ይዘት
አንድ፡ መካከለኛ ሙዝ
አንድ፡ እንቁላል
ሁለት፡ የሾርባ ማንኪያ ዘይት
አንድ፡ የቡና ስኒ የተከተፈ ኦቾሎኒ
ሁለት፡ የቡና ስኒ አጃ (የቆርቆሮ)
ሦስት፡ የቡና ስኒ ዱቄት
አንድ፡ የሻይ ማንኪያ ቤኪንግ ፖውደር
እሩብ፡ የሻይ ማንኪያ ሶዳ
ግማሽ፡ የሻይ ማንኪያ ቀረፋ
አንድ፡ የቡና ስኒ ስኳር
አሠራሩ
1. ሙዙን ልጦ ማላምና በሚሠራበት እቃ ላይ ስኳሩን መጨመር
2. እንቁላሉን ዘይቱን ኦቾሎኒውን አጃውን ጨምሮ ማሸት
3. ዱቄቱን ቤኪንግ ፖውደሩን ሶዳውንና ቀረፋውን መንፋት እተደባለቀው ውስጥ ጨምሮ ማሸት
4. መጋገሪያውን ቅቤ መቀባት
5. በደንብ በጋለ ምድጃ አሥራ አምስት ደቂቃ ያህል ማብሰልና ማውጣት
– ገነት አጥናፉ ‹‹የቤት መስናዶ በመልካም ዘዴ›› (1955)