Monday, July 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ ከአምስት ሺሕ በላይ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ሊቀጠሩ ነው

በአዲስ አበባ ከአምስት ሺሕ በላይ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ሊቀጠሩ ነው

ቀን:

በሔለን ተስፋዬ

በአዲስ አበባ በተጀመሩ ፕሮጀክቶች የሚሳተፉ ከአምስት ሺሕ በላይ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ወደ ሥራ እንደሚያስገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡

የከተማው ፕሬስ ሴክሬተሪያት ጽሕፈት ቤት ምክትል ኃላፊ አቶ ነስረዲን ሙሐመድ ኅዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ ከ20 ሺሕ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶችና አሥር ኪሎ ሜትር የመንገድ ፕሮጀክቶች መጀመራቸውን አስታውሰው፣ ፕሮጀክቶቹ ከከተማዋ ገጽታ ግንባታ በተጨማሪ፣ ለበርካታ ሥራ አጥ ምሩቃን የሥራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ተናግረዋል፡፡

በከተማዋ የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራንና ለአዳዲስ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን የሥራ ዕድል ማመቻቸቱን ያወሱት ምክትል ኃላፊው፣ በከተማዋ የሚታየውን የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለመፍታት ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በቅርብ የተመረቁ ተማሪዎችን ወደ መንግሥት ሥራ የማስገባቱ ሒደት እየተከናወነ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ባስቀመጠው የሥራ ዕድል ፈጠራ አቅጣጫ መሠረት የዩኒቨርሲቲ ምሩቃንን ወደ መንግሥት ሥራ ለማስገባት ጥረት እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ወ/ሮ ነጂባ አክመል ገልጸዋል፡፡

ቢሮው ሰሞኑን ባወጣው የሥራ ቅጥር ማስታወቂያም ተቋማት የሚሰጡትን አገልግሎት ለማቀላጠፍና የከተማዋን ወጣቶች የሥራ ዕድል ተጠቃሚ ለማድረግ የታለመ መሆኑንም አክለዋል፡፡

ሥራ አጥ የዩኒቨርሲቲ ምሩቃን በተደረገው ጥሪ መሠረት እየተመዘገቡ ሲሆን፣ እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ወጣቶች ተመዝግበው ተሠልፈው እንደነበረ ሪፖርተር ለመታዘብ ችሏል፡፡

በስም ቅደም ተከተል እንዲመጡ መነገሩን፣ ካለው ተመዝጋቢ ብዛት አንጻር ሥራውን የማግኘት ዕድላቸው አናሳ መሆኑን ተሠልፈው ያገኘናቸው አንዳንድ ወጣቶች ነግረውናል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...