Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ተጠናክሮ ይቀጥላል

ቀን:

ሰብል ማሰባሰብ እየተከናወነ ነው

በሔለን ተስፋዬ

በዓመቱ 12.5 ሚሊዮን ሔክታር መሬት የሸፈነው ሰብል ሰሞኑን በጀመረው ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ይበላሻል የሚል ሥጋት በመኖሩ ሰብል የማሰባሰብ ሥራ መጀመሩን  ግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ያልተጠበቀ ዝናብ በተለያዩ የአገሪቱ ክልሎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የሚኒስቴሩ ሕዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ከበደ ላቀው ለሪፖርተር የገለጹ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት ሚኒስቴሩ ባደረገው የማነቃቃት ሥራ በኦሮሚያ 40 በመቶ፣ በአማራ ከ20 እስከ 30 በመቶ፣ በደቡብ 10 በመቶ፣ በትግራይ 60 በመቶና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ አንድ በመቶ የሚሆን ሰብል ለማሰባሰብ በሒደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡  

አቶ ከበደ፣ የደረሱ ሰብሎችን ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ ለመከላከል ከፍተኛ ጥንቃቄና ርብርብ ካልተደረገ፣ የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት እንቅፋት ይሆናል ብለዋል፡፡ ሰብል የማዳን ሥራው ተጠናክሮ እንዲቀጥል፣ ያልደረሱ ሰብሎች መባከናቸው እንደማይቀርና የደረሱትንም ሳይባክኑ በጥንቃቄ እንዲሰበስቡ ይደረጋል ብለዋል፡፡

በጋምቤላ ክልል አቦቦ ወረዳ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ መከሰቱን አርሶ አደሮችና ባለሀብቶች መናገራቸው ይታወሳል፡፡ በወረዳው እየጣለ ያለው ዝናብ በቆሎ፣ ሰሊጥና ሌሎችም ሰብሎች እንዲበላሹ ምክንያት መሆኑ ተሰምቷል፡፡ በአካባቢው የተከመረ የበቆሎ ምርት ሳይቀር እየተበላሸ መሆኑን፣ ሰብሉን ለማሰባሰብ ጥረት ቢደረግም፣ ዝናቡ ፋታ እንዳልሰጠ በዚህም የማሰባሰብ ሥራው ፈታኝ እንደሆነ አርሶ አደሮቹ ተናግረዋል፡፡

በተለይም በማሽላና በሰሊጥ ምርት ላይ ዝናብ በመጣሉ ሳቢያ የጥራት ችግር ሊያስከትል እንደሚችል አንዳንድ ባለሀብቶች ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የጉራጌ ዞን ሕዝብ ግንኙነት በማኅበረሰብ ትስስር ገጹ ላይ በኢትዮጵያ አየር ትንበያ መረጃ መሠረት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት ስለሚችል አርሶ አደሩ የደረሰ ሰብል እንዲያሰባስብ የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በዞኑ ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብ በተጨማሪ የአንበጣ መንጋ ሊከሰት እንደሚችል ሥጋት መኖሩን፣ በዓመቱም 168,974 ሔክታር መሬት በተለያዩ ሰብሎች መሸፈኑ ተገልጿል፡፡ በተደረገው ግምገማ 14 ሚሊዮን 831,974 ኩንታል ምርት የሚጠበቅ ሲሆን፣ ይህን ወቅቱን ካልጠበቀ ዝናብና ከአንበጣ መንጋ መታደግ ከተቻለ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ በተለያዩ ወረዳዎች የደረሱ ሰብሎችን በኮምባይነርና በሰው ኃይል በመታገዝ እየተሰበሰበ እንደሚገኝም ተገልጿል፡፡  

የሰብል ማሰባሰቡ ያስፈለገበት ወቅቱን ባልጠበቀ ዝናብ ምክንያት ብቻ ሳይሆን፣ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የአንበጣና የግሪሳ ወፍ ሥጋት በመኖሩ እንደሆነም አቶ ከበደ ተናግረዋል፡፡     

በምሥራቅና በሰሜን ምሥራቅ የአገሪቱ አካባቢዎች በስድስት ክልሎችና በ61 ወረዳዎች የነበረው የበረሃ አንበጣ ወረርሽን የመከላከል ሥራ ቢሠራም፣ ሙሉ ለሙሉ እንዳልተወገደ ይታወቃል፡፡ በአንዳንድ የሰሜን፣ የምሥራቅና የመካከለኛ የአገሪቱ ተፋሰሶች ገናሌ ዳዋ፣ ዋቢ ሸበሌ፣ ኦጋዴን፣ የመካከለኛውና የታችኛው ስምጥ ሸለቆ፣ ኦሞ ጊቤ፣ የዓባይ ደቡባዊ ክፍል፣ ባሮ አቦቦ ተፋሰሶች፣ ምሥራቅ ዓባይ፣ ተከዜ ተፋሰሶች፣ አዋሽ ምዕራብና ምሥራቅ ወለጋ፣ ጅማ፣ ኢሉአባቦራ፣ አርሲ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና ጋምቤላ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ ሊከሰት እንደሚችል ብሔራዊ ሜቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...