Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጤና አዋኪ ነፍሳትን ለማጥፋት ተስፋ የተጣለበት ቴክኖሎጂ

ጤና አዋኪ ነፍሳትን ለማጥፋት ተስፋ የተጣለበት ቴክኖሎጂ

ቀን:

ከሰሃራ በታች በሚገኙ አገሮች ገዳይ ከሆኑ ቀዳሚ በሽታዎች የሚመደበውን ወባ ለመከላከል በዓለም አቀፍ፣ በአኅጉርና በአገር ደረጃ የተለያዩ ጥረቶች ሲከናወኑ ቆይተዋል፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ ወባን ለማጥፋት ከተሠሩ ሥራዎች አንዱ ወንድ ወባን ጨረር ተጠቅሞ ማምከን ይገኝበታል፡፡

የነፍሳት ወሊድ መቆጣጠሪያ ተደርጎ የሚወሰደው ነፍሳትን በጨረር የማምከን ቴክኖሎጂ፣ ነፍሳት እንዳይባዙ በማድረግ ቁጥራቸው እንዲቀነስ የሚያስችል ዘዴ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደምም በግብርናው ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ነፍሳትን ለማጥፋት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡

ከአሠርታት በፊት በአሜሪካ ግብርና ቢሮ የተጀመረውና ሰብልንና የቁም ከብቶችን የሚያጠቁ ነፍሳትን ለማጥፋት የዋለው ወንድ ነፍሳትን የማምከን ቴክኖሎጂ፣ የወባ ትንኝንም ለማምከን እየተሠራበት ይገኛል፡፡

የዓለም ጤና ድርጅት፣ የወባን ሥርጭት ለመቀነስ ጥቅም ላይ እየዋለ የሚገኘውን ወባን የማምከን ቴክኖሎጂ፣ ለዓለም ሥጋት እየሆኑ ለመጡትና በነፍሳት ምክንያት ለሚተላለፉት ችጉንጉኒያ፣ ደንጉና ዚካን ለማጥፋት ሙከራ እንደሚደረግ አስታውቋል፡፡

እንደ ድርጅቱ መግለጫ፣ በቆላ በሽታዎች የምርምርና ሥልጠና ፕሮግራም (ቲዲአር)፣ የዓለም አቶሚክ ኤጀንሲ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የምግብና ግብርና ድርጅት እንዲሁም የዓለም ጤና ድርጅት በመተባበር ነፍሳትን በጨረር ለማምከን ለሚፈልጉ አገሮች መመርያ አዘጋጅተዋል፡፡

የዓለም ግማሹ ክፍል በደንጉ በሽታ አደጋ ውስጥ መገኘት

ድርጅቱ እንደሚለው፣ ግማሹ የዓለም ክፍል በደንጉ በሽታ ሥጋት ውስጥ ወድቋል፡፡ በዓለም ጤና ድርጅት ተቀዳሚ ሳይንቲስት ሱመያ ስዋሚናታን (ዶ/ር)፣ ደንጉ፣ ችጉንጉኒያና ዚካን ለመቆጣጠር የሚሠራው ሥራ በተለመደው አካሄድ ከቀጠለ ውጤታማ መሆን አይቻልም፡፡ በመሆኑም አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም በተለይ ነፍሳትን የማምከን ቴክኖሎጂ ተስፋ የተጣለበት ነው ብለዋል፡፡

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ የደንጉ ሥርጭት ከሚጠበቀው በላይ ጨምሯል፡፡ ለዚህም የአየር ንብረት ለውጥ፣ ቁጥጥር አልባው ከተሜነት፣ ትራንስፖርትና ጉዞ እንዲሁም በቂ ያልሆነ የተላላፊ በሽታዎች ቁጥጥር ሥርዓትና ትግበራ አለመኖር ችግሩን አባብሶታል፡፡

የደንጉ ወረርሽኝ አሁን ላይ በተለያዩ አካባቢዎች ተከስቷል፡፡ በህንድ የተወሰኑ አካባቢዎች ደንጉ የተከሰተ ሲሆን፣ በባንግላዴሽ ደግሞ እ.ኤ.አ. በ2000 ከተከሰተው የደንጉ ወረርሽኝ በኋላ ከፍተኛ የተባለው ወረርሽን አሁን ተከስቷል፡፡ ከ2019 መጀመርያ አንስቶም 92,000 ታማሚዎች የተመዘገቡ ሲሆን፣ በየቀኑ ከ1,500 በላይ ታማሚዎች ሆስፒታል እንደሚመጡም ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

በትንኝ አማካይነት የሚተላለፉት ደንጉ፣ ወባ፣ ዚካ፣ ቺኩንጉኒያ እንዲሁም ቢጫ ወባ በዓለም ከሚከሰቱ ኢንፌክሽኖች 17 በመቶውን ይይዛሉ፡፡ በእነዚህ በሽታዎች ምክንያትም በየዓመቱ ከ700 ሺሕ በላይ ሰዎች ይሞታሉ፡፡

ለሰው ልጅ በሽታ የሚያመጡ ትንኞችን ለማጥፋት የነፍሳት ማምከን ቴክኖሎጂ ተስፋ

በአሜሪካ በነፍሳት አማካይነት በግብርናው ዘርፍ የሚደርስ ውድመትን ለመከላከል ከ60 ዓመታት በፊት የተጀመረው ነፍሳትን በጨረር የማምከን ቴክኖሎጂ፣ ዛሬ ላይ በስድስት አህጉሮች ተግባር ላይ ውሏል፡፡

ከግብርናው ባለፈ በሰው ልጆች ጤና ላይ ጉዳት የሚያስከትሉ ነፍሳትን ለመቀነስ አገሮች ቴክኖሎጂውን ወስደው በሙከራ ጣቢያ መሞከር ይጠበቅባቸዋል፡፡ ለዚህ መመርያ የተዘጋጀ ሲሆን፣ በተለይ በደንጉና ዚካ ቫይረስ የተጠቁ አገሮች መድኃኒትን የተለማመዱና በትንኝ አማካይነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ሊጠቀሙበት ይገባል ተብሏል፡፡

ባለፉት 60 ዓመታት በግብርናው ዘርፍ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያተረፈው ይህ ቴክኖሎጂ፣ ሰዎችን ከነፍሳት አምጪ ተላላፊ በሽታዎች ለመከላከል ትልቅ አቅም እንደሚሆን ተስፋ ተጥሏል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...