Monday, April 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየዜና አገልግሎትና የፕሬስ ድርጅት ሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በቦርድ እንዲወሰን ተደነገገ

የዜና አገልግሎትና የፕሬስ ድርጅት ሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በቦርድ እንዲወሰን ተደነገገ

ቀን:

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትንና የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ማቋቋሚያ አዋጆች እንደገና ለማሻሻል የቀረቡለትን ሁለት ረቂቅ አዋጆች ፓርላማው መርምሮ ሲያፀደቅ፣ በማሻሻያዎቹ መሠረት የሁለቱም ተቋማት ሠራተኞችና በመንግሥት የሚሾሙላቸው አመራሮች የደመወዝ እርከንና ጥቅማ ጥቅሞችን በተመለከተ የመወሰን ሥልጣኑ የቦርድ አመራሮች እንዲሆን ተደነገገ፡፡

ምክር ቤቱ ሐሙስ ኅዳር 4 ቀን 2012 ዓ.ም. ባካሄደው አራተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትንም ሆነ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን ማቋቋሚያ አዋጆች እንደገና ለማሻሻል የቀረቡለትን ሁለት ረቂቅ አዋጆች፣ በአንድ ዓመት ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ነው መርምሮ ያፀደቃቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ከ2006 ዓ.ም. ጀምሮ በአዋጅ ሳይሆን በደንብ ሥራውን እስከ 2011 ዓ.ም. ካከናወነ በኋላ፣ በደንብ መሆኑ ቀርቶ በአዋጅ ሆኖ ተጠሪነቱም ለምክር ቤቱ እንዲሆን በሚያዚያ 2011 ዓ.ም. ተወስኖ ነበር፡፡ በዚህም አዋጅ ከተጠሪነቱ በተጨማሪ የሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በምክር ቤቱ እንዲወሰን ተደንግጎ እንደነበር፣ ረቂቁን ያዘጋጀው የምክር ቤቱ የሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በተወካዩ በአቶ አበበ ጎዴቦ አማካይነት አስረድቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ሆኖም አዋጁ ወደ ሥራ በሚገባበት ወቅት ከኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ጋር በተያያዘ በምክር ቤቱ ደረጃ ውሳኔ ለመስጠት፣ እንዲሁም በቀጣይ ይህን አሠራር ተግባራዊ ለማድረግ ተጨባጭ ችግሮች በማጋጠማቸው ያሉ አማራጮችን በመመልከት፣ የአዋጁን ድንጋጌ ማሻሻያ ተገቢ ሆኖ ተገኝቷል ሲሉ ለምክር ቤቱ አስረድተዋል፡፡

እንደ ዜና አገልግሎት የማሻሻያ አዋጅ የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም ራሱን የቻለ የማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጅ በተናጠል ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ቢሆንም፣ እንደ ቀዳሚው ሁሉ የድንጋጌ ማሻሻያ እንደተደረገለትና ተመሳሳይ ማብራሪያ ተሰጥቶታል ብለዋል፡፡

“የድርጅቱ ማቋቋሚያ አዋጅ እንደ ኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ሁሉ ቀደም ሲል የፀደቀ ቢሆንም፣ ምክር ቤቱ የተቋማቱን አመራሮችና ሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም ለመወሰን የሚያስችል አሠራር የሌለው በመሆኑ አዋጁን ማሻሻል አስፈልጓል፤” በማለት አቶ አበበ ገለጻ አድርገዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት የሁለቱንም ተቋማት ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም አወሳሰንን አስመልክቶ መብራራት ይገባቸዋል ያሏቸውን ጥያቄዎች አንስተው፣ ከግማሽ ሰዓት በላይ ክርክር ተደርጎባቸዋል፡፡

ድርጅቶቹ ቦርድ ያላቸው በመሆኑ ከምክር ቤቱ ይልቅ ለቦርዶቹ ኃላፊነቱን መስጠትና የተሰጣቸውን ኃላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ ክትትልና ቁጥጥር ማድረጉ፣ ከጊዜና ከአዋጭነት አንፃር “ተመራጭ” ተደርጎ መወሰዱንም ነው አቶ አበበ የተናገሩት፡፡

“ሁለቱም የሚዲያ ተቋማት ለአገሪቱ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ እስካሁን ያበረከቱት አስተዋጽኦ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ በቀጣይም በሚዲያ ኢንዱስትሪው ውስጥ ያላቸውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እንዲችሉ አደረጃጀታቸውን፣ እንዲሁም ደመወዝና ጥቅማ ጥቅማቸውን ማሻሻል ያስፈልጋል፤” ሲሉም አክለዋል፡፡

በተለይም የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎትን ለማቋቋም ቀደም ሲል የፀደቀው አዋጅ በዋና ሥራ አስፈጻሚና በምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም አወሳሰን ላይ ክፍተት የነበረበት በመሆኑ፣ ይህንን አዋጅ እንዲሻሻል ማድረጉ ችግሩን ይፈታዋል ብለዋል፡፡

ምክር ቤቱም በማሻሻያ ረቂቅ አዋጆቹ ላይ ከተወያየና ከመረመረ በኋላ የፕሬስ ድርጅትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በአሥር ተቃውሞ፣ በአሥር ድምፀ ተዓቅቦና በአብላጫ ድምፅ፣ እንዲሁም ዜና አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በዘጠኝ ተቃውሞ፣ በ12 ድምፀ ተዓቅቦና በአብላጫ ድምፅ የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ሠራተኞች ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም በቦርድ እንዲወሰን የሚለውን ረቂቅ አዋጅ አፅድቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...