Tuesday, May 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናበዩኒቨርሲቲዎች አንፃራዊ መረጋጋት እየተፈጠረ መሆኑ ተገለጸ

በዩኒቨርሲቲዎች አንፃራዊ መረጋጋት እየተፈጠረ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ መጡበት የተመለሱ በርካቶች ናቸው

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ማክሰኞ ኅዳር 9 ቀን ባወጣው መግለጫ፣ በዩኒቨርሲቲዎች አንፃራዊ መረጋጋት እየተፈጠረ መሆኑን አስታወቀ፡፡ ‹‹በዛሬው ዕለት ከሰዓት በአብዛኞቹ ዩኒቨርሲቲዎቻችን ሰላማዊ ሁኔታዎች ታይተዋል፡፡ ባለፈው ችግር ከነበረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ዛሬ ከሰዓት ትምህርት ያስጀመሩ አሉ፡፡ በተወሰኑት ደግሞ ከዶርም ውጪ በመማሪያ ክፍሎችና በአዳራሾች ውስጥ የነበሩ ተማሪዎች ወደ ዶርሞቻቸው ተመልሰዋል፣ እየተመለሱም ይገኛሉ፤›› ብሏል፡፡

ባለፈው ሳምንት በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ሕይወቱ ካለፈው ተማሪ ጋር በተያይዘ ወንጀሉን የሚያጣራ ግብረ ኃይል ሥራ መጀመሩን ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡ ባለፈው ሳምንት ከሕንፃ ላይ ተወርውሮ የተገደለው የሦስተኛ ዓመት ተማሪ ሕልፈት ከተሰማ በኋላ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ውጥረት መንገሡ ይታወሳል፡፡ ተማሪዎች በግንብ ተንጣላጥለው ሲሸሹ የሚያሳዩ ምሥሎችም በማኅበራዊ የትስስር ገጾች ከመታየታቸውም በላይ፣ ሴት ተማሪዎችም መደፈራቸው በሰፊው ሲነገር ነበር፡፡

- Advertisement -

በዩኒቨርሲቲዎች ያለው አንፃራዊ ሰላም ቀጣይነት እንዲኖረው ለማድረግም ከተለያዩ አካላት ጋር በትብብር እየተሠራ መሆኑን ሚኒስቴሩ አስታውቆ፣ ‹‹ሰላም የእያንዳንዱ ግለሰብ ውጤት እንደመሆኑ ለዩኒቨርሲቲዎቻችን ሰላም ሁላችንም ድርሻ አለን፡፡ ያንንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባል፤›› ሲል አክሏል፡፡

‹‹ሰሞኑን ስንገልጽ እንደነበረው የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎችን ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን ተከታታይ የማወያየት ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛሉ፡፡ በውይይቶቹ የተለያዩ ሐሳቦች ተንሸራሽረዋል፡፡ በዚህም መሠረት ተገቢ የሆኑና ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሥርዓት መፍጠር የሚያስችሉ መግባባቶች ላይም እየተደረሰ ይገኛል፡፡ በእነዚህ መድረኮች ከተደረጉ ጥልቅ ውይይቶች በኋላ የተገኙ ውጤቶች አሉ፤›› ሲል ሚኒስቴሩ አስረድቷል፡፡

በዚህም መሠረት ባለፉት ቀናት ችግር ከነበረባቸው ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ በተወሰኑት መማር ማስተማር መጀመሩን፣  በቀሪዎቹ ደግሞ ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያሳተፉ ውይይቶች ተካሂደው መግባባት ላይ ስለደረሱ በቀጣይ ቀናት ትምህርት እንደሚጀምሩ፣ እንዲሁም በቀጣይ ሊፈጠሩ የሚችሉ ችግሮችን ለመቀነስ የሚያግዙ ውይይቶችም እየተካሄዱ መሆናቸውን ጠቁሟል፡፡

‹‹ዩኒቨርሲቲዎቻችን ሰላማዊ የዕውቀት መንደር ብቻ ለማድረግ እየተሠራ ባለበት በአሁኑ ወቅት አንዳንድ የሚዲያ ተቋማት የኢትዮጵያ የብሮድካስት አዋጅን በተፃረረና ኃላፊነት በጎደለው መንገድ ያልተጣሩ ‹መረጃዎችን› እንደወረዱ ትክክለኛ መረጃ አስመስለው ለሕዝብ የማድረስ ተግባር በመፈጸም ላይ ይገኛሉ፤›› ብሎ ይኼንንም የሚከታተለውና ተገቢ ተጠያቂነትን የሚያረጋግጥ መሆኑ እንደተጠበቀ ሆኖ፣ የሚዲያ ተቋማት ዩኒቨርሲቲዎች ያሉበትን ሁኔታ አስመልክቶ መረጃ ማግኘት ሲፈልጉ ከዩኒቨርሲቲዎቹ ፕሬዚዳንቶችና የኮሙዩኒኬሽን ክፍል ኃላፊዎች እንዲሆን አሳስቧል፡፡

በሌላ በኩል ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ተማሪዎች ትምህርታቸውን አቋርጠው ወደ መጡበት መመለሳቸው ተረጋግጧል፡፡ በዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ የሚፈጠሩ ግጭቶችን በመሸሽ ወደ ቤተሰቦቻቸው የተመለሱ ተማሪዎች በጭንቀት ውስጥ መክረማቸውን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡ ሰላማዊ ሁኔታ ካልተፈጠረና በመማር ማስተማሩ ሒደት በተረጋጋ ሁኔታ ውስጥ የማይከናወን ከሆነ ተመልሶ ለመሄድ ፈቃደኛ አለመሆናቸውን ተማሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ በጎንደር ዩኒቨርሲቲ በአንድ ሕንፃ ላይ አጋጥሞ የነበረ የእሳት አደጋ በቁጥጥር ሥር መዋሉን፣ በሰው ላይ የደረሰ አደጋ አለመኖሩንና መንስዔው በመጣራት ላይ እንደሆነ ሚኒስቴሩ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...