሪቷ አሳሳቢ ሁኔታ ውስጥ እንደምትገባ ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...