Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባለሀብቶች ፎረም ለማቋቋም መመርያ አፀደቀ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባለሀብቶች ፎረም ለማቋቋም መመርያ አፀደቀ

ቀን:

ከመሬት፣ ከመሠረተ ልማትና ከፋይናንስ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎች ሲነሱ፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተነጋግሮ መፍትሔ ለመስጠት፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የባለሀብቶች ፎረም  የማቋቋሚ መመርያ ማፅደቁ ተጠቆመ፡፡

ፎረሙ መቋቋሙ ባለሀብቶች ውጤታማ ተግባር እንዲያከናውኑ እንደሚያስችላቸው፣ የሚነሱ ጥያቄዎችን በተናጠል ከመመለስ ይልቅ በተደራጀ መንገድ ለማስተናገድና ፍላጎታቸውን በማሟላት አሠራሩን የተሻለ እንደሚያደርገው ተገልጿል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ የፎረሙን ማቋቋሚያ መመርያ ኅዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም. ማፅደቁን አስመልክቶ አስተያየታቸውን የሰጡት፣ የአስተዳደሩ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን የፕሮጀክት ክትትልና ድጋፍ ዳይሬክተር አቶ ብሩክ እስከዚያ፣ በኮሚሽኑ አቅም ብቻ ከመንቀሳቀስ የባለሀብቶች መደራጀት ጠቃሚ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ፎረሙ ሕገወጥ ኢንቨስትመንትን በማስቀረት ወደ ሕጋዊ መንገድ ለማምጣት አጋዥ እንደሚሆንም አክለዋል፡፡

በፎረሙ በማኅበራዊና በአገልግሎት ዘርፍ የተሰማሩ ባለሀብቶች አባል መሆን እንደሚችሉም ተነግሯል፡፡ ፎረሙ የባለሀብቶችን ችግር ከመቅረፍ ባሻገር ለቴክኖሎጂ ሽግግር ዕድገት፣ የሥራ አጦችን ቁጥር ለመቀነስና የውጭ ምንዛሪ ለማሻሻል ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለውም አቶ ብሩክ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ፈቃድ የወሰዱ ከ48,000 በላይ ባለሀብቶች እንዳሉም ተጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...