Saturday, April 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየክልል ስታዲየሞች ግንባታ አለመጠናቀቅ የፈጠረው ሥጋት

የክልል ስታዲየሞች ግንባታ አለመጠናቀቅ የፈጠረው ሥጋት

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ካለበት ዝቅተኛ ሥፍራ መውጣት ተስኖት በሚኳትንባቸው ዓመታት በአራቱም አቅጣጫ የመያዝ አቅማቸው ከፍተኛ የሆነ ስታዲየሞች ግንባታ በሁሉም ክልሎች መመልከት የተለመደ ሆኗል፡፡ ፍጻሜ ባይኖረውም እንደቀጠለ ይገኛል፡፡

ባለፉት አሥር ዓመታት በተለይ የስታዲየም ግንባታው የክልሎችን ኮታ ለማሟላት በሚመስል መልኩ በየዓመቱ ኅዳር 29 ቀን የሚደረገውን የብሔር ብሔረሰቦች ቀን እንዲስተናገድበት የክልል ከተሞች የማጠናቀቂያ ጊዜ ሰሌዳ ያልተቀመጠላቸው አንዳንድ ስታዲየም አግኝተዋል፡፡

ከሰሞኑ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ከተገነቡትና ካልተጠናቀቁት መካከል የባህር ዳር፣ የመቐለና የወልዲያ ዓለም አቀፍ ስታዲየሞች አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማስተናገድ ‹‹ይችላሉ አይችሉም›› የሚለውን ገምግሟል፡፡

ካፍ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ድረስ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የፊታችን ማክሰኞ ኅዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም. የአይቮሪኮስት አቻውን መቐለ በሚገኘው የትግራይ ዓለም አቀፍ ስታድየም ሊያስተናግድ የነበረውን መርሐ ግብር ሰርዞ ጨዋታው ለጊዜው በባህር ዳር ስታድየም እንዲደረግ ወስኗል፡፡

ከዚህ በመነሳት አስተያየት ሰጪዎቹ ለመከራከሪያቸው ማሳያ በየክልሉ ከብሔር ብሔረሰብ በዓላት ዓመታዊ አከባበር ጋር በፍጥነት እንዲደርስ የተገነቡት ስታዲየሞች አለመጠናቀቃቸውን የሚተቹ ሰሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ግንባታው ከበዓሉ ማለፍ ወዲህ ከነበረበት ቅርፅና ይዘት ያለፈ ሥራ አለመሠራቱን በማውሳት ጭምር ይናገራሉ፡፡

በዚህ መሐል የሚገኘው የስታዲየሞቹ ግንባታ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ከዓለም አቀፍ መመዘኛ ጋር እየተያያዘ፣ ምናልባትም ካፍ ከሚሰጠው ቀጠሮና ማስጠንቀቂያ አንፃር ለአገሪቱ ብሔራዊ  ክብር ጠባሳ እንዳያስከትል ሥጋት መፍጠሩ አልቀረም፡፡

በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የክለብ ላይሰንሲንግ ዳይሬክተር አቶ ተድላ ዳኛቸው ካፍ በሦስቱ ስታዲየሞች ላይ ያደረገውን ግምገማ በሚመለከት፣ ‹‹የካፍ ልዑካን  እስካሁን ስታድየሞቹ አህጉራዊና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማስተናገድ አለማስተናገዳቸውን በሚመለከት ያላቸውን አስተያየትም ሆነ ውሳኔ አላሳወቁም፤›› ይላሉ፡፡

ቀደም ሲል በመቐለ ስታዲየም ቀጠሮ ተይዞለት የቆየው የኢትዮጵያና የአይቮሪኮስት የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ በባህር ዳር ስታዲየም እንዲደረግ ውሳኔ ያሳለፈው ውድድሩን በበላይነት የሚመራው ካፍ አይደለም ወይ? ለሚለው የሪፖርተር ጥያቄ አቶ ተድላ፣ ‹‹ካፍ በሥሩ የሚመራቸው ማለትም ስታዲየሞችን ጨምሮ ሌሎች መሠረተ ልማቶችን የሚመለከተው ዲፓርትመንትና ውድድር ነክ የሆኑ ጉዳዮችን የሚመለከተው ክፍል ተግባብተው የሚሠሩ አይመስለኝም፡፡ ከሰሞኑ ከስታዲየሞቻችን ጋር የተያያዘው ዜና እኔ እስከማውቀው ድረስ የመቐለ ስታድየም ጨዋታ እንዳያስተናግድ፣ የባህር ዳር ደግሞ ማስተናገድ እንደሚችል አልተረጋገጠም፡፡ ከካፍ  ገምጋሚ ቡድን ጋር አብሬ ነበርኩ፣ ጨዋታው በመቐለ እንዳይደረግ የወሰነው ገምጋሚው ቡድን ቢሆን ኖሮ በግልባጭ ለእኔም ይደርሰኝ ነበር፤›› ብለው ካፍ ውስጥ ያለውን ያለመናበብ ክፍተት ያስረዳሉ፡፡

ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራር በተለይ ለሪፖርተር እንደገለጹት ከሆነ፣ ‹‹የራሳችንን ችግር ውጫዊ ማድረግ አይጠቅመንም፣ ምክንያቱም ካፍ አንጋፋውን የአዲስ አበባ ስታዲየም ባገደ ማግስት፣ ለባህር ዳርና ለመቐለ ስታዲየሞች መሰረታዊ የሚባሉ የማስተካካያ ግንባታ እንዲያደርጉ የሦስት ወር ቀነ ገደብ ሰጥቷል፣ ይሁንና አንዳቸውም ሊፈፅሙ አልቻሉም፡፡ የሚገርመው የኢትዮጵያና የአይቮሪኮስት ጨዋታ ከመቐለ ወደ ባህር ዳር ሲዛወር የባህር ዳር ስታዲየም የተባለውን ግንባታ በማከናወኑ እንዳልሆ ሊወሰድ ይገባል፤›› ብለው በቀጣይ የአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያዎች አሁን ባለው ሁኔታ በጎረቤት አገር ስታዲየሞች እንዲደረግ ካፍ እንዳይወስን ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳዩን መከታተል እንደሚኖርበት ጭምር ያስረዳሉ፡፡      

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ተወግዘው የነበሩ ሦስቱ ሊቀጳጳሳትና 20 ተሿሚ ኤጲስ ቆጶሳት ውግዘት ተነሳ

_ቀሪዎቹ ሦስት ህገወጥ ተሿሚዎች የመጨረሻ እድል ተሰጥቷቸዋል ​ ጥር 14...

በሕወሓት አመራሮች ላይ ተመስርቶና በሂደት ላይ የነበረው የወንጀል ክስ ተቋረጠ

በቀድሞ የትግራይ ክልል ፕሬዚደንት ደብረጽዮን ገብረሚካኤ,(ዶ/ር)ና ባለፈው ሳምንት በተሾሙት...

[የምክር ቤቱ አባል ላቀረቡት ጥያቄ በተሰጣቸው ምላሽ አቤቱታቸውን ለክቡር ሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር ትክክል ነው? ምነው? ምክር ቤቱም ሆነ...

የጉራጌ የክልልነት ጥያቄ ትኩሳት

ቅዳሜ መጋቢት 16 ቀን 2015 ዓ.ም. በጉራጌ ዞን ወልቂጤ...