ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የኢሕአዴግ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ለሦስት ቀናት ያደረገውን ስብሰባ ካጠናቀቀ በኋላ፣ በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ማክሰኞ ኅዳር 9 ቀን 2012 ዓ.ም. ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሦስቱ የኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች ተዋህደው የሚፈጥሩት የብልፅግና ፓርቲ ለኢትዮጵያ በቁስ ብቻ ሳይሆን በክብርም፣ በነፃነትም፣ በሁሉም ሁለንተናዊ መንገዶች ብልፅግ፣ ማረጋገጥ የሚችል እንደሆነና አሁን ባለችው ኢትዮጵያ ውስጥ የተበታተነ ጉልበት ስብስብ ብሎ በጋራ በመቆም መምራት እንዲቻል መወሰን መቻሉ፣ እጅግ በጣም ትልቅ ውሳኔ ነበር ሲሉ አስታውቀዋል፡፡