Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነትን መርሆዎችን ተከትሎ የሚሠራበት አሠራር መዘርጋቱን አስታወቀ

ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዳኝነትን መርሆዎችን ተከትሎ የሚሠራበት አሠራር መዘርጋቱን አስታወቀ

ቀን:

በወ/ሮ መዓዛ አሸናፊ የሚመራው የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት፣ የዳኝነት ሥራ ከማንኛውም አካል ወገንተኝነት ነፃ በሆነና መሠረታዊ የዳኝነት መርሆዎችን ብቻ በመመርኮዝ የሚሠራበት አሠራር መዘርጋቱን አስታወቀ፡፡

የፕሬዚዳንቷና የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ቃል አቀባይ አቶ ተስፋዬ ንዋይ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከዚህ በኋላ የዳኝነት አካሉ በሕገ መንግሥቱ ላይ በተቀመጠው አግባብ ብቻ ሥልጣንና ኃላፊነቱን ለመወጣት አክብሮ ይሠራል፡፡ ባለድርሻ ከሆነ የፍትሕ አካላት ጋር በመሆን የዳኝነት አካሉን ተቋማዊና ግለሰባዊ ነፃነት ባከበረ መንገድ፣ ለማኅበረሰቡ ፈጣንና ውጤታማ ፍትሕ ለመስጠት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ተባብሮ ለመሥራት ዝግጁ መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡

ዳኞች ከማንኛውም ውጫዊና አስተዳደራዊ ጣልቃ ገብነት ነፃ ሆነው ሙያዊ ሥራቸውን እንዲያከናውኑ በተደረጉ ጥረቶች በአጭር ጊዜ ውስጥ አበረታች ውጤት መመዝገቡን የጠቆሙት አቶ ተስፋዬ፣ ለዚህም ማረጋገጫ የሆኑት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ከዳኞችና ከፍርድ ቤቶች ተገልጋዮች በተገኘ አስተያየት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይኼ የሚሳየው ባልተመቻቸና ከፍተኛ የሥራ ጫና ባለበት ሁኔታ ውስጥም ሆነውም ቢሆን፣ ነፃነታቸውን ዕውን ለማድረግ በተደረገው ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤቱን ማየት እንደተቻለ አቶ ተስፋዬ አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቶች በሕገ መንግሥቱ የተጣለባቸውን የዳኝነት አገልግሎት ለኅብረተሰቡ በአግባቡ ለመስጠት ተዘጋጅተው መጠበቅ ቢኖርባቸውም፣ ለዘመናት ተከማችተው የነበሩትን መዝገቦች መቀነስና በየቀኑ ለሚከፈቱ መዝገቦች ዕልባት ለመስጠት፣ በዳኝነት ሥራ ላይ ጫናው እየጨመረ መምጣቱን አቶ ተስፋዬ ጠቁመዋል፡፡

ጫናዎቹን በአግባቡ በማስተናገድና ሕዝቡ የሚፈልገውን ሕጋዊና ፍትሐዊ የዳኝነት አገልግሎት በተገቢ ሁኔታ ለመስጠት፣ ዳኞችና የፍርድ ቤት ሠራተኞች ከፍተኛ ርብርብ እያደረጉ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ትኩረት ተሰጥቶት እየተከናወነ የሚገኘው፣ ‹‹አማራጭ የሙግት መፍቻ ሥርዓት መተግበር ነው፤›› ያሉት አቶ ተስፋዬ፣ ፍርድ ቤት መሪ የሆነ የአስማሚነት ሥርዓት በሁሉም ፍርድ ቤቶች ለማስጀመር የሚያስችሉ ሥራዎች በመሥራት ላይ መሆናቸውንም ጠቁመዋል፡፡

በዋናነትም በቤተሰብ፣ በንግድ፣ በሥራ ክርክርና ግንባታ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን አክለዋል፡፡

ፍርድ ቤቶች በተለያዩ ሕጎች ውስጥ የተደነገጉ የሰው ልጆችን ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች ለማረጋገጥ የሚያስችል ሕግ የመተርጎም ሥራዎች የሚከናወኑባቸውን ሁኔታዎች በመመቻቸት ላይ እንደሆነም አቶ ተስፋዬ አብራርተዋል፡፡

በዳኞች ላይ የሚታዩትን ክፍተቶች ለመሙላት ሥልጠናዎች እየተሰጡና ውይይቶችም እየተካሄዱ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...